Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 1 7
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
2. ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው።
ሀ. 2 ጢሞ. 3፡16-17
ለ. እግዚአብሔር የራሱን ፈጣሪ ሕይወት በቃሉ ውስጥ አኑሯል።
3. እግዚአብሔር ቅዱሳን መጻሕፍትን በእርሱ መንፈስ የቃል በቃል መሪነት እንዲጽፉ እንደ ፈቀደ ማመን አይጠበቅብንም። ይልቁንም መንፈስ ቅዱስ የጸሐፊዎቹን የቃላት አቅም፣ ልምዶች እና ችሎታዎች እሱ ባሰበው ልክ እንደ ተጠቀመ እናምናለን ስለዚህም በጽሑፎቻቸው ያቀረቡት ሁሉ የራሱ ፍጥረት ነው ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስ ጸሐፊዎቹን ያነሳሳቸው እርሱ የሰነዶቹ ጸሐፊ ተብሎ ሊጠራ በሚችልበት መንገድ ነው። በዚህ መንገድ ነው ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን ለእምነት እና ለኑሮ እንደ ባለሥልጣን እና እንደ መመሪያ አድርጋ የወሰደችው።
1
ሀ. 2 ጴጥ. 1.19-21
ለ. ሰዎች ራሱ መንፈስ ቅዱስ እንደነዳቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ተናግረዋል።
ለ. ቅዱሳት መጻሕፍት (መጽሐፍ ቅዱስ) በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ በመሆኑ ከእርሱ ከወጣ እንዲሁ በከንቱ ወደ እርሱ አይመለስም። በሁሉም መንገድ፣ የእግዚአብሔር ቃል ፍፁም ታማኝ እና ፍፁም ስልጣን ያለው፤ ልንታመነውና ልናጠናው የሚገባ ሆኖ ይታያል።
1. ኢሳ. 55.8-11
ሀ. የእግዚአብሔር መንገድ ከመንገዳችን እጅግ የራቀ ነው፣ ይህም ማለት ፍፁም ከፍለጋችን ወይም ግኝታችን በላይ ነው።
ለ. የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር እንዲሰራ በፈለገውና በሾመው ነገር ሁሉ ላይ ይሰራል።
Made with FlippingBook Annual report maker