Church PLANT Manual, Amharic Edition
የቡድን መልመጃዎች፥ ማሳደግና ሽግግር • 87
መልመጃ 9 ሽግግር፥ የመብዛት ስልቶች 1
ቡድናችሁ መብዛትን በተመለከተ ግልጽ የሆነ ርእይ፣ ስልትና ዕቅድ ያስፈልገዋል።
መመሪያዎች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች በቡድን በመስራት መልሶቻችችን ጽፋችሁ አስቀምጡ። 1. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ተተኪ የሚሆኑ መሪዎችን ለይተህ ማወቅ፣ ዕውቅና መስጠትና ማሠልጠን የምትችሉለው እንዴት ነው? 2. ታማኝ መሪዎች፣ ዲያቆናት፣ ሽማግሌዎችና መጋቢዎች እንዲሆኑ እንዴት አስታጥቃችሁ ትሾማላችሁ? 3. ቤተ ክርስቲያናችሁ ልጅ ቤተ ክርስቲያን ለመውለድ ዝግጁ መሆኗን የሚጠቁሙ ምልክቶች ምንድን ናቸው? 4. ቤተ ክርስቲያን ራሷን የምታስተዳድር፣ ራሷን የምትደግፍና አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት ማኅበር አባል ለመሆን ምን ማድረግ አለባት? 5. የመጀመሪያ አመራር ሚናዎችን ወደ ሰፊው ቡድን እንዴት የምታሸጋግሩት እንዴት ነው? 6. ዐዳዲስ የቡድኑ አባላት ሲያድጉ የምትሰጧቸው ኀላፊነቶች ምንድን ናቸው? 7. ለኅብረት፣ ርስ በርስ ለመደጋገፍና የጋራ አገልግሎት ለመሥራት ሲባል በአካባቢያችሁ በሚደረጉ ትልልቅ ስብሰባዎች ወይም ቡድን ውስጥ እንደ አጋር አገልግሎት በታማኝነት የምትመሩት እንዴት ነው?
1 Adapted from an Evangel School exercise in Ripe for Harvest , pp. 416-420.
Made with FlippingBook - Share PDF online