Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

8 6 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

7. የእግዚአብሔር ቃል መለወጥን ሲያመጣ የጠፉትን በተመለከተ የአማኙን አመለካከት ይለውጣል። የእግዚአብሔር ቃል አዲስ አማኝ ኢየሱስን ከማያውቁት ጋር ያለውን ግንኙነት እንዴት እንደሚለውጥ አስረዳ። 8. አንድ ሰው ሌሎች ኢየሱስን ሲያገኙ የማየት ምንም ፍላጎት ካላሳየ ከኢየሱስ ጋር የጠበቀ ግንኙነት መስርቻለሁ ማለት ይችላል? መልስህን አስረዳ።

ግንኙነት

ይህ ትምህርት የሚያተኩረው የእግዚአብሔር ቃል በአማኙ ውስጥ በንስሐ እና በእምነት አዲስ ሕይወት ለመፍጠር፣ አማኙን ከኃጢአት ተጽእኖ እና ኃይል ለማዳን በአማኙ ህይወት ውስጥ አዲስ የመንፈስ መገኘት እና ኃይል ምልክቶችን ለመፍጠር በሚችልበት ችሎታ ላይ ነው። ቃሉ ይለውጣል፥ ይህም ማለት የአማኞችን ሕይወት ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ ክርስቶስ ይስባል፤ ስለዚህም በሁሉም የሕይወታቸው አቅጣጫ እግዚአብሔርን የማክበርን ፍላጎት ይሰጣቸዋል።  የሚለውጠው ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከሚገኘው የመዳን የምስራች ጋር ተመሳሳይ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚለውጥ ቃል ነው።  ይህ ብርቱ ቃል ወደ ሜታኖያ ይመራናል፥ ይህም ማለት ከኃጢአት ንስሐ መግባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው።  ይህ ቃል ወደ ንስሐ (ሜታኖያ) ድኅነት የሚያደርስና በአማኙ ላይ እምነትን (ፒስቲስ) ለማምጣት በተመሳሳይ ኃይል የሚሰራ ነው። ይህ እምነት አማኙን ከኃጢአት ቅጣት፣ ኃይል እና ህይወት ያድናል።  የእግዚአብሔር ቃል አንድ ጊዜ በንስሐ እና በእምነት መስራት ከጀመረ የእግዚአብሔርን ይቅርታ እና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአማኙ ሕይወት ውስጥ የሚያረጋግጡ ምልክቶችን ይፈጥራል።  አማኙ በውስጣዊ ማንነቱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔርን እንደ ሰማያዊ አባት ማወቅን፣ አዲስ የጸሎት ልምምድን፣ የእግዚአብሔርን ቃል መረዳትን እና የኢየሱስን ድምጽ ምሪት የመከተልን ጨምሮ የአዲሱን ህይወት ምልክቶችን ያሳያል።  በውጫዊውና በሚዛመደው መንገድ ደግሞ የሚለውጠው ቃል ራስን ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር መለየትን፣ አዲስ የክርስቶስን ባህሪ እና የአኗኗር ዘይቤን ማሳየትን፣ ለሌሎች አማኞች ፍቅር እና የጠፉትን ለክርስቶስ የመማረክን መሻት ጨምሮ ውጫዊ ምልክቶችን ያሳያል።  ሶላ ግራሺያ (በጸጋ ብቻ) እና ሶላ ፊዴ (በእምነት ብቻ) የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በማመን የመለወጥን ተፈጥሮ የሚያጠቃልሉ ጠቃሚ የላቲን ቃላት ናቸው። በጸጋው የዳንነው በእምነት ብቻ ማለትም በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ስራ በመደገፍ ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ የመቤዠት እና የይቅርታ መሠረት ይህ ጸጋ እና እምነት ብቻ ነው።

የቁልፍ ፅንሰ-ሀሳቦች ማጠቃለያ

ገጽ 177 12

3

Made with FlippingBook Annual report maker