Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

6 2 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

የእግዚአብሔር ቃል ስለ ኃጢአት፣ ጽድቅ፣ ፍርድ እና እውነት ይወቅሳል። ኃጢአትን በተመለከተ፣ ቃሉ የሚያስተምረው ኃጢአት በሥፋቱና በባህሪው የሰውን ልጅ የሚያበላሽ ሁለንተናዊ እንደሆነ ነው። ጽድቅን በተመለከተ፣ የእግዚአብሔር ቃል ስለ እግዚአብሔር ፍጹም ጽድቅ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ጽድቅ ለአማኞች የሰጠውን የጸጋ ስጦታ ይመሰክራል። ፍርድን በተመለከተ እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ላይ እንደ ሥራው ይፈርዳል። የመጨረሻው ፍርድ ሁሉን አቀፍ ይሆናል፣ እስራኤል እና አህዛብ ቤተ ክርስቲያን፣ ሰይጣን እና መላእክቱ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከማያምኑት ከሞቱት ጋር። በመጨረሻም፣ የእግዚአብሔር ቃል እውነትን በተመለከተ ይወቅሰናል። ኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱሳት መጻሕፍት ዋና ርዕሰ ጉዳይ ነው፣ በአብርሃም በኩል ያለው የእግዚአብሔር መንግሥት እቅድ የእግዚአብሔር ሥራ ዳራ ሆኖ ያገለግላል። የቃሉ እውነተኝነት በነቢያት፣ በሐዋርያት እና በኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ላይ የተመሰረተ ነው፣ ይህም መጽሐፍ ቅዱሳችንን በሁሉም የእምነት እና የተግባር ጉዳዮች ፍጹም አስተማማኝ ያደርገዋል። ስለ “ወደ እውነት የሚመራው ቃል” ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል: Pinnock, Clark H. Biblical Revelation: Foundation of Christian Theology. Chicago: Moody Press, 1971. ይህ የትምህርቱን ግንዛቤዎች ከትክክለኛው የተግባር አገልግሎትህ ሁኔታ ጋር ልዩ እና ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ለመዳሰስ እድሉን የምታገኝበት አጋጣሚ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ወደ እውነት የመምራት ኃይል በሁሉም የሕይወታችን አቅጣጫ ተፈጻሚ ነው፤ በተለይም በቤተክርስቲያን ውስጥ በምንሰራው ሥራ ወይም ቤተ ክርስቲያንን በመወከል በምንሰጠው አገልግሎት ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ጉልህ ነው። ለመጀመር ያህል ስለ ራስህ ሕይወትስ ምን ማለት ይቻላል - የእግዚአብሔር ቃል ስለ እውነት እየወቀሰህ ነው? በህይወትህ ውስጥ የእግዚአብሔር እውነት የበለጠ እና ግልጽ የሆነ ቦታ የሚፈልግበት ስፍራ አለ? የእግዚአብሔርን ቃል የበለጠ እየተረዳህ ነው? በአንተስ ውስጥ ተገቢውን አይነት አመለካከት እየፈጠረ ነው? ስለምታገለግላቸው ሰዎችስ ምን ማለት ይቻላል - እለት እለት የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት ይበልጥ እያገኙ ነው? ለእነርሱስ የጌታን ጸጋ መፈለግ አለብህ? - በአንዳንድ የሕይወታቸው ክፍል የእውነት ቃል ያስፈልጋቸዋል? በተለይ መንፈስ ቅዱስ ለአንተ፣ ለቤተሰብህ፣ ለቤተ ክርስትያንህ፣ ለአገልግሎትህ በተለይም ስለ “የሚወቅሰው ቃል” ምን ይልሃል? በሕይወትህ ውስጥ ስላለው የቅዱሳት መጻሕፍት የመውቀስ ኃይል በእግዚአብሔር ላይ እንዴት መታመን እንደምትችል ስታስብ ምን ልዩ ሁኔታ ወደ አእምሮህ ይመጣል? Smart, J. D. The Interpretation of Scripture. London: SCM press, 1961. Young, E. J. Thy Word is Truth. London: Banner of Truth, 1963.

የትምህርቱ ንድፈሃሳብ በድጋሚ መጻፍ

ምንጮች እና ማጣቀሻዎች

2

የአገልግሎት ግንኙነቶች

ገጽ 172

18

Made with FlippingBook Annual report maker