Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

/ 6 1

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ከኃጢአት የመጣ የትኛውም ነገር? በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ወጣቶች አንዷ ስለ “ኃጢአት” ርዕሰ ጉዳይ ልታናግርህ ጠየቀች። ለክልሉ የማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኛ እንደመሆኗ የራሷ የግል ሃይማኖታዊ አመለካከት ለደንበኞቿ” የምትሰጠውን የምክር እና መረጃን የማቅረብ ስራዋን እንዳያስተጓጉል በተደጋጋሚ ተነግሯታል፤ አብዛኛዎቹ ከፕሮጀክቶቹ የመጡ እና ክርስቶስን ማወቅ በጣም የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ከእነዚህ እገዳዎች ዋና ምክንያቶች አንዱ የበላይ ኃላፊዋ የ “ኃጢአት”ን ጽንሰ ሀሳብ ሙሉ በሙሉ አለመቀበሉ ነው። የበላይ ሃላፊው ሲከራከር ኃጢአትን ለመከላከል ሲባል አንዳንድ ሃይማኖታዊ ቡድኖች የራሳቸውን ጠባብ ሥነ ምግባራዊ አመለካከት በሌሎቻችን ላይ ለመጫን ያመጡት ብቻ እንደሆነ ይናገራል። ማንም ሰው ይህ ነገር ኃጢአት ነው ብሎ ሊናገር አይችልም ምክንያቱም “ኃጢአት” ማለት በሃይማኖት ቡድን ውስጥ ያለ ነገር ብቻ ነው ብሎ ይሟገታል። እዚህ ላይ ስለ “ኃጢአት” ጽንሰ ሀሳብ ይህን ወጣት የማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኛ ምን ትመክረዋለህ? የማን ጽድቅ ነው የሚበልጠው ጽድቅ? ከቤተክርስቲያናችሁ አባላት አንዱ ከይሖዋ ምሥክር ጋር ረዘም እና ሞቅ ያለ ውይይት ካደረገ በኋላ ቤተክርስቲያንን አስመልክቶ በተነሱት ክርክሮች በአንዱ ተሰናክሎ አገኘኸው እንበል። የይሖዋ ምሥክርን የሕይወት ጥራት ደረጃ ከአማካይ የቤተ ክርስቲያን ሂያጆች ጋር በማነፃፀር እንዲህ የሚል ሐሳብ ቀርቧል “በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ስለ ጽድቅ የሚነገር ቢሆንም በአብዛኛው የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ። ለነገሩ ሙዚቀኞቹ በፆታዊ ግንኙነት በሚዋኙበት፣ አንደኛው ዲያቆን በስብሰባ መሃል መጋቢውን በሚሳደብበትና የወጣት አገልግሎት መሪው ደግሞ ከባለቤቱ ጋር ተለያይቶ በነበረበት ቤተክርስቲያን እገኝ ነበር። ማንም ስለእነዚህ ሁኔታዎች ምንም አልተናገረም። የይሖዋ ምሥክር ስለነበርኩ እኛ እራሳችን በጽድቅ እንኖራለን እንጂ ማንንም ሰው በዓመጻው አንታገሥም። እንግዲህ የቤተክርስቲያናችሁ አባል እንደዚህ አይነት ሁኔታዎችን ያውቅ ስለነበር በክርክሩ ወደ መረታት መጥቷል። ስለዚህ ወደፊትስ እንዲህ ያሉ ክርክሮችን እንዴት እንዲመልስ ትመክረዋለህ? ዋናውን ነገር ዋና ማድረግ አንተ በቅርቡ የቤተክርስቲያንህ የሰንበት ትምህርት ቤት የበላይ ሃላፊ ሆነህ ተሹመሃል ብለን እናስብ፤ ስለዚህም ለምትሰጧቸው የተለያዩ የዕድሜ ደረጃዎች መምህራንን በመምረጥ ላይ ነህ። ያለፈውን አንድ ዓመት ተኩል ትምህርት ወደኋላ መለስ ብለህ ስትመለከት ትምህርቶቹ የሚያተኩሩበት አንድም ወጥ የሆነ ርዕሰ ጉዳይ እንደሌለ ደርሰህበታል። ሁሉም ዓይነት ርዕሰ ጉዳዮች በተለያዩ የዕድሜ ደረጃዎች ቢዳሰሱም አንዳቸውም ጥልቅ በሆኑ ሥነ-መለኮታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለማተኮር ብዙም ፍላጎት ያላቸው አይመስሉም። አብዛኛዎቹ አስተማሪዎች እንደ “ገንዘብዎን ማስተዳደር” ወይም “በእግዚአብሔር ፊት ንፁህ መሆን” ወይም “የተሻለ የጸሎት ሕይወት ማግኘት” ያሉ ርዕሶችን ይመርጣሉ። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ ሥራው የሚያስተምሩት ትምህርት በጣም ጥቂት መሆኑ አሳስቦሃል፥ በመሆኑም እንዴት ይህን ማድረግ እንዳለብህ ከአስተማሪዎች ጋር ስብሰባ ማድረግ ትፈልጋለህ። በሌሎቹ ርእሶች እና አቀራረቦች ላይ የጥፋተኝነት ስሜት ሳይፈጠርባቸው ይህን ጉዳይ ከመምህራኖቻችሁ ጋር እንዴት ልትወያዩ ትችላላችሁ?

2

2

3

4

Made with FlippingBook Annual report maker