Church PLANT Manual, Amharic Edition

86 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

8. ለዐዳዲስ የቤተ ክርስቲያን አመራሮች እንደ መስፈርት የሚያገለግላችሁ ምንድን ነው? 9. ሴቶችን እና ወንዶችን ለቤተ ክርስቲያን አመራርነት የምታስታጥቋቸው እንዴት ነው? 10. የዐዳዲስ መጋቢያንና እረኞች (ሽማግሌዎች) ሥርዓተ ሹመታችሁ ምን ይመስላል? በውይይታችሁ መሠረት በቀጣዮቹ ከ6-12 ወራት ውስጥ ግቦቻችሁን አዳብሩና ሰነድ አዘጋጁ። ግቦቻችሁ ሊለኩ የሚችሉ መሆናቸውን ርግጠኞች ሁኑ። ግልጽ የመጨረሻ ቀናትን አስቀምጡ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ግን ተጠሪ የሚሆን ሰው በኀላፊነት መድቡ። ግቦቻችሁን እስካስቀመጣችሁና ውሳኔያችሁን የምትወስኑበትን ቀን እስከቆረጣችሁ ድረስ ከኢቫንጄል ትምህርት በኋላ ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

Made with FlippingBook - Share PDF online