Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

2 8 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

መ. ልናጠናው ይገባል። የቤርያ ሰዎች በሐዋርያት ሥራ 17.11 ከተሰሎንቄ ሰዎች ይልቅ “የላቁ ጠቢባን” ተሰኝተዋል ምክንያቱም የሐዋርያው ጳውሎስን ቃል መስማት ብቻ ሳይሆን የጳውሎስን ወንጌል ለማረጋገጥ በየቀኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑ ነበር።

ሠ. በቤተክርስቲያን ሲሰበክ እና ትምህርት ሲሰጥ መስማት ይኖርብናል። ሮሜ 10፡ 17 “እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነውና” እንደሚል ቃሉን እንስማ እንጂ ትንቢትን መናቅ የለብንም።

1

ረ. በሁሉም ሕይወታችን እና ንግግራችን ውስጥ ልናካትተው ይገባል። የሚፈጥረው ቃል በሼማ (shema) ቃል እንደተነገረው በሕይወታችን ውስጥ ዋነኛው ኃይል መሆን አለበት፣ ዘዳ. 6፡4-9።

ሐ. ይህ የእግዚአብሔር ፈጣሪ ቃል በክርስቲያን ማኅበረሰብ አውድ ውስጥ ይሰማ እና ይከበር ዘንድ ይገባል።

1. ትንቢትን አትናቁ፥ መንፈስም አታጥፉ፣ 1ኛ ተሰ. 5፡19-22።

2. ቃልን መግለጥ በጉባኤ መካከል ይመጣል፣ 1ኛ ቆሮ. 14.26.

3. እግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶችን በመንፈስ ቅዱስ ታጥቀው የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምሩ ዘንድ ስጦታ አድርጎ ለቤተክርስቲያን ሰጥቷል፣ ኤፌ. 4፡11-13።

III. ቃሉ የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ዓላማ ለፍጥረተ ዓለሙ ይገልጣል፡- ሁሉም ነገር ለጌታ ክብርን እና ሞገስን ያመጣ ዘንድ።

ሀ. ከመለኮታዊው ታሪክ ማዕከላት ውስጥ አንዱ ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ለራሱ እና ለክቡር ስሙ ክብርን እና ምስጋናን ለማምጣት ነው የሚለው ነው።

1. ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ለእግዚአብሔር ዓላማ ነው፣ ምሳ. 16.4.

Made with FlippingBook - Online magazine maker