Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

1 6 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ማለት ይቻላል? ከኢየሱስ ጋር እውነተኛ ህብረትና እምነት እንዳለህ ለመናገር መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ሁሉ ማመን የለብህም? ለምን?

የሚፈጥረው ቃል ክፍል 1

ይዘት

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል እና የጌታ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል የጽሑፍ መዝገብ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አምላከ ሥላሴ ለእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ዋስትና ይሰጣል፤ ይህም ፍጹም እምነት የሚጣልበት ነው። በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር ፈጣሪ እና ሕይወት ሰጪ ቃል አማካኝነት ነው። ጌታ አምላክ ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደሚመልስ ሁለተኛው የሥላሴ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ራሱን ገልጧል። የዚህ “የሚፈጥረው ቃል” የተሰኘ የመጀመሪያ ክፍል አላማችን የትምህርቱን አንድምታዎች እንድታይና እንድትረዳ ለማስቻል ነው። ይህም:- • ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል እና የጌታ ሕያውና ዘላለማዊ ቃል የጽሑፍ መዝገብ መሆናቸውን። የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር አምላከ ሥላሴ ለእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ዋስትና እንደሚሰጥና ይህም ፍጹም እምነት የሚጣልበት መሆኑን፥ • በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር ፈጣሪ እና ሕይወት ሰጪ ቃል አማካኝነት መሆኑን • ጌታ አምላክ ራሱን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ዓለምን በመቤዠት እና በጽድቅ አገዛዙ ሥር ያለውን ጽንፈ ዓለም እንዴት እንደሚመልስና ሁለተኛው የሥላሴ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ራሱን እንዴት እንደሚገልጥ ትረዳ ዘንድ ነው።

የክፍል 1 ማጠቃለያ

1

I. ቅዱሳት መጻሕፍት (መጽሐፍ ቅዱስ) ከእስትንፋሱ ወጥቶ ከማንነቱና ከሥራው ጋር የተቆራኘ የሕያው እግዚአብሔር ቃል ነው።

የቪዲዮ ክፍል 1 መግለጫ

ሀ. ቅዱሳት መጻሕፍት (መጽሐፍ ቅዱስ) ሕያው እና ዘላለማዊ ቃል ነው።

1. የእግዚአብሔር ቃል ዘላለማዊ ነው፣ የእግዚአብሔርን የፍፁም እውነተኝነት እና ስልጣን ባህሪም ይዟል። 1ጴጥ. 1፡23-25።

Made with FlippingBook Annual report maker