Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

5 8 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ማጠቃለያ

የእግዚአብሔር ቃል ስለ እውነት ይወቅሰናል።

»

» የእግዚአብሔር ቃል የእውነትን ተፈጥሮን በተመለከተ የመውቀስ ችሎታ እና ስለዚህ ህይወታችንን እና አመለካከታችንን በመንፈስ ቅዱስ የመቀየር ችሎታውን አለው። » የናዝሬቱ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መገለጥ ዋና ጭብጥ ነው፥ ስለዚህ የመንግስቱ ታሪክ መልእክቱ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የማስተማር ዳራ ሆኖ ያገለግላል። » የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሱስ ጋር ባለው ግንኙነት፣ እንዲሁም በመንፈስ አነሳሽነት ከተጻፉት ነቢያትና ሐዋርያት ጋር በመገናኘቱ ከሁሉ የላቀ ታማኝነት አለው።

የሚከተሉት ጥያቄዎች የተነደፉት በሁለተኛው የቪዲዮ ክፍል ውስጥ ያለውን ይዘት ለመገምገም ነው። የተነደፉትም የኢየሱስ ክርስቶስን እውነት፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት እና የእምነትን ትንቢታዊ እና ሐዋርያዊ ምሥክርነት ታማኝነት በተመለከተ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የተያያዙትን ወሳኝ ሐሳቦች እንድትገመግም ነው። እባክህ መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. በዮሐንስ 17 ላይ የኢየሱስ ሊቀ ካህናዊ ጸሎት እውነትን እንረዳ ዘንድ ከማገዝ አንጻር የእግዚአብሔርን ቃል ምንነት እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው? 2. የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ጭብጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንደሆነ የሚጠቁም ምን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለን? 3. ኢየሱስ በተጨባጭ መልኩ የብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ሥርዓት ፍጻሜ መሆኑን በምን ልዩ መንገድ እናውቃለን? 4. የኢየሱስ ማንነት እግዚአብሔር አብ በብሉይ ውስጥ ከተገለጠበት መገለጥ ጋር እንዴት ይዛመዳል? አብን ለእኛ በመግለጥ (በማሳወቅ) ረገድ ያለው ልዩ ሚና ምንድን ነው? 5. እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባው የቃል ኪዳኑ ታማኝነት ታሪክ እግዚአብሔር በዓለም ውስጥ ስላለው ሥራ እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው? 6. በሦስት ወገን በሆኑት የመልእክተኞች ቡድን (ማለትም፣ ነቢያት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና ሐዋርያት) በኩል የመጣው የእግዚአብሔር መገለጥ ቅዱሳት መጻሕፍት እውነት መሆናቸውን፤ ማለትም እግዚአብሔር በአለም ላይ ስላደረጋቸው ነገሮች አስተማማኝ እና ትክክለኛ ምስክሮች መሆናቸውን እንድናምን የሚረዳን እንዴት ነው?

መሸጋገሪያ 2

2

የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች

ገጽ 171

14

Made with FlippingBook Annual report maker