Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
/ 8 1
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
2. መንፈስ ቅዱስ ጥልቅ በሆነ መንፈሳዊ መንገድ የክርስቲያኑን የጸሎት ህይወት ያጠናክራል፣ ሮሜ. 8፡26-27።
3. እኛ የዳንን በልባችን ወደ አባታችንና አምላካችን “አባ አባት!” (አረማይክ፣ “ፓፓ!”) ብለን እንጮሃለን፣ ሮሜ. 8.15.
ሐ. ሌላው የውስጥ የመለወጥ ምልክት ለእግዚአብሔር ቃል ያለው ፍላጎት እና ረሃብ ነው።
1. እውነተኛ አማኞች አሁን እንደተወለዱ ሕፃናት የጥንካሬያቸውና የተመጣጠነ ምግብ ምንጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ንጹሕ ወተት ይመኛሉ፣ 1ጴጥ. 2፥2.
2. የመንፈስ ቅዱስ የማስተማር አገልግሎት አዲስ የመለየት/የመገለጥ ልምምድን፣ ቃሉን መራብን እና ለእግዚአብሔር ቃል መሰጠትን ይፈጥራል።
3
ሀ. 1 ቆሮ. 2.15
ለ. 1ኛ የዮሐንስ 2፡27
ሐ. ዮሐንስ 16፡12-15
3. የእግዚአብሔርን ቃል በመመገብ አማኙ የክርስቶስን እውቀት ይጨምራል፣ 2ጢሞ. 1.12.
መ. የመጨረሻው ውስጣዊ የመለወጥ ምልክት ኢየሱስ ክርስቶስን ከመስማት እና እርሱን ከመከተል ጋር ይዛመዳል። አዲስ አማኞች የአዳኙን ድምጽ ይለያሉ፥ ይከተሉትማል።
1. የሚያውቁት ቃሉን ይሰማሉ፥ እንግዳ ድምጾችንም አይከተሉም ዮሐ 10፡1-6።
Made with FlippingBook Annual report maker