Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
6 0 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ስለ እግዚአብሔር ቃል እና ኃጢአትን፣ ጽድቅን፣ ፍርድን እና እውነትን የመኮነን ችሎታን በተመለከተ ከተማሪዎችህ ጋር የምትወያይበት ጊዜ አሁን ነው። በአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ማገልገል ይህን ቃል መያዝን ይጠይቃል፤ ይህም ቃል ወደ ውስጥ ዘልቆ የሚገባ እና በሚሰሙት ሰዎች ልብ ውስጥ ንጽህናውን እና እውነተኝነቱን ያሳምናል። የቃሉን የመኮነን ሃይል በማሰብ፣ አሁን ካጠናኸው ነገር አንጻር ምን አይነት ልዩ ጥያቄዎች አሉህ? ምናልባት ከዚህ በታች ያሉት አንዳንድ ጥያቄዎች የራስህን ልዩና ወሳኝ ጥያቄዎችን እንድትፈጥር ሊረዱህ ይችላሉ። * የእግዚአብሔርን ቃል ሌሎችን ስለ ኃጢአት፣ ጽድቅ፣ ፍርድ እና እውነት እንዲወቅስ መምህሩ ወይም ሰባኪው ማመን አለባቸው? መልስህን አስረዳ። * የእግዚአብሔር ቃል አማኙን የሚወቅሰው የማያምነውን በሚወቅስበት ተመሳሳይ ደረጃ ነውን? እንዴት ሆኖ? ምሳሌዎችን ጥቀስ። * መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ስለ ኃጢአት፣ ጽድቅ እና ፍርድ ይወቅሳል? ለምን? * የእግዚአብሔር ቃል የሚቀርብበት ወይም የሚሰበክበት የአቀራረብ ዘዴ የማሳመን ኃይሉ ላይ የሚፈጥረው ትጽዕኖ ይኖራል? * ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የቅዱሳት መጻሕፍት ዋና ጭብጥና ርዕሰ ጉዳይ መሆኑን ሌሎች ሰዎች እንዲገነዘቡ ምን አይነት ተግባራዊ ነገሮችን ማድረግ እንችላለን? አንድ ነገር በመንፈሳዊ አገላለጽ አሳማኝ ሆኖ በሆነ መንገድ ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የማይገናኝ ሊሆን ይችላል? መልስህን አስረዳ። * ቅዱሳት መጻሕፍት በክርስቶስ በኩል የእግዚአብሔር ሥራ እውነተኛና አስተማማኝ ምስክሮች መሆናቸውን ለማረጋገጥ በሐዋርያትና በነቢያት ታማኝነት ማመን ለምን አስፈለገ? * በከተማ ውስጥ የጠፉትን እንደሚያገለግል አንድ አገልጋይ ቅዱሳት መጻሕፍት ሌሎችን ለመውቀስ ያላቸውን ችሎታ መረዳት በጣም አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው? ክርስትና ከሁሉም ሃይማኖቶች ልዩ ነው? በማህበረሰቡ ውስጥ ላለው የመድብለ-ባህላዊ እድገት እና የሃይማኖቶች ትብብር ክብር ሲባል መጥተህ ስለ “ብዝሃዊ ማህበረሰብ ውስጥ ስላለው ሃይማኖታዊ እውነታ ተፈጥሮ” ያለህን አስተያየት እንድታካፍል ተጋብዘሃል። በሌላ አነጋገር፣ ብዙ ዓይነት ሃይማኖቶች በሚተገበሩበትና በሚታመኑበት ማኅበረሰብ ውስጥ እንደ ክርስቲያን አማኝ “እውነትን መፈለግና መናገር” ሲባል ምን ማለት ነው? አንዳንድ ወዳጆችህ ሂድና በቀላሉ ሁሉም ሌሎች ሃይማኖቶች ውሸት ናቸው፥ ክርስትና ብቻ እውነት ነው፣ ኢየሱስ ጌታ ነው፣ በቃ ይኸው ነው ብለህ ተናገር ይላሉ። እንግዲህ የቅዱሳት መጻሕፍትን እምነት በተለይም ክርስትና ስለእግዚአብሔር እንናገራለን በሚሉት ሁሉ መካከል ኢየሱስ ልዩ ቦታ እንዳለው ስለሚናገረው ነገር ለማካፈል እንዴት ትሄዳለህ?
የተማሪ ተባራዊ አርምጃ እና አንድምታ
ገጽ 171
16
2
ጥናቶች
1
ገጽ 172 17
Made with FlippingBook Annual report maker