Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

/ 5 1

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

6. እግዚአብሔር በመጨረሻ ለፍርድ ለማቅረብ ያሰበውን አንዳንድ ቡድኖችን እና አካላትን ዘርዝር? በዓለም ሁሉ ላይ ያለውን የፍርድ ሐሳብ በተመለከተ ከቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት ስለ እግዚአብሔር ምን እንማራለን? 7. የእግዚአብሔር ቃል የፍርዱን ዓለም የሚኮንነው እንዴት ነው? በዓለም ላይ ባለው የእግዚአብሔር ፍርድ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?

የሚወቅሰው ቃል ክፍል 2

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

2

በዚህ ክፍል ውስጥ የእውነትን ተፈጥሮ በተመለከተ የእግዚአብሔርን ቃል የመኮነን አቅም እናገኛለን ስለዚህም ህይወታችንን እና አመለካከታችንን በመንፈስ ቅዱስ የመቀየር ችሎታውን እንማራለን። የእግዚአብሔር ቃል ክርስቶስን ያማከለ የእግዚአብሔርን መገለጥ ተፈጥሮ፣ የመንግሥቱን ታሪክ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር አጠቃላይ አስተምህሮ ዳራ እና መጽሐፍ ቅዱስ በነቢያት እና በሐዋርያት አማካኝነት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስላለው ግንኙነት ይገልፃል። የእነርሱ ምስክርነት ለእምነት እና ለኑሮ ለቅዱሳት መጻሕፍት የመጨረሻ ስልጣን ይሰጣል፤ በፍርድ እና በእውነት ጉዳዮች ላይ ፍጹም አስተማማኝ ነው። የዚህ “የሚወቅሰው ቃል” የተሰኘ ሁለተኛ ክፍል ውስጥ አላማችን የሚከተለውን እውነት እንድትረዳ እና ለሌሎች እንድትናገር ለማስቻል ነው፡- • የእግዚአብሔር ቃል ስለ እውነት ይወቅሰናል። የእግዚአብሔር ቃል በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ውሸት ከማያውቀው ከእውነት አምላክ ጋር የተያያዘ ነው። ስለዚህም የማይሻር የእግዚአብሔር ምስክር እና የእውነት መዝገብ ነው። የእውነትን ተፈጥሮ፥ ማለትም ስለ እግዚአብሔር፣ በዓለም ላይ ስላለው ሥራ፣ እና የሰው ልጅ እጣ ፈንታ እና ዓላማን በተመለከተ እውነት የሆነውን ነገር በተመለከተ እምነትን ይሰጣል። • የእግዚአብሔር ቃል የቅዱሳት መጻሕፍት ዋና ርዕሰ ጉዳይ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ሥራ መገለጥ ጥልቅ እምነትን ይሰጣል። • የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን መገለጥ አጠቃላይ ዳራ ማለትም የመንግስቱን እቅድ መገለጥ በተመለከተ እምነትን ይሰጣል። • እግዚአብሔር ቃሉን መስርቷል። የእግዚአብሔርን ማንነት እና እቅድ የመወከል እና የመናገር ሃላፊነት በተሰጣቸው በእግዚአብሔር በተመረጡት መልእክተኞች፣ ነቢያት እና ሐዋርያት ታማኝነት አማካኝነት እምነትን ይሰጣል።

የክፍል 2 ማጠቃለያ

Made with FlippingBook Annual report maker