Conversion and Calling, Amharic Module 1 Mentor Guide
9 6 /
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ጊዜ ከትዳር ጓደኛ ጋር እና የአገልግሎት ጊዜ የቤተክርስቲያኒቱ ሽማግሌዎች በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ አርብ ምሽት ይገናኛሉ፣ ይህም አብዛኞቹ ወንዶች እና ሴቶች የሚሳተፉበት ጊዜ ነው። አንድ ውድ ወንድም ከሽማግሌዎች ቦርድ መልቀቅ እንዳለበት ወስኗል ምክንያቱም ላለፉት ጥቂት ዓመታት ዓርብ ምሽቶችን ከሚስቱ ጋር የፍቅር ምሽቶች ማሳለፍ ባለመቻላቸው ነው። እግዚአብሔር ከቤተክርስቲያን በፊት ለትዳሩ ቅድሚያ እንዲሰጥ ስለሚፈልግ በቤተክርስቲያን የሽማግሌዎች ጉባኤ ውስጥ ማገልገል እንደማይችል ያምናል። ሌሎች የቦርዱ አባላት በበኩላቸው ቤተክርስቲያንን እና የቤተክርስቲያን ጉዳዮች እንደ እግዚአብሔር ማህበረሰብ ከጋብቻ እና ከቤተሰብ ጉዳዮች ይልቅ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ ይከራከራሉ። ይሄ የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ቤተሰብ የክርስቶስ እና የቤተክርስቲያን አርአያ መሆን እንዳለበት የሚጠቁሙ ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍትን በማስደገፍ ተከራክሯል። ከእነዚህ ወገኖች ክርክር አሳማኝ ሆኖ ያገኘኸው የየትኛውን ወገን ነው? ወደ መዳን ሳይሆን ወደ ደቀመዝሙርነት ጋብዟቸው በአቅራቢያው የሚገኘው የባፕቲስት ጉባኤ በአምልኮ አገልግሎቱ ላይ ውዝግብ እየገጠመው ነው። ጥሩ ክርስቲያን እና የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ የሆነው አዲሱ የቤተክርስቲያኒቱ መጋቢ ያለ ጥሩ ደቀመዝሙርነት መዳን እንደማይኖር ያምናል። ቤተ ክርስቲያኒቱ በየአገልግሎቱ መጨረሻ ላይ ጌታን ያልተቀበሉ ወገኖች በእምነት እና በመታዘዝ ወደ እርሱ እንዲመጡ ትጋብዛለች። ይህ መጋቢ ከመጣበት ጊዜ አንስቶ ኢየሱስን እንደ ጌታህ ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆንክ አዳኝ አድርገህ ልትቀበለው አትችልም በማለት ደጋግሞ ሰብኳል። ኢየሱስን አዳኝ እና ጌታ አድርጋችሁ ትቀበላላችሁ እንጂ አንዱን አንደኛ ሌላውን ደግሞ ሁለተኛ አድርጋችሁ አትቀበሉም። ይህም አንዳንድ ዲያቆናት ከተረዱት ነገር ጋር የሚቃረን ይመስላል፣ “መዳን በእምነት በጸጋ” ነው፥ ይህ ድነትን የእግዚአብሔር ስጦታ ሳይሆን የክርስቲያን ሥራ ከማድረግ ጋር የተያያዘ ይመስላል ይላሉ። የክርስቶስን ግብዣ እንዴት መረዳት አለብን - ምን ማለት ነው?
2
3
4
የሚጠራው ቃል ክፍል 1
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
ይህ የመጀመሪያው ክፍል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ደቀመዝሙርነት የሚጠራ ቃል ነው የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ይዳስሳል። እግዚአብሔር በቀላሉ ክርስቶስን ወደ መምሰል አይለውጠንም፥ ይልቁንም የእርሱን ታሪክ በደቀ መዝሙርነት ሕይወት እንድንኖር ጠርቶናል። በእምነት ወደ መዳን የሚጠራን ቃሉ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እሱን እንድናገለግለው ከጋብቻ እና ከቤተሰብ በላይ እርሱን እንድንወደው፣ ለኢየሱስ ራሳችንን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንድንቀርብ ይጠራናል። አዲሱን ማንነታችንን በክርስቶስ ልንቀበል ይገባናል፤ ይህም የደቀመዝሙርነት ጥሪ እግዚአብሔርን ለማክበር እና አዲሲቱን የእግዚአብሔር ከተማ በክብር የምንፈልግ እንደመሆናችን መጠን በዚህ ዓለም
የክፍል 1 ማጠቃለያ
Made with FlippingBook Annual report maker