Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
9 4 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ጥሞና
የምንጓዘው መንገድ ማቴዎስ 4፡17-22 አንብብ። በህይወትህ ውስጥ ካሉት “ምን”፣ “ማን” እና “እንዴት” በስተጀርባ ያለው ትልቁ “ለምን” የህይወትህ አላማ ምንድነው? ማንም ሰው ሙሉ የበለጸገ ሕይወት መኖር አይችልም ወይም የተጠራበትን እና እግዚአብሔር የሚፈልገውን ሳያውቅ ምን ማድረግ እንዳለበት ሊገነዘብ አይችልም። ኦስ ጊነስ The Call በተሰኘው አስደናቂ መጽሃፉ ውስጥ ሁሉም ሰዎች የሕይወታቸውን የመጨረሻ ዓላማ ለማወቅ ስላላቸው ጥልቅ ፍላጎት ይናገራል። በልባችን ውስጥ ሁላችንም ከራሳችን የሚበልጥን አላማ ማግኘትና መፈፀም እንፈልጋለን። በራሳችን ልንደርስበት እንደማንችል ወደምናውቀው ከፍታ ሊያነሳን የሚችለው እንደዚህ ያለ ትልቅ ዓላማ ብቻ ነው። ለእያንዳንዳችን እውነተኛው ዓላማ ግለሰባዊ እና የምንወደው ነው - እኛ ምን ለማድረግ እና ለምን እዚህ እንዳለን ለማወቅ። ኪርኬጋርድ በጆርናሉ እንዲህ ሲል ጽፏል:- ‘ቁም ነገሩ ራስን መረዳት ነው፥ እግዚአብሔር በእውነት ምን እንዳደርግ የሚፈልገውን ማየት ነው፤ ነገሩ ለእኔ እውነት የሆነ እውነትን መፈለግ፣ እኔ ልኖርለትና ልሞትለት የምችለውን ሃሳብ ማግኘት ነው።” (Os Guinness, The Call. [Nashville: World Publishing, 1998, p.3])። ኢየሱስ በእርሱ አማካኝነት ለመጣው የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲኖሩ እየጠራ ወደ ምድር የሚመጣውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሰብክ ነበር። ጌታችን ስምዖንና እንድርያስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ሁለቱን ወንድማማቾች ሲያገኛቸው አሳ ከማጥመድ ወደሚበልጥ እውነተኛና ታላቅ ዓላማ ጠራቸው። ኢየሱስን እንደ ጌታ ለመከተል፣ ለሚያድነው እና ለደቀ መዝሙርነት የመታዘዝ ቃል ምላሽ መስጠት - የሕይወት አላማ ይህ ነው። ኢየሱስ ወደ እነዚህ ሰዎች መጥቶ እርሱን እንዲከተሉት ያደረጋቸውን ጥሪ እና ሰዎችን አጥማጆች እንደሚያደርጋቸው የገባውን ቃል ተናገራቸው። ሥራቸውን ብቻ ሳይሆን ሕይወታቸውንም ለወጠው። እነርሱም ቃሉን ሰምተው በእምነትና በታዛዥነት ምላሽ ሰጡ። ያ ወደ እምነት የጠራቸው ቃል ወደ ደቀመዝሙርነት ጠራቸው፣ በዚያም ቃል የሕይወትን ትርጉም አገኙ - ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን በማገልገል ለእግዚአብሔር ብቻ ክብርንና ምስጋናን ማምጣት። ዛሬ የተጓዝንበት መንገድ ምንም ይሁን ምን፣ ብንሰማ የጌታችንን ቃል በከተማው ጨለማማ ጎዳናዎች ላይ ሳይቀር ወጥቶ እንሰማለን። ኢየሱስ ሕያው ነው፤ በመንፈሱም ቅዱሳን ወንዶች እና ሴቶችን እንደ አገልጋዮቹ ይኖሩ ዘንድ መንፈሱ በየቀኑ ለእርሱ በመታዘዝ ሕይወታቸውን እንዲያስተካክል ወደራሱ ይጠራል። የጥንቶቹ ደቀመዛሙርት (ሁሉም እውነተኛ ደቀ መዛሙርት እንደሚያደርጉት) ወዲያውኑ በታዛዥነት፣ በእውነተኛ ስሜት እና በእውነተኛ ጉጉት ለእግዚአብሔር ምላሽ ሰጥተዋል። ምንም እንኳን ቤተሰብ፣ ኃላፊነቶች፣ ግዴታዎች እና ስራዎች ቢኖራቸውም ማንም ሊሰጣቸው የማይችለውን የዘላለምን ህይወት ሊሰጣቸው የሚችለውን እርሱን ለመከተል ሁሉንም ነገር ትተው ተከተሉት። በጉዞህ መካከል፣ በስራህ፣ በህይወህ ውስጥ የእግዚአብሔርን ጥሪ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሰምተህ ምላሽ ሰጥተሃል? ከላይ ያየናቸው ወንድማማቾች እንዳደረጉት ‘ወዲያው ሁሉን ትተህ ተከተልኸው’? ከሰማኸው ለእነርሱ እንደሰጣቸው አይነት ሉዓላዊ የምሪት ቃል ሲሰጥህ ትሰማለህ። “ተከተሉኝ፣ ሰዎችን አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” የሚለው የገባው ቃል ዘወትር የታመነ ነው። ከእንግዲህ ለራስህ አትኖርም፣ ለክብሩ ትኖራለህ፣ ለሌሎችም የታላቅ የክብር ማዳኑ ምስክር ትሆናለህ። ለቃሉ ምላሽ ስጥ፣ ደቀ መዝሙሩ ሁን፣ ወደ ራሱ እና ወደ ደቀ መዝሙርነት ለሚጠራህ ቃሉ ምላሽ ስጥ።
ገጽ 179
2
4
Made with FlippingBook Annual report maker