Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
4 4 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ፍትሃዊ አይደለም! በቅርቡ ስለ መጨረሻው ዘመን እና ዳግም ምጽአት የሚያጠና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ከመጨረሻው ዘመን ጋር የተያያዙትን የተለያዩ ፍርዶች ማጥናት ጀመረ። በቡድኑ ውስጥ ካሉት እህቶች አንዷ ጥናቱ ብዙ ውስጣዊ ውጥረት እና ውዥንብር ፈጥሮባታል፣ በተለይም በአንድ ነጥብ ላይ - ስለ ክርስቶስ ሰምተው በማያውቁት ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል በሚለው ሃሳብ ላይ። በአእምሮዋ፣ ስለ ኢየሱስና ስለ ፍቅሩ ለመስማት ዕድል ባላገኙ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ላይ ይፈርዳል የሚለው ሐሳብ ተቀባይነት የለውም። “እግዚአብሔር ይህን ማድረግ የለበትም - ማንም ስለ ጌታ ስላልነገራቸው ብቻ በእግዚአብሔር ተፈርዶባቸው ወደ ገሃነም ይገባሉ። ይህ ደግሞ እነርሱ ምንም ባላጠፉት እግዚአብሔርን ስላለማወቃቸው መውቀስ ተገቢ አይሆንም።” በጥናቱ ውስጥ ላሉት ሌሎች ደግሞ ጉዳዩ የእግዚአብሔር ፍትሃዊነት ሳይሆን የእግዚአብሔር ቅድስና ነው። እግዚአብሔር ባስቀመጠው መስፈርት (ማለትም በክርስቶስ ማመን) ሁሉንም ካልፈረደ የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል ብሎ ተናግሯልና የራሱን ጽኑ አቋም እንደሚያፈርስ ይከራከራሉ (ሮሜ 10፡9-10)። በግልጽ መወያየታቸውን ቢቀጥሉም ጉዳዩን ለመፍታት ግን አልቻሉም። ምን ማድረግ አለባቸው?
3
2
የሚወቅሰው ቃል ክፍል 1
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
በዚህ ክፍል፣ የእግዚአብሔር ቃል የመንፈስ ቅዱስ መሣሪያ ሆኖ ዓለምን ስለ ኃጢአት፣ ጽድቅ እና ፍርድ እንዴት እንደሚወቅስ እንመረምራለን። ኃጢአትን በተመለከተ የእግዚአብሔር ቃል ለእግዚአብሔር ህግ አለመታዘዛችንን እና ህይወታችንን ከቅዱስ ባህሪው እና ፍላጎቶች ጋር ባለማስተካከላችን ይወቅሰናል። ጽድቅን በተመለከተ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወሰን በሌለው የእግዚአብሔር ጽድቅ እና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት በሌለው የኛ ጽድቅ መካከል ያለውን ርቀት ያሳየናል። በመጨረሻም የእግዚአብሔር ቃል ፍርድን በተመለከተ የሚሰጠውን ትምህርት እንመለከታለን፣ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ከጽድቅ ፍላጎቶቹ እና ለእርሱ ካላቸው መታዘዝ አንጻር ተጠያቂ ለማድረግ ያለውን ሃሳብ እንማራለን። የዚህ የቃሉ የመጀመሪያ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታዩ ለማስቻል ነው፡- • የእግዚአብሔር ቃል ኃጢአትን፣ ጽድቅን እና ፍርድን የሚወቅስ ቃል ነው። • የእግዚአብሔርን አካልና ሥራ ከምንረዳባቸው መንገዶች ሁሉ ኃጢአትን እንድንረዳ የሚያስችለን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው። • የእግዚአብሔር ህግ በኃጢአታችን ይወቅሰናል፣ ይህም በድርጊታችንና በሃሳባችን እና በእግዚአብሔር የቅድስና ፍላጎት መካከል ያለውን ርቀት ያሳያል።
የክፍል 1 ማጠቃለያ
Made with FlippingBook Annual report maker