Church PLANT Manual, Amharic Edition
52 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
•
የኦይኮስ ግንኙነቶች ክትትል ይፈልጋሉ።
• ኦይኮስ መላውን የቤተ ሰብ አባላት ዒላማ ያደርጋል • የኦይኮስ ግንኙነቶች ዘወትር ዐዳዲስ የግንኙነት መሠረቶችን ይዘረጋሉ።
ዝክር፦ ወንጌል ወደ እናንተ የመጣው እንዴት ነው? የራሳችሁን የኦይኮስ ግንኙነቶችን ተመልከቱ
3. የከተማ ስብከተ ወንጌል አስከትሎቶች • በምታደርጓቸው እያንዳንዱ ግለሰባዊ ግንኙነቶች ውስጥ “ኢኮኖሚያዊ” በሆነ መንገድ ዐስቡ በዚያ መልኩም አሳድጉት። ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን ቤተ ሰብን ለመማረክ ጥረት አድርጉ። • ዘላቂ የሆነ ተጽዕኖ ለመፍጠር በግንኙነት መረባችው ውስጥ ተገቢ መሠረት አኑሩ። • የግለሰቦች መለወጥን ብትሹም መላው ቤተ ሰብ ላይ አትኩሩ • ወደ ክርስትና የተለወጡት ሁሉ ለራሳቸው ቤተ ሰቦች እንደ እንድርያስ እንዲሆኑ አበረታቷቸው (ዮሐንስ 1፥40-43) • በምታዩዋቸው የተለወጡ ሰዎች ዘንድ ባሏቸው የቤተ ሰብ
ግንኙነቶች ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የመልካም ብስራቱን መልእክት እንዲያንቀሳቅሰው በማመን ከእግዚአብሔር ዘንድ ጠብቁ።
II. ክትትል፦ በእግዚአብሔር ቤተ ሰብ ውስጥ ማካተትና መንከባከብ • ብያኔ፦ ለሕንጸትና ለፍሬያማነት ዐላማ፤ ለእግዚአብሔር ክብር በእግዚአብሔር ቤተ ሰብ ውስጥ መካተት።
Made with FlippingBook - Share PDF online