Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ተጨማሪ መግላጫ • 123
ተጨማሪ መግላጫ 1 ከዕለታት አንድ ቀን የፅንፈ ዓለሙ ድራማ ስለ ዓለም መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ትረካ ሬቨ. ዶር. ዶን ኤል. ዳቪስ
ከዘላለም እስከ ዘላለም ጌታችን አምላክ ነው። ከዘላለም ጀምሮ ማለትም ጊዜ ከመጀመሩ በፊት አቻ በማይገኝለት ድንቅ በሆነ ምስጢራዊ ህላዌ ስሉስ እግዚአብሄር ዕፁብ ድንቅ በሆነ በዘላለም ህብረት ውስጥ እንደ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ እኔ እኔ ነኝ በሆነ ማንነቱ ውስጥ ፍጹምና ውብ የሆነውን ማንነቱን በዘላለም ግንኙነታቸው ውስጥ አንዳች በማይፈለግ፣ ባልተውሰነ ቅድስና ደስታ እና ውበት ራሱን በመግላጥ ይኖራል። እንደ እርሱ ሉዓላዊ ፈቃድ አምላካችን ፍፁም ከሆነው ፍቅሩ በመነሳት የእርሱ ድንቅ ግርማና ውበት የሚታይበትን ግዙፍ የሆነ አጽናፈ ዓለምን፣ የእርሱ ክብር የሚገለጥበትን እና በመልክና በአምሳሉ የፈጠራቸውን የእርሱን ልጆች የሚኖሩበትን፣ ከእርሱም ጋር በህብረት የሚካፈሉበትን እና ከእርሱም ጋር ባላቸው ግንኙነት አንድ መሆናቸውን ሃሴት የሚያደርጉበትን ለእርሱ ክብር የሚያመጡበትን ዓለምን ፈጠረ። እሱ በሉዓላዊ አምላክነቱ በእርሱ ፍጹም ትዕዛዝ ላይ ሊያምጽ የሚችል ዓለምን ፈጠረ። በሰማያዊ ስፍራ በእግዚአብሄር እመሰላለው ብሎ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ፍቃድ በመቃወም ባሴረው ዲያብሎሳዊ ሴራው ምክንያት ስፍር ቁጥር የሌላቸው መላዕክትን አስከተሎ በወደቀው በዚህ ዓለም ጋዢ በሆነው በሰይጣን ተታልለው የመጀመሪያዎቹ ሰብዓዊ ፍጡራን በምኞት በስግብግብነት እና በትዕቢት ጎምዥተው በእርሱ ፈቃድ ላይ አመጹ። በአዳምና በሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት ራሳቸውን እና ወራሾቻቸውን ለሀዘንና ለሞት አጋለጡ፤ እናም በአመጻቸው ምክንያት ፍጥረትን ሁል ወደ ድቅድቅቅ ቀውስ መከራና ክፋት ውስጥ ከተቱ። በኃጢአታቸው እና በአመፃቸው ምክንያት በእግዚአብሔር እና በፍጥረታት መካከል ያለው አንድነት ጠፋ እናም አሁን ሁሉም ነገሮች የዚህ ታላቅ ውድቀት ውጤት እና የሁሉም ነገሮች መሠረታዊ እውነታ ወይም ሃቅ በሆነው መጥፋት መለያየት እና ኩነኔ ተገዢ ሆነዋል። ይህንን ችግር ምንም ዓይነት መላዓክ የሰው ልጅ ወይም ፍጥረት አይፈታውም፤ እናም ያለ እግዚአብሔር ቀጥታ ጣልቃ ገብነት ሁለም ጽንፈ ዓለም ምድር እና ሁለም ፍጥረታት በሙሉ ይጠፋሉ። በሉዓላዊ ኪዳናዊ ፍቅር ውስጥ እግዚአብሔር የዓጽናፈ ዓለሙን ዓመፅ ለሜበዠትና ለማስወገድ የወደቀውን የሰውን ልጅ መልክ የሚወስድ ከእግዚአብሄር መለየቱና መጥፋቱን የሚካፈልና የሚያስወግድ እንዲሁም ስለ ሃጢአትና አለመታዘዛቸው የእነርሱ ምትክ ሆኖ መከራን የሚቀበል አሸናፊ የሆነ አንድ ልጁን እንደሚልክ ወስኗል። ስለዚህ በቃል-ኪዳኑ ታማኝነት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ድነታቸው ሲል በቀጥታ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ተካፋይ ሆነ። ጌታ እግዚአብሔር ፍጥረቱን ለማደስ ሲል፣ ክፉን ለአንዴና ለመጨርሻ ጊዜ ለመገደብ እና እርሱ ለሚያመጣው አና ለሚመሰርተው የግዥነት ህይውት ለራሱ የሚሆንን ህዝብ ለመመሥረት ራሱን ዝቅ አደረገ። ስለዚህ ገዥው የሚመጣበትን ሕዝብ አስነስቶ ነበር። ስለዚህም በኖኅ አማካኝነት ዓለምን ከራሱ ክፋት አዳነው በአብርሃምም አማካኝነት የተስፋውን ዘር የሚያመጣበትን ነገድ መረጠ። በይስሐቅ በኩል ለአብርሃም የተገባውን ቃል ኪዳኑን አስቀጠለ እናም በያዕቆብ በኩል(እስራኤል) ዘሩን የሚያመጣበትን ነገድ(ይሁዳን) ለይቶ በመምራጥ ህዝቡን መሰረተ። በሙሴ አማካኝነት ከጭቆና ባርነት ነፃ አውጥቶ የቃል ኪዳኑን ሕግ ሰጣቸው እናም በኢያሱ አማካኝነት ሕዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር አመጣ። በመሳፍንት እና በእስራኤልዳ መሪዎች ነገር ግን በምሕረቱ እና በለጋስ ፍቅሩ ምክንያት ጌታ አምላክ ፍጥረቱን ለማዳን ቤዛ እንደሚልክ ቃል ገብቷል።
Made with FlippingBook - Online magazine maker