Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide

/ 9 5

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት

የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ የሚገኝ) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ: የዘላለም አምላክ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሆይ፥ ሕያው ጌታ የሆነው ልጅህ ሕዝብህ እንሆን ዘንድ እንዲጠራንና በመንፈስህ ኃይል የሚደግፈንን ቃል እንዲናገር እንለምንሃለን። የተጠራነው ወደ ደቀመዝሙርነት፣ ማህበረሰብ፣ ነጻነት እና ሚሽን ነው። ቅዱስ እና ዘላለማዊው ቃልህ በመካከላችን ይሰማ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፣ ቃልህንም በሙሉ ልባችን እንድንከተል፣ በደስታ እንድናገለግልህ፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንድንጸና፣ ልብህንም ለማሳረፍ እንተጋ ዘንድ እና በቤተክርስቲያንም ክብርህን እናመጣ ዘንድ ድፍረት እና ጽኑ ፍላጎትን ስጠን። ወደ ራስህ ስለሚጠራን ቃል እናመሰግንሃለን። በኢየሱስ ስም አሜን። ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ በሰማያዊ ስጦታህ ስላነቃቃኸን እናመሰግንሃለን። ከምህረትህ የተነሳ በአንተ ላይ ባለን ጽኑ እምነት እርስ በርሳችን በልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር እንድንኖር እንጸልያለን። አሜን።

ገጽ 179 3

~ Martin Luther. Devotions and Prayers of Martin Luther. Trans. Andrew Kosten. Grand Rapids: Baker Book House, 1965. p. 39.

ማስታወሻዎችህን አስቀምጥ ፣ ሀሳብህን ሰብስበህ የትምህርት 3ን ፈተና ውሰድ ፣ የሚለውጠው ቃል

አጭር ፈተና

ከሌላ ሰው ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደበውን የቃል ጥናት ክፍል ፃፍ ወይም በቃልህ አንብብ: ሮሜ 10: 8-13

የቃል ጥናት ክፍል ቅኝት

4

ባለፈው ሳምንት ለተሰጠው የንባብ የቤት ስራ መምህርህ የሚጠብቅብህን ዋና ዋና ነጥቦችና ማጠቃለያ አቅርብ (ንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ)።

የቤት ስራ ማስረከቢያ

እውቂያ

አንድ ክርስቲያን ምን ያህል ገንዘብ ማግኘት ይችላል? በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚገኝ የወንዶች ደቀ መዛሙርት ጥናት ቡድን ውስጥ በሉቃስ ወንጌል ላይ ጥናት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ የጦፈ ሙግት እየተካሄደ ነው። ሉቃ 14፡33 “እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።” ይላል። አንድ ወንድም ይህንን (ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጋር) ሲተረጉም አንድ ክርስቲያን ሀብታም መሆን አልፎ ተርፎም የግል ሃብትን ማካበት እንደማይችል በመግለጽ ያለውን ሁሉ መተው እንዳለበት ይናገራል። በጥናቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወንድሞች ደግሞ ይህ ከልክ ያለፈ ትርጓሜ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ዋናው ነገር ንብረታቸውን ሁሉ ለመተው ፈቃደኛ መሆን አለባቸው ማለት ነው እንጂ ያላቸውን መተው አይኖርባቸውም የሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ። በዚህ ውይይት ውስጥ የሚታየው የደቀመዝሙርነት እውነተኛ ባህርይ ምንድነው?

1

ገጽ 180 4

Made with FlippingBook Annual report maker