Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 1 5
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ይህ ትምህርት ፈተና የለውም
ፈተና
ይህ ትምህርት የቃል ጥናት ጥቅስ የለውም
የቃል ጥናት ጥቅስ ምዘና
ይህ ትምህርት የቤት ስራ/መልመጃ የለውም
የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ
1
እውቂያ
የባለሙያ ጥያቄ ዛሬ በአጠቃላይ ህብረተሰብ ውስጥ ሙያዊም ሆነ የግል ችግር ያለባቸው አብዛኞቹ ሰዎች ችግሩን በራሳቸው ለመፍታት ወይም “አዋቂዎችን” - ሳይንቲስቶችን፣ ዶክተሮችን፣ አማካሪዎችን ወይም ሌሎችን ማማከሩ የተለመደ ነው። በአሁኑ ወቅት የእግዚአብሔር ቃል የሰዎችን ችግር ለመፍታት ምን ቦታ አለው? በአሁኑ ወቅት በኅብረተሰቡ ውስጥ ለእግዚአብሔር ቃል ትምህርት አክብሮት እንዳለህ የምታየው ወይም ማየት የሚሳንህ በምን መንገዶች ነው? ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነትን በሚመለከት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንህ አገልግሎት በወጣቶች ቡድን ውስጥ አንድ ወሳኝ ጉዳይ እንደሚነሳ አስብ። ብዙዎቹ ህጻናት በአካባቢያቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ የተለመደ እና የሚጠበቅ መሆኑን እና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን እና የመፀነስ አደጋን እስከተከላከሉ ድረስ ምንም ችግር እንደሌለው እየተማሩ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚነሱ ክርክሮች በወጣት ቡድናችሁ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ተማሪዎችን በመጠኑም ቢሆን እየማረኩ መጥተዋል፤ እነዚህ ተማሪዎች በዛሬው ጊዜ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ያለ አንድ ጥንታዊ መጽሐፍ ከነሱ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እያሰቡ ነው። በሕይወታቸው የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣን ላለመቀበል ለሚታገሉት እና በኃላፊነት እና በግልጽ እስከያዝናቸው ድረስ ነገሮች ምንም አይደሉም ብለው ለሚያምኑት ልጆች ምን ትላቸዋለህ? ኢየሱስ - እሺ፥ መጽሐፍ ቅዱስ - እምቢ! ስለኢየሱስ ማንነት እና ትምህርት በጥልቀት የሚያምኑ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነትነት ላይ ችግር ያለባቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ኢየሱስ ፍቅርን፣ ትሕትናንና በጎ ፈቃድን በሰዎች መካከል አስተምሯል፥ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ብዙ ዘመናዊ ሰዎች ለማመን በሚከብዷቸው ነገሮች ስለ መላእክት፣ አጋንንት፣ እና ተአምራት በሚናገሩ ያልተለመዱ ትምህርቶች የተሞላ ነው። አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጉዳዮችን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት መቀበል የሚቻል ይመስልሃል? ለኢየሱስ “እሺ!” በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስላሉት ብዙ ነገሮች ግን “እምቢ” ወይም “እርግጠኛ አይደለሁም”
1
ገጽ 162 5
2
3
Made with FlippingBook Annual report maker