Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 3: ማሳደግና ሽግግር • 73
2. ለመንግሥቱ የተለየ አኗኗር 3. ቅድስናን ከልብ መከተል 4. በግል ሕይወት ውስጥ ያለ ሥነ ሥርዓት 5. ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ ዐብሮ ሠራተኛ መሆን 6. ለሌሎች በምግባራቸው፣ በንግግራቸውና በአኗኗራቸው መልካም ምሳሌ መሆን (የመንፈስ ፍሬ) • አጨንጋፊ ሰይጣናዊ ስልት፦ የአገልግሎት ተግባራትን ወይም/እና ጠንክሮ መሥራትን በመንፈሳዊነት እና ክርስቶስቶን የመምሰል ምትክ ማድረግ። • ቍልፍ ደረጃዎች I. በክርስቶስ መኖር II. እግዚአብሔርን ለመምሰል ራስን ማስገዛት III. በሁሉም ነገር ቅድስናን መሻት • ውጤት፦ በጠንካራ ክርስቶስን በሚመስል ሕይወት ሌሎችም ክርስቶስን እንዲመስሉ ምሳሌ መሆን። III. ብቃት • ትርጉም፦ የተመደቡባቸውን ሥራዎችና አገልግሎቶች በብቃት ለመወጣት በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ምላሽ መስጠት። • ልብ ሊባሉ የሚገቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፦ 2ጢሞቴዎስ 2፡ 15፣ 2ጢሞቴዎስ 3፥16-17፣ ሮሜ 15፥14፣ 1ቆሮንቶስ 12 • ወሳኝ ሐሳብ፦ ከእግዚአብሔር የሆነ መሪ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል የመንፈስ ቅዱስን ስጦታና ቅባት ይሠራል። • ዋና ዋና ነጥቦች፦ 1. ስጦታው ከመንፈስ ቅዱስ ነው።
Made with FlippingBook - Share PDF online