Church PLANT Manual, Amharic Edition
የቡድን መልመጃዎች፥ መጀመርና መሰባሰብ • 63
መልመጃ 7 ስብከተ ወንጌል እና ክትትል 1
ቡድናችሁ የስብከተ ወንጌል ኹነቶችን ለማዘጋጀትና በወንጌል የሚደረሰውን ማኅበረ ሰብ ለመከታተል ስልቶችን መቀየስና ዕቅድ ማዘጋጀት ያስፈልገዋል። መመሪያዎች ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች በቡድን ተወያይታችሁ መልሶቻችሁን መዝግባችሁ ያዙ 1. በቤተ ክርስቲያን ላይ ሰዎችን ለመጨመር ምን ዐይነት የስብከተ ወንጌል ኹነት ታዘጋጃላችሁ? 2. ዐዳዲስ አማኞችን የምትከታተሏቸው እንዴት ነው? 3. ለክትትል እንዲሆናችሁ ምን ዐይነት ስታትስቲካዊ መሣቲያዎች ትጠቀማላችሁ? 4. ዐዳዲስ አማኞችን ለመከታተተል አነስተኛ ቡድኖችን ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በምን መልኩ ታዘጋጃላችሁ? ስብከተ ወንጌሉን እንዴት ለመቀጠል ዐስባችሁ? 5. ለመጀመሪያ ስብከተ ወንጌል የምትሄዱት ወዴት ነው? እንዴትስ ነው የምትደርሷቸው? 6. በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎችን ለመድረስ በተሻለ መልኩ ማገልገል የሚያስችሏችሁ ልትጠቀሙበት የምትችሏቸው የአካባቢ፣ የከተማ፣ የአገር ወይም የቤተ ክርስቲያን ሀብቶች አሉ? 7. ዐዳዲስ አማኞችንና ተሳታፊዎችን እንዴት ነው የምትከታተሏቸው? የክትትሉ ኀላፊነት የማን ነው? የሚያስፈልጓቸው መሣሪያዎችስ ምንድን ናቸው?
1 Adapted from the exercises “Expand the Church” and “Establish the Church” in Ripe for Harvest , pp. 288-291 and 296-300.
Made with FlippingBook - Share PDF online