Church PLANT Manual, Amharic Edition

62 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

2. በገንዘብ ረገድ ምን ያስፈልጋችኋል? መጀመሪያ ማሟላት ያለባችሁ መሣሪያዎች ምንድን ናቸው? 3. በየሳምንቱ የሚከናወነው አገልግሎት ከአካባቢው ባህል አንጻር ምን ዐይነት መልክ ይኖረዋል? ለእያንዳንዱ የአገልግሎት ተግባራት ኀላፊነቱን የሚወስደው ማን ነው? በውይይታችሁ መሠረት በቀጣዮቹ ከ6-12 ወራት ውስጥ ግቦቻችሁን አዳብሩና ሰነድ አዘጋጁ። ግቦቻችሁ ሊለኩ የሚችሉ መሆናቸውን ርግጠኞች ሁኑ። ግልጽ የመጨረሻ ቀናትን አስቀምጡ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ግን ተጠሪ የሚሆን ሰው በኀላፊነት መድቡ። ግቦቻችሁን እስካስቀመጣችሁና ውሳኔያችሁን የምትወስኑበትን ቀን እስከቆረጣችሁ ድረስ ከኢቫንጄል ትምህርት በኋላ ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

Made with FlippingBook - Share PDF online