Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

1 1 2 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ሐ. እግዚአብሔር የክርስቶስን መንግስት ክብር በመልካም ስራ እና አገልግሎት ለማሳየት ለርህራሄ እና ለፍትህ አገልግሎት ጠርቶናል።

1. የተፈጠርነው እግዚአብሔር እንድንሰራው ለጠራን ለበጎ ሥራ ​ነው፤ ኤፌ. 2.10.

2. ለመልካም ሥራ የምንቀና የክርስቶስ ልዩ ህዝብ ነን፣ ቲቶ 2፡14.

3. በሁሉም ሰዎች መካከል በተለይም በእምነት ቤተሰቦች መካከል ፍትህን ለማድረግ መፈለግ አለብን፣ ገላ. 6.9-10.

4. የተጠራነው የእምነታችንን እውነታ በፍቅር አገልግሎት በተለይም ለድሆች እና ለመበለት ለመግለጥ ነው።

ሀ. በድርጊት ያልተደገፈ እምነት ባዶ እና የሞተ እምነት ነው፣ ያዕ 2፡14-26.

4

ለ. የእግዚአብሔር ፍቅር የክርስቲያን ወንድሙን ተግባራዊ ፍላጎት ቸል ባለ ሰው ልብ ውስጥ አያድርም 1ኛ ዮሐንስ 3፡16-18።

ሐ. እውነተኛ ሃይማኖት በእግዚአብሔር ፊት መበለቶችንና ድሀ አደጎችን መንከባከብ እና ከዓለም እድፍ እራስን መጠበቅ ነው፣ ያዕ 1፡27.

መ. ለድሆች፣ ለመጻተኞች፣ ለተራቡ፣ ለተጠሙ፣ ለታመሙ፣ ለታሰሩ፣ እና ለታረዙት የምናደርገው ወይም የማናደርገው ነገር ለኢየሱስ ክርስቶስ እንዳደረግነው ወይም እንዳላደረግነው ይቆጠራል፣ ማቴ. 25.31-46.

ማጠቃለያ

» ወደ ደቀመዝሙርነት የሚጠራን ያው ቃል በእግዚአብሔር ህዝብ (ላኦስ) ውስጥ እንደ ክብሩ ቤተሰብ አባላት በክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ እንድንኖር እና እንድንሰራ ይጠራናል። » ሌሎችን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት አዲሱን ህይወት ስንኖር እርስ በርሳችን በመዋደድና በማገልገል በክርስቶስ ነጻነት እንድንኖር ቃሉ ይጠራናል።

Made with FlippingBook Annual report maker