Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 5
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ
ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን፥
የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን በእግዚአብሔር ቃል የመፍጠር፣ የመውቀስ፣ የመለወጥ እና የመጥራት ሃይል ላይ ጥልቅ እምነት አለን። አስደናቂውን የለውጥ እና ጥሪን በረከት ለመረዳት፣ የእግዚአብሔር ቃል በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ቦታ በጥልቀት መገምገም ያስፈልገናል። የሚፈጥረው ቃል የተሰኘው የመጀመርያው ትምህርታችን እንደ እግዚአብሔር ቃል የቅዱሳት መጻሕፍትን ተፈጥሮ ይዳስሳል። የእግዚአብሔር ፍጹም ታማኝነት የቅዱሳት መጻሕፍትን ፍጹም ታማኝነት እንደሚያረጋግጥ እንመለከታለን። በተጨማሪም እግዚአብሔር አጽናፈ ሰማይን በቃሉ እንዴት እንደፈጠረ እና እራሱን በኢየሱስ ክርስቶስ ከቃሉ ጋር እንዴት እንደሚለይ እንገነዘባለን። መንፈስ ቅዱስ በሚያምኑት ውስጥ አዲስ ሕይወት የሚፈጥርበት መንገድ በመሆናችን፣ በኢየሱስ ቃል ውስጥ በመኖር ደቀ መዛሙርት መሆናችንን እናረጋግጣለን። የቤተክርስቲያን አባላት እንደመሆናችንም መጠን ቃሉን እንደ አንድ ማህበረሰብ እንቀበላለን፣ ይህም የፍጥረትን ሁሉ የመጨረሻ አላማ ይሰጠናል፣ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ክብር ነው። በሚቀጥለው የሚወቅሰው ቃል በተሰኘው ትምህርት የእግዚአብሔር ቃል ኃጢአትን፣ ጽድቅን እና ፍርድን እንዴት እንደሚወቅስ እንመለከታለን። ቃሉ ኃጢአት በይዘቱ ዓለም አቀፋዊ እና በተፈጥሮው ብልሹ መሆኑን ያስተምራል። የእግዚአብሔር ቃል ጽድቅን በተመለከተም የእግዚአብሔርን ፍጹም ጽድቅና የእኛን ያለመብቃት በማሳየት ያስረዳናል፤ እግዚአብሔር በእስራኤል እና በአሕዛብ፣ በቤተ ክርስቲያን፣ በሰይጣን እና በመላእክቱ እና በክፉዎች ሙታን ሁሉ ላይ በፍትሃዊ ውሳኔው እንደሚፈርድ በማስተማር ፍርድን በተመለከተ ያስረዳል። የእግዚአብሔር ቃል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እና ስለቃሉ ታማኝነት በመልእክተኞቹ፣ በነቢያት እና በሐዋርያት በኩል ስለ እውነት ይናገረናል። የሚለወጠው ቃል የተሰኘው ትምህርት ሦስት ደግሞ የሚያተኩረው የእግዚአብሔር ቃል በአማኙ ውስጥ አዲስ ሕይወት ለመፍጠር ባለው ኃይል ላይ ነው። ይህ የሚለውጠው ቃል ከኢየሱስ ወንጌል ጋር ተመሳሳይ ነው፤ እንደገና እንድንወለድ፣ የመታደስ መታጠብ እና የመንፈስ ቅዱስ ተሃድሶ እንድንለማመድ የሚያደርገን የድኅነት ወንጌል ነው። የእግዚአብሔርን የመታደስ ኃይል የሚያሳዩ ተጨባጭ ምልክቶችን በምናምን ውስጥ ቃሉ ያፈራል። አዲስ ሕይወትን የሚፈጥር፣ የሚደግፈን፣ መንፈሳዊ ምግብን የሚመግበን፣ የሚያሳድገን እና ከዲያብሎስ ሽንገላም ራሳችንን እንድንከላከል የሚረዳን ይኸው ቃል ነው። በመጨረሻም የሚጠራው ቃል የተሰኘው ትምህርት አራት (ሜታኖያ)፣ ማለትም ወደ እግዚአብሔር ንስሐ መግባት እና እምነት (ፒስቲስ) የተሰኙ ጽንሰ-ሀሳቦችን ይዳስሳል። በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን እግዚአብሔር አማኙን ከኃጢያት ቅጣት፣ ኃይል እና ህልውና የሚያድንበት መንገድ ነው። በክርስቶስ ከኃጢአት ወደ እግዚአብሔር ስንመለስ፣ ቃሉ የእግዚአብሔርን አዲስ ተፈጥሮ (ዳግም መወለድ) እንድንቀበል እና ወደ እግዚአብሔር ሰዎች (ወደ እግዚአብሔር ላኦስ) በጸጋ በእምነት ብቻ እንድንዋሃድ ያደርገናል። ወደ መዳን የሚጠራን ቃል ደግሞ ወደ ደቀመዝሙርነት (እንደ ኢየሱስ
Made with FlippingBook Annual report maker