Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

/ 8 5

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ማጠቃለያ

» የሚለውጠው ቃል በእውነተኛ አማኝ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ የአዲሱ ሕይወት ምልክቶችን የሚያፈራ ሕያውና ብርቱ ቃል ነው። » ይህ ቃል አማኙ በውስጣዊ ማንነቱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔርን እንደ ሰማያዊ አባት ማወቅን፣ አዲስ የጸሎት ልምምድን፣ የእግዚአብሔርን ቃል መረዳትን እና የኢየሱስን ድምጽ ምሪት የመከተልን ጨምሮ የአዲሱን ህይወት ምልክቶችን ያሳያል። » በውጫዊውና በሚዛመደው መንገድ ደግሞ የሚለወጠው ቃል ራስን ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር መለየትን፣ አዲስ የክርስቶስን ባህሪ እና የአኗኗር ዘይቤን ማሳየትን፣ ለሌሎች አማኞች ፍቅር እና የጠፉትን ለክርስቶስ የመማረክን መሻት ጨምሮ ውጫዊ ምልክቶችን ያሳያል። የሚከተሉት ጥያቄዎች የተዘጋጁት በሁለተኛው የቪዲዮ ክፍል ውስጥ ያለውን ይዘት ለመገምገም ለመርዳት ነው። የእግዚአብሔር ቃል በአማኙ ውስጥ እውነተኛ ፍሬ የማፍራት ችሎታ እና ሃይል ለእኛ የአገልግሎት ተስፋ እና ብርታት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ለማካፈል እንተጋለን ምክንያቱም ቅዱሳት መጻህፍት የተቀበሉትን እና የሚያምኑትን ሰዎች ህይወት ለመለወጥ ባለው ችሎታ ላይ ሙሉ እምነት ስላለን ነው። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. የእግዚአብሔር ቃል አዲስ አማኝ ከአብ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚለውጠው በምን መንገድ ነው? አዲሱ አማኝ በክርስቶስ በማመን እና በመንፈስ ውስጥ በመኖር ከእግዚአብሔር ጋር ስለሚኖረው አዲስ ግንኙነት ምን አይነት ማረጋገጫ ይሰጣል? 2. ቅዱሳት መጻሕፍት የጸሎትን ልምምድ በእግዚአብሔር ቃል የመለወጥ ምልክት አድርገው እንዴት ይገልጹታል? 3. የእግዚአብሔር ቃል በአማኞች ልብ ውስጥ ካለው ተጽእኖ የተነሳ የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳትና የኢየሱስን ትእዛዛት ለመከተል ባላቸው ፍላጎት ረገድ ምን ዓይነት ዝንባሌና ድርጊቶችን ያሳያሉ? 4. አንድ ሰው የእግዚአብሔር ነኝ ብሎ መለወጡን ለማሳየት ከእነዚህ አንዱን (ወይም ሌላ) የውስጥ የመለወጡ ምልክቶች የግድ ማሳየት አለበት? አንድ ሰው ተለውጦ ምንም አይነት የለውጥ ምልክቶችን ላያሳይ ይችላል? እንዴት? 5. እያንዳንዱ እውነተኛ አማኝ የእግዚአብሔር ሕዝብ ለሆነችው ለቤተክርስቲያን ያለው አመለካከት ምን መሆን አለበት? በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን የጠበቀ ግንኙነት መጠበቅ እና ለሌሎች ክርስቲያኖች ደንታ ቢስ መሆን ይቻላልን? እንዴት? 6. ኢየሱስን በመውደድ እና ሌሎች አማኞችን መውደድ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? አብራራ።

መሸጋገሪያ 2

የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች

3

ገጽ 176

11

Made with FlippingBook Annual report maker