Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 51

ብዙውን ጊዜ አንድ ቤተ ሰብ ወንዶችን፣ ያገቡ ሴቶችን፣ ያላገቡ ልጃገረዶችን፣ ወንድና ሴት ባርያዎችን፣ ዜግነት የሌላቸውን ሰዎችን፣ እና መንገደኞችን ወይም ከሌላ አገር የመጡ ሠራተኞችን ጨምሮ አራት ትውልዶችን ያካትታል።

ሃንስ ዋልተር ዎልፍ፥ Anthology of the Old Testament.

በዐዲስ ኪዳን ትረካዎች ውስጥ ወንጌል የተገለጸው ወደ ተለያዩ ሰዎች ቤት ሲመጣ ነው (ለምሳሌ፦ ማርቆስ 5፥19፤ ሉቃስ 19፥9፤ ዮሐንስ 4፥53፤ ዮሐንስ 4፥53፤ ዮሐንስ 1፥41-45 ወዘተ.) ቆርኔሌዎስ ለዚህ ዐይነተኛ ምሳሌ ይሆናል፣ ሐዋርያት ሥራ 10-11።. 1. የተፈጥሯዊና ከሰዎች ጋራ ያሉን ግንኙነቶች ገጽታዎች • የጋራ ዝምድና ግንኙነቶች (ወዲያኑ፣ የተራዘሙ፣ የተጨመሩ ቤተሰቦች) • የጋራ ወዳጅነቶች (ጓደኞች፣ ባልንጀሮች፣ ልዩ ፍላጎቶች) • የጋራ ትብብሮች (የሥራ ግንኙነቶች፣ ልዩ ፍላጎቶች፣ መዝናኛ፣ የብሔር ወይም የባህል ይምረቶች፣ ብሔራዊ ወይም አገራዊ ጥምረቶች) 2. ቤተ ሰብ ተኮር ስብከተ ወንጌል ውጤታማ የሆነው ለምንድን ነው? • ኦይኮስ (ቤተ ሰብ) ተኮር ስብከተ ወንጌል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፦ ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያቱ ያገለገሉት በዚህ መልኩ ነው። • ኦይኮስ (ቤተ ሰብ) ካሉ ግንኙነቶች ሁሉ ተፈጥሯዊና ብዙም አደጋ የሌለው ግንኙነት ነው። • ኦይኮስ (የቤተ ሰብ) አባላት እያንዳንዳቸው ሌላውን የቤተ ሰብ አባል የሚቀበሉ ናቸው (የጋራ ታሪክ፣ ተመክሮ፣ እና ዐሳቦችን ይገነባሉ) • የኦይኮስ ግንኙነቶች ለተልእኮ መስክ ምቹ ማረፊያ ናቸው።

Made with FlippingBook - Share PDF online