Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 5 9
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ግንኙነት
ይህ ትምህርት የእግዚአብሔር ቃል ጽኑ እምነትን በተለያዩ ደረጃዎች ለመፍጠር በሚያስችልበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነው፣ እነዚህ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ጥልቅና የጠበቀ ግንኙነት ይመራናል። የእግዚአብሔር ቃል ስለ ኃጢአት፣ ጽድቅ፣ ፍርድ እና እውነት ይወቅሰናል። የእግዚአብሔር ቃል መንፈስ ቅዱስ በኃጢአት፣ በጽድቅ እና በፍርድ ዓለምን ለመውቀስ የሚጠቀምበት መሣሪያ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት ኃጢአት ከእግዚአብሔር ፍጹም ባሕርይ፣ ሕግ እና ፈቃድ ጋር የሚጣረስ ማንኛውም ነገር ነው። ኃጢአት እና ውጤቶቹ የሰው ልጆችን ሁሉ ይነካሉ፣ በሥፋቱ ሁለንተናዊ እና በባህሪውም በካይ ነው። የእግዚአብሔር የሥነ ምግባር ሕግ የእግዚአብሔር ቃል አንዱ ጉልህ ክፍል እንደመሆኑ መጠን በኃጢአታችን ይወቅሰናል፣ ይህም በእኛ ድርጊት እና እግዚአብሔር በሚጠብቅብን የሞራል ኃላፊነት መካከል ያለውን ርቀት ያሳያል። የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጽድቅ ይወቅሳል። የእግዚአብሔርን ህግ ለመጠበቅ ብቁ አለመሆናችንን እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ በማመን የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ ያሳያል። የእግዚአብሔር ቃል በሰው ልጆች ሁሉ ላይ፥ በሕያዋንም ሆነ በሙታን ላይ እንደ ሥራቸው ይፈርድባቸዋል። በዘመኑ ፍጻሜ፣ እግዚአብሔር በእስራኤልና በአሕዛብ፣ በቤተ ክርስቲያን፣ በሰይጣንና በመላእክቱ እንዲሁም በክፉዎች ሙታን ሁሉ ላይ ይፈርዳል። በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር አካል ጋር ካለው ቁርኝት የተነሳ የእግዚአብሔር ቃል የእውነትን ተፈጥሮ፣ ማለትም፣ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ስላለው ስራ እና የሰው ልጅ እጣ ፈንታን በተመለከተ እውነተኛውን እምነትን ይሰጣል። ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የቅዱሳት መጻሕፍት ዋና ርዕሰ ጉዳይ፣ የብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ሥርዓት ፍጻሜ እና የማይታየው የእግዚአብሔር ሦስትነት ክብር ብቸኛ ገላጭ ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት እቅድ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባው ቃል ኪዳን ባሳየው ታማኝነት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት ፍጻሜው ተገልጧል። የእግዚአብሔር ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አንድን ህዝብ ከምድር አህዛብ ሁሉ ለማዳን ያለው አላማ እውነት መሆኑን ያስረዳናል። የእግዚአብሔር ቃል ታማኝነት የእግዚአብሔርን አካል እና እቅድ የመወከል እና የመናገር ተግባር በተሰጣቸው በእግዚአብሔር በተመረጡት መልእክተኞች፣ ነቢያት እና ሐዋርያት ታማኝነት ይደገፋል።
የቁልፍ ፅንሰ-ሀሳቦች ማጠቃለያ
ገጽ 171
15
2
Made with FlippingBook Annual report maker