Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
1 1 4 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ግንኙነት
ይህ ትምህርት የሚያተኩረው የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ ምላሽ በሚሰጥ ሰው ሕይወት ላይ ባለው የእግዚአብሔር ጥሪ ስፋት እና ጥልቀት ላይ ነው። ቃሉ ወደ ደቀመዝሙርነት፣ ወደ ማህበረሰብ፣ ወደ ነፃነት፣ እና በተልእኮ እንድንሳተፍ ይጠራናል። አዲስ ሕይወትን የሚሰጠው ይኸው ቃል፣ በዚህ ዓለም ውስጥ የአምባሳደርነት ኃላፊነታችንን በመወጣት ለኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በመሆን ሥር ነቀል የመታዘዝ አኗኗር እንድንመራ ይጠራናል። በእምነት አዲስ ሕይወትን በውስጣችን የሚፈጥረው ቃል እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንድንኖር፣ እርሱንና መንግሥቱን በማገልገል፣ ለፈቃዱ ታዛዦች እንድንሆን ይጠራናል። አብ የሚያምኑትን ሁሉ እርሱን አብዝተው እንዲወዱት፣ ከሁሉ በላይ ጌታ ለሆነው ለእርሱ ብቻ እንዲኖሩ ራሳቸውን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያቀርቡ ይጠራቸዋል። በዚህ ዓለም ውስጥ እንደ እንግዶችና መጻተኞች በክርስቶስ አዲስ ማንነት አለን። በአለም ውስጥ እንደ ክርስቶስ አምባሳደሮች ሆነን በመጥፎ አለም መካከል እንደ እግዚአብሔር መንግስት ዜጎች እየኖርን እንደ ኢየሱስ ተወካዮች ልንኖር ይገባናል። እኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች ነን፥ ለክብሩ በመስዋዕትነት የምንኖር ባሪያዎች ነን። እንደ ራሱ እስረኞች፣ እንደ አገልጋዮቹ የምንሆነውን ሁሉ በደስታ ልንፈጽምና እርሱ በሚመራን መሠረት እርሱን ማክበር እና ፈቃዱን መፈጸም ይኖርብናል። ለግለሰባዊ ደቀመዝሙርነት ተጠርተናል፣ ደግሞም በእግዚአብሔር ህዝብ (ላኦስ) ውስጥ እንደ የእግዚአብሔር የከበረ ቤተሰብ አባላት በመሆን በማህበረሰብ ውስጥ እንድንኖርና እንድንሰራ ተጠርተናል። በዳግም መወለድ እና በልጅነት መንፈስ ቅዱስ አዲሱ አማኝ የራሱን የእግዚአብሔርን መንፈሳዊ ዲኤንኤ እንዲጋራና በዚህም የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል እንዲሆን አድርጓል። የእግዚአብሔር ሕዝብ አባላት እንደመሆናችን መጠን በኢየሱስ ክርስቶስ በነፃነት እንድንኖር፤ ነፃነታችንን እንደ ኃጢአት መሸፈኛ ሳይሆን ሌሎችን ለመውደድ ዕድል ልንጠቀምበት (ታላቁን ትእዛዝ በመፈጸም) እና ሌሎችን ለማዳን ሲባል ስለ ክርስቶስ ግልጽ ምሥክርነት ለመስጠት ተጠርተናል። ወደ ደቀመዝሙርነት፣ ማህበረሰብ እና ነፃነት የሚጠራን ቃል ወደ ተልእኮም ይጠራናል። የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች እንደመሆናችን መጠን ታላቁን ተልዕኮ እንድንፈጽም፣ ከመንፈሳዊ ጠላታችን ከዲያብሎስ ጋር እንድንዋጋ እና የመንግስቱን ህይወት በፍቅራችንና በበጎ ስራዎቻችን እንድናሳይ ተጠርተናል።
የቁልፍ ፅንሰ-ሀሳቦች ማጠቃለያ
ገጽ 185 12
4
Made with FlippingBook Annual report maker