Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
5 0 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
3. እግዚአብሔር በሰይጣንና በወደቁት መላእክት ላይ ይፈርዳል፣ ራዕ 20፡10.
4. እግዚአብሔር በክፉዎች ሙታን ላይ ይፈርዳል፣ ራዕ. 20፡11-15።
ማጠቃለያ
» የእግዚአብሔር ቃል፣ የመንፈስ ቅዱስ መሣሪያ ሆኖ፣ ዓለምን ስለ ኃጢአት፣ ጽድቅ እና ፍርድ ይወቅሳል። » ኃጢአትን በተመለከተ፣ የእግዚአብሔር ቃል ለእግዚአብሔር ህግ አለመታዘዛችንን እና ህይወታችንን ከቅዱስ ባህሪው እና ፍላጎቶች ጋር ባለማስተካከል ይወቅሰናል። » ጽድቅን በተመለከተ፣ የእግዚአብሔር ቃል በጌታ ጽድቅ እና በእኛ ጽድቅ መካከል ያለውን ርቀት በመግለጥ ወሰን የሌለው ጻድቅ አምላክ እንደሆነ እና የእኛ ጽድቅ በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ያሳያል። እባክህ በነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ስለ እግዚአብሔር ቃል ኃጢአትን፣ ጽድቅን እና ፍርድን የመኮነን አቅም አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ መልሶችህን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አስደግፍ፡፡ 1. በመንፈስ ቅዱስ እና በቅዱሳት መጻሕፍት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዴት መረዳት አለብን? የመንፈስ አገልግሎት በራሱ በእግዚአብሔር እስትንፋስ አማካኝነት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ይሰራል መባሉስ ትክክል ነው? 2. ቅዱሳት መጻሕፍት ዓለምን ስለ ኃጢአት የሚኮንኑት በምን አይነት መልኩ ነው? በብሉይ ኪዳን ውስጥ ኃጢአትን እንደ ጽንሰ-ሐሳብ እንዴት እንረዳዋለን? አዲስ ኪዳን ስለዚህ ተመሳሳይ ጽንሰ-ሐሳብ ምን ይላል? 3. በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተገለጹትን አራት የጽድቅ ገጽታዎች ግለጽ? የእግዚአብሔር ቃል ዓለምን በጽድቅ ስለመኮነኑ ስንነጋገር እነዚህን የተለያዩ ገጽታዎች መረዳት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 4. በእግዚአብሔር በራሱ የተሰጠን የእግዚአብሔር ጽድቅ የእኛ የሚሆነው በምን መንገድ ነው? 5. የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር በሰው ልጆች ላይ ስለሚኖረው ፍርድ ያለውን ሐሳብ የሚገልጸው እንዴት ነው? እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት አባባል እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ላይ የሚፈርደው በምን መሠረት ነው?
2
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎችና ምላሽ
ገጽ 170
10
Made with FlippingBook Annual report maker