Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 4 5
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
• የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጽድቅ ይወቅሳል፣ የእግዚአብሔርን ህግ ለመጠበቅ ብቃት እንደሌለን ያሳያል፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፅድቅ በእምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ይገልጥልናል። • የእግዚአብሔር ቃል ፍርድን በሚመለከት ይወቅሳል፣ በሁሉም ቦታ ያሉ ፍጥረታትን ሁሉ ተጠያቂ ለማድረግ ያለውን ሃሳብ እና በእስራኤል እና በህዝቦች፣ በቤተክርስቲያን፣ በሰይጣን እና በመላእክቱ እና በክፉ ሙታን ሁሉ ላይ ሊመጣ ያለውን ፍርድ ያሳያል።
11.1
የቪዲዮ ክፍል 1 መግለጫ
I. መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት የዓለምን ኃጢአት ይኮንናል።
2
ገጽ 169
7
ሀ. ኃጢአት ዓለም አቀፋዊ እና በባሕሪውም በካይ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተምሩናል።
1. ኃጢአት ሁሉን አቀፍ ነው።
ዮሐንስ 16: 7 - 11 “እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤ ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤ ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።”
ሀ. ሮሜ 3፡23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል፥ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል ይላል።
ለ. ኃጢአት በእግዚአብሔር ላይ ነው፤ ኃጢአት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ማመጽ ነው። (1) መዝ. 51.4
(2) ሉቃስ 15፡18
2. ኃጢአት ከእግዚአብሔር ባህሪ እና ዓላማ ጋር የሚቃረን እና የማይስማማ ማንኛውም ነገር ነው።
ሀ. ሁሉንም ሰው የሚነካ እና ሁሉንም የሰው ልጅ እኩል የሚያበላሽ ነው።
ለ. ኃጢአት ሁሉን አቀፍ ሲሆን ሁሉንም ፍፁም የሚበክል ባሕርይ አለው ሮሜ. 3.9-12.
Made with FlippingBook Annual report maker