Church PLANT Manual, Amharic Edition

54 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

3. ቀጣይነት ያለው ትምህርት፣ ክብካቤ፣ እና ምገባ ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ፦ ዐዳዲስ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ቃልና ፈቃድ ማወቅ ያስፈልጋቸዋል፤ 1ጴጥሮስ 2፥2፤ ዕብራውያን 5፥11-6፥4 4. በእግዚአብሔር መንግሥት ዕይታ ለመኖርና በዚያ ሕይወት ለማደግ ጓደኞች አስፈላጊ ስለሆኑ፦ ዐዳዲስ ክርስቲያኖች ቅዱስ ሕይወት ይኖሩ ዘንድ የሚያበረታቷቸው ጓደኞች ያስፈልጓቸዋል፤ ዮሐንስ 13፥34-35 5. መደበኛ የሆነ አባታዊና ምጋቤያዊ ክብካቤ አስፈላጊ ስለሆነ፦ ዐዳዲስ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ስለ ነፍሳቸው ጉዳይ የሚተጉ እረኞች ያስፈልጓቸዋል፤ ዕብራውያን 13፥17 • የክትትል እንቅስቃሴዎች 1. በአካባቢ ካሉ አማኞች ጋራ መቀራረብ - ዕብራውያን 10፥24 25 2. ጌታን ከመከተል ውሳኔ በኋላ ወዳየውኑ መደበኛ የሆነ ግንኙነት መጀመር 3. አስተምህሯዊ ክብካቤና ትምህርት 4. ስልታዊ ወዳጅነት 5. ኦይኮስ ቤተ ሰብን ማወቅና ዘልቆ መግባት 6. ምገባና ክብካቤ 7. በክርስቶስ አካል ውስጥ ዐዲስ ግንኙነት መመሥረት • የክትትል ትግበራ 1. ጥምቀት 2. ስለ ድነትና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ትምህርት ጥልቅ ግንዛቤ ማዳበር

Made with FlippingBook - Share PDF online