Church PLANT Manual, Amharic Edition

የቡድን መልመጃዎች፥ መጀመርና መሰባሰብ • 61

መልመጃ 6 ባህልንና ዐውድን ማሰስ

ቡድናችሁ የመረጣችሁትን ማኅበረ ሰብ ባህልና ዐውድ ለማሰስ ወይም ለመረዳት ዕቅድ ማውጣት ያስፈልገዋል።

የውይይት ጥያቄዎች 1. ለክርስቲያኖች የተለያዩ ባህሎችን መረዳትና በዚያም ውስጠ መሳተፍ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 2. በዙሪያችሁ ካሉ ሰዎች ጋራ ያላችሁን ባህላዊ ልዩነት በተሻለ መልኩ ለመረዳትና ለማድነቅ እንደ ቤተ ክርስቲያን ምን ታደርጋላችሁ? 3. ቤተ ክርስቲያን በምትተክሉበት አካባቢ ዐውድ ውስጥ ወንጌልን ዐውዳዊ በማድረግ ማኅበረ ሰቡ ወንጌሉን በራሱ ቋንቋ እንዲረዳ ማድረግ የምትችሉባቸው መንገዶች ምንድን ናቸው? 4. ወንጌልን በዐውዳችሁ ውስጥ ውጤታማ በሆነ መልኩ ማወጅና መግለጥ ትችሉ ዘንድ ማሸኘፍ ያለባችሁ ባህላዊ መሰናክሎች ምንድን ናቸው? 5. ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው እውነታ በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ ተጽዕኖ የሚፈጥረውና የሚመራችሁ እንዴት ነው? 6. ይህ እውነታ ቤተ ክርስቲያናችሁን በምን መልኩ ይገልጸዋል፣ ይመራዋል፣ ያሳድገዋል? 7. ሌሎችን ለመድረስ የባህል ድንበሮችን ጥሶ መሄድን በተመለከተ ከኢየሱስ ምሳሌ ምን ትማራላችሁ? 8. የኢየሱስን ፍቅር ለሌሎች ለማካፈል እንደ ቤተ ክርስቲያን እስከ ምን ድረስ ለመሄድ ፈቃደኛ ናችሁ?

ሌሎች የስብሰባ የውይይት ጥያቄዎች 1. የስብሰባ ቦታ የሚያስፈልጋችሁ መቼ ነው?

Made with FlippingBook - Share PDF online