Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 1 1 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
» ወደ ደቀመዝሙርነት፣ ማህበረሰብ እና ነፃነት የሚጠራን ያው ቃል ወደ ተልእኮም ይጠራናል። የተጠራነው ታላቁን ተልዕኮ እንድንፈጽም፣ ከመንፈሳዊ ጠላታችን ከዲያብሎስ ጋር እንድንዋጋ እና የመንግስቱን ህይወት በፍቅራችን እና በበጎ ስራዎቻችን እንድናሳይ ነው።
የሚከተሉት ጥያቄዎች የተነደፉት በሁለተኛው የቪዲዮ ክፍል ውስጥ ያለውን ይዘት ለመገምገም ለመርዳት ነው። የሚጠራውን የቃሉን ምንነት በመረዳት፣ የእግዚአብሔር ሰው መሆን ምን ማለት እንደሆነ እና የእሱ የተመረጡ ሰዎች አካል መሆን ምን ማለት እንደሆነ ፍንጭ እናገኛለን። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. “ዳግም መወለድ” እና “ልጅነት” የሚሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ትርጉም ምንድን ነው? እነዚህ ጽንሰ-ሐሳቦች የእግዚአብሔርን በማኅበረሰብ ውስጥ የመኖር ጥሪን ምንነት እንድንገነዘብ የሚረዱን እንዴት ነው? 2. መንፈስ ቅዱስ፣ እንደልጅነት መንፈስ፣ እንደ እግዚአብሔር ቤተሰብ ሰዎችና አባላት እንድንኖርና እንድንሰራ የሚረዳን እንዴት ነው? 3. ቃሉ ወደ ማህበረሰቡ እንደጠራን የሚገልጹ ዋና ዋና አንድምታዎች ምን ምን ናቸው? ከእነዚህ አንፃር የደቀመዝሙርነት ሕይወትን መምራት እና የጤነኛ አማኞች አካል አባል መሆን አለመቻል ይቻላል? መልስህን አስረዳ። 4. በኢየሱስ ክርስቶስ በነጻነት እንድንኖር ተጠርተናል ማለት ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር ነፃ ያወጣን እንዴት ነው? 5. እግዚአብሔር ነፃ ያወጣን ከምን አይነት ነገሮች ነው? እግዚአብሔር ነፃ ያወጣንስ ምን አይነት ነገሮችን እንድናደርግ ነው? 6. ጌታ በነጻነታችን ላይ ምን ገደቦችን አድርጓል፣ በሌላ አነጋገር ለምንደሰትባቸው ነገሮች ላይ ባለን ነፃነት ላይ የተቀመጡ ገደቦች (ካሉ) ምን ምን ናቸው? በክርስቶስ ነፃ የወጣነው ለምንድነው? 7. ለተልዕኮ ተጠርተናል። በእግዚአብሔር ተልእኮ ውስጥ ለመሳተፍ ከቤተክርስቲያን ጥሪ ጋር የተያያዙት ልዩ ድርሻዎች ወይም ተግባራት ምንድን ናቸው? 8. ኢየሱስ ዲያብሎስና አገልጋዮቹን ድል ካደረገ፣ እኛም በዚህ ዓለም ውስጥ ከጠላት ጋር ስንዋጋ ምን እንድናደርግ ተጠርተናል? 9. የተጎዱትንና ድሆችን ወክሎ በመልካም አገልግሎት ላይ መሳተፍ በህይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ጥሪ የሚፈፀመው እንዴት ነው?
መሸጋገሪያ 2
የተማሪ ጥያቄዎች እና ምላሾች
ገጽ 185
11
4
Made with FlippingBook Annual report maker