Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
This is the Amharic edition of Fight the Good Fight of Faith, a follow-up curriculum based on the book of Ephesians.
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ በእግዚአብሄር አስደናቂ ሥራ ውስጥ የእኛን ሚና መጫወት
በቄስ ዶን ኦልስማን እና ቄስ ዶን ዶ.ዴቪስ
Amharic
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ በእግዚአብሄር አስደናቂ ሥራ ውስጥ የእኛን ሚና መጫወት የቅዱስ መሰረት ስርዓተ ትምህርት መከታታያ
በቄስ ዶን ኦልስማን እና በቄስ ዶ/ር. ዶን ኤል. ዳቪስ
TUMI Press 3701 East 13th Street North Wichita, Kansas 67208
የከተማ አገልግሎት ተቋም ፥ የዓለምዓቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ አገልግሎትድርጅት
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ: በእግዚአብሄር አስደናቂ ሥራ ውስጥ የእኛን ሚና መጫወት
© 2014, 2016. የከተማ አገልግሎት ተቋም። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው የመጀመሪያ ዕትም 2014 ሁለተኛ እትም 2016 © 2017 የአማርኛ ዕትም በመጋቢ ቴዎድሮስ በ ወርቅነህ ተተረጎመ
የ 1976 የቅጅ መብት ደንብ በግልጽ ካልተፈቀደልዎ ወይም ከዓታሚው በጽሁፍ ካልተፈቀደ በስተቀር ይህንን መጽሐፍ መገልበጥ፣ እንደገና ማሰራጨት እና / ወይም ማንኛቸውም ያልተፈቀዱ ስርጭቶችን ማድረግ በህግ የተከለከሉ ናቸው። የፍቃድ ጥያቄዎች በሚከተለው አድራሻ በጹሁፍ መላክ አለባቸው::
The Urban Ministry Institute 3701 East 13th Street North Wichita, Kansas 67208
ISBN: 978-1-62932-201-8
በTUMI Press ታተመ የዓለምዓቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ አገልግሎት ክፍል ኢንክ.
የከተማ አገልግሎት ተቋም የዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ አገልግሎት ድርጅት ክፍል ነው
በተለየ መልኩ በጸሐፊው ካልተጠቀሰ በስተቀረ ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ከኢንግሊሽ ስታንዳርድ ቨርዝ(ኢኤስቪ) መጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ናቸው። ይሁን እንጂ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በጸሃፊው ቀለል ባለ መልኩ ተተርጉመው ቀርበዋል።
ይህ መጽሐፍ የተፃፈው ለአዳዲስ እና እያደጉ ያሉ አማኞችን ለሚያስተምሩ እና ሜንቶር ለሚያደርጉ ነው. . .
13 ለመጋቢዎ መምህራን ሜንቶሮች መንፈሳዊ ዳይሬክተሮች እና ደቀ-መዝሙር አድራጊዎች - ለቅዱሳን መንፈሳዊ እንክብካቤ ለሚያቀርቡ እና ዘወትር የክርስቶስን ተከታዮች ለማጠናከርና ለማነፅ ጽኑ ፍላጎት ላላቸውና እንዲሁም ቅዱሳንን በመውደድ በማጽናናት በማስተማርና በማጠናከር መንፈስ ቅዱስ በመላው ዓለም እንዲጠቀምባቸው ለተሰማሩ እና ተገቢውን ጥረት ለሚያደርጉ ሁሉ ነው።
14 ስጦታቸውን መንፈሳዊ ብቃት ያላቸው አዲስ ትውልድ ሠራተኞችን ለማስነሳት፣ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማክበር እና መንግሥቱን ለማስፋት ስለሚተቀሙ አገልጋዮች እግዚአብሔርን እናከብራለን።
• • •
ለፌይርማውንት ፓርክ ዴይብሬክ ቡድን- ከብዙ አመታት በፊት ልክ እንደኔ ለከተማ ወጣት አገልግሎት እና የወጣት መሪዎችን ለእግዚአብሄር መንግሥት ለማስነሳት መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ያመኑና ኢንቨስት ያደርጉ ነበርና ለእነርሱም ምስጋናዬ ታላቅ ነው።
ዶን ዴቪስ
• • •
ለሼርሊ አይዛክ- ለጌታ ኢየሱስ እና ለወንጌል ላስተዋወቀኝ የ6ኛ ክፍል ጓደኛዬ እና ለቶሮን ፍራይበርግ ለመጽሐፍ ቅዱስ ሊኖረኝ የሚገባውን ፍቅር ላሳየኝና በመንፈስ መመላለስን ላስተማረኝ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወጣት መሪዬ።
ዶን ኦልስማን
• • •
ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡2
የርዕስ ማውጫ • 5
የርዕስ ማውጫ
7 መግቢያ
15 ትምሕርት 1 ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል
የእኛን ታሪክ ከእግዚአብሔር ታሪክ ጋር ማስተሳሰር
25 ትምሕርት 2
ወዶ ዘማችነታችን ዘመን ጠገብ በሆነው በዓጽናፈ ዓለም ግጭት ውስጥ ያለንን ሚና መቀበል
37 ትምሕርት 3
የምናገኘው መግቢያ ህይወታችንን በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ህይወት ጋር ማዛመድ
49 ትምሕርት 4
የተቀበልነው ስጦታ በመልካሙ የእምነት ተጋድሎ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ሚና
61 ትምሕርት 5
የምናሳየው ልዕቀት በዚህ ዓለም እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን እና የክርስቶስ አምባሳደሮች መኖር
73 ትምሕርት 6
የምንፈለገው መታነጽ በክርስቶስ አካል ውስጥ እርስ በርስ መተናነጽ
85 ትምሕርት 7
የምንዋጋው ጠላት በእግዚአብሔር ጠላቶች ላይ በድል መመላለስ
97 ትምሕርት 8
የምንጠቀመው መሣሪያ የእግዚአብሔርን ዕቃጦር ሁሉ መልበስ
109 ትምሕርት 9
የምናሳየው ጽናት የቅዱሳን ጽናት
6 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
121 ተጨማሪ አባሪ 123
ተጨማሪ አባሪ 1 • ከዕለታት አንድ ቀን:
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዓለም በዘገበው ዘገባ ውስጥ የፅንፈ ዓለሙ ድራማ/ክስተት
ተጨማሪ አባሪ 2 • እግዚአብሔር የሚናገረው ታሪክ
125 126 128 129 130 132 133 135 136 137 138 140 144 131
ተጨማሪ አባሪ 3 • መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መጀመር የሚቻለው እንዴት ነው?
ተጨማሪ አባሪ 4 • የናዝሬቱ ኢየሱስ - የወደፊቱ መገኘት ተጨማሪ አባሪ 5 • የእግዚአብሔር ታሪክ: የእኛ ቅዱስ መሰረት
ተጨማሪ አባሪ 6 • ከጅማሬ ወደ ፍፃሜ:
የእግዚአብሔር ዕቅድ እና የሰዎች ታሪክ
ተጨማሪ አባሪ 7 • ጥላ እና አካል ተጨማሪ አባሪ 8 • በክርስቶስ
ተጨማሪ አባሪ 9 • በክርስቶስ ላይ ጥገኛ የመሆናችን መገለጫ፡ ነጻነት በክርስቶስ
ተጨማሪ አባሪ 10 • የቤተሰብ ሁኔታ
ተጨማሪ አባሪ 11 • የክርስተስ ቪክቶር ሥነ-መለኮት
ተጨማሪ አባሪ 12 • ክሪስተስ ቪክቶር:
የተቀናጀ ራዕይ ለክርስቲያን ሕይወት እና ምስክርነት
ተጨማሪ አባሪ 13 • መጽሐፍ ቅዱስን በተናጠል እና በጠቅላላው መረዳት
ተጨማሪ አባሪ 14 • በክርስቶስ የተገኙ ሰላሳ ሶስት በረከቶች
ተጨማሪ አባሪ 15 • ጉብታው
145 ተጨማሪ አባሪ 16 • ወደ ኋላ መለስ ብለን በመሄድ ወደፊት መጓዝ- ወደ ታላቍ የወንጌላዊያን ባህል እንደገና መመለስ 150 ተጨማሪ አባሪ 17 • የቅዱሳት መጻሕፍት ማጠቃለያ ዝርዝር ንድፍ 154 ተጨማሪ አባሪ 18 • የአዲስ ኪዳን የዘመን ቅደም ተከተል ሰንጠረዥ 155 ተጨማሪ አባሪ 19 • መሲሑን ማስተላለፍ: የወንጌላት ስምምነት 156 ተጨማሪ አባሪ 20 • ለመወከል ምቹ መሆን: የእግዚአብሔር መንግሥት ደቀ-መዛሙርቶችን ማባዛት 157 ተጨማሪ አባሪ 21 • የአዲስ ኪዳን ሥነ-ምግባር፡ከላይ-ወደታች በሆነ የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ መኖር 158 ተጨማሪ አባሪ 22 • ኢየሱስ ክርስቶስ፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳይ እና ጭብጥ 159 ተጨማሪ አባሪ 23 • እግዚአብሔር ይነሣ! ጌታን የመፍለግ እና የእርሱን ሞገስ የመቀበያ ሰባቱ “ሀ” ዎች 160 ተጨማሪ አባሪ 24 • የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ 161 ተጨማሪ አባሪ 25 • የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ ጋር 163 ተጨማሪ አባሪ 26 • የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ
መግቢያ
ደቀ መዝሙርነት የዕውቀት መግባባት ሳይሆን የህይወት ግንኙነት።
~ ጁዋን ካርሎስ ኦርቲስ
የእምነት አርበኞች ሆይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ብርቱ ስም ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ወጣት ደቀ መዛሙርት /የክርስቶስ ተዋጊ/ ሆይ ይህንን መልካሙን የእምነት ገድል መጋደል— በእግዚያብሔር አስደናቂ ሥራ ውስጥ የእኛን ሚና መጫወት የተሰኘውን መጽሐፍ/ ሀብታችንን/ ለእናንተ በማቅረባችን ታላቅ ደስታ ይሰማናል። ይህ የመማሪያ መጽሐፍ የመጽሃፍ ቅዱስ ድራማ ወይም ታሪክ ማለትም እኛ በእግዚአብሔር ዓብይ ታሪካዊ ስራ ውስጥ ያለንን ቁልፍ ተሳትፎ ወይም ገጽታ ምን እንደሚል የተፃፈውን ንድፍ ያሳየናል። እኛ የዓለም እውነተኛ ታሪክ ዓላማና ፍፃሜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቧል የሚል ጽኑ እምነት አለን። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን እንደ የሕይወት ምንጭ፣ አጽናፈ ዓለሙን የፈጠረ፣ የምድርን አህዛብን ሁሉ እንድሚባርክ ለዚህም የተባረከ አንድ ዘር እንደሚልክላቸው ለአብርሃም ቃል ኪዳንን እንደሰጠ እንደሚያሳይ ፅኑ እምነት አለን። እግዚአብሔር አምላክ ለሕዝቦቹ ማለትም የተቀባውን መሲሑ እንዲመጣ የተጠቀመበትን ለእስራኤል ህዝብ ራሱን ገለጠ። ጌታ ኢየሱስ ሞትን ለማሸነፍ፣ እርግማንን ለማጥፋት እና በሰው ልጆች መካከል የእሱን አገዛዝ ለመመስረት ወደ ዓለም የመጣ በእግዚአብሔር የተመረጠ አገልጋይ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ መሲሁ በሕዝቡ /በእስራኤላውያኑ/ በኩል እንደመጣና እርሱ ማን እንደሆን እናውቃለን፤ የናዝሬቱ ኢየሱስ ቤዛ እና ንጉሥ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር የእግዚአብሄር አብን ዕቅድ እና ክብር ለሰው ልጆች ሁሉ እንደገለጠ በመስቀል ላይ በመሞት እና ከሙታን በመነሳት ከኃጢአታችንም እንደተቤዠን፣ እንዲሁም በዳግመኛ ምፅዓቱ በቅርቡ ሁሉን እንደገና እንደሚያድስ ይናገራሉ። እኛ ንስሓ ስንገባ እና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነትነትና አዳኝነት ስናምን ይህ ታላቅ ታሪክ የእኛ የራሳችን ታሪክ ይሆናል። ይህም አስደናቂ የጸጋ እና የፍቅር ታሪክ፥እኛ እንድንካፈለው እና በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ካሉት ቤተሰቦች/በቤተ ክርስቲያን/ ጋር ለመኖር የሚጋብዘን ድንቅ ታሪክ ነው። የትምህርቱ አጠቃላይ ዕይታ: መልካሙን የእምነት ገድል እንዴት መጋደል እንደሚቻል ይህ መጽሐፍ ለአንባቢዎች ግልጽ እና ቀላል በሆነ መንገድ የዘመናት ጥያቄ የሆነውን እና የእርሱን አጠቃላይ ማብራሪያ ጎላ ባለ መልኩ ለማስረዳትና ለማብራራት እንዲሁም ትምህርቱን ከራሳችሁ ጋር በማዛመድ ከእግዚአብሔር ጋር እና ከሌሎች ቅዱሳን ጋር በቤተ ክርስትያን እንዴት እንደምትኖሩ ለመርዳት የቀረበ ነው። ይህም መንፈሳዊ ረሃብን ለተራባችሁ እና እያደጋችሁ ላላችሁ ለእናንተ በእግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ አዲስ ተዋናይ እንደሆነ ሰው እያንዳንዱን ትምህርት በጥንቃቄ በመረዳት እና በማዛመድ እንድትኖሩት ለማስቻል ይረዳ ዘንድ በተጠና መልኩ የተዋሃዱ ዘጠኝ ትምህርቶችን በማዋቀር የሚያብራራ ዘጠኝ ትምህርቶች ያካተተ ነው። ትምህርቶቹም ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን መጽሐፍ ውስጥ የገለጻቸውን የከበሩ እውነታዎችን በመዘርዘርና በማብራራት እናንተን በመሰረታዊ የክርስትና እምነት እና ምልልስ ላይ መሰረት ለመስያዝ የተነደፈ ነው። የትምህርት ክፍለ ርዕሶቹ እና ስለ እያንዳንዱ ትምህርት የተሰጠው አጭር ማብራሪያ ከዚህ በታች ቀርቧል።
7
8 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ትምህርት 1 ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል - የእኛን ታሪክ ከእግዚአብሔር ታሪክ ጋር ማስተሳሰር የሚለውን ሃሳብ ያስተምራል። ይህ ትምህርት ዓጽናፈ ዓለሙን ሁሉ የፈጠረ አምላክ ሁሉን ቻይ ጌታ ብቸኛ እውነተኛ እና የዘላለምም አምላክ እንደሆነና በሶስት አካል ውስጥ አባት፣ ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ እውን መሆኑን ያሳውቀናለ። እሱ ሁሉንም ነገር ማለትም- የሚታየውንና የማይታይውን ሁሉ የፈጠረ እንዲሁም ሰዎችን በራሱ መልክና አምሳል የፈጠረ ነው። ይህ ትምህርት የሰይጣንን እና የመጀመሪያዎቹን ሰብዓዊ ጥንዶች፣ የአዳምን እና ሔዋንን ዓመፅ እና በነርሱም አለመታዘዝ ምክንያት ፍጥረት ሁሉ እንዴት እንደተረገመ ያብራራል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ደግሞ ክፋትን ሁሉ የሚያሸንፍ እና ሁሉንም ለእግዚአብሔር ክብር የሚመልስ የአዳኝን እንደሚልክ ተስፋ እንደሰጠንም ያሳያል። ትምሕርት 2 ወዶ ዘማችነታችን፦ በአጽናፈ አለሙ ዘመን ጠገብ ግጭት ውስጥ ያልንን ድርሻ መቀበል የሚለው ትምህርት የናዝሬቱ ኢየሱስ ሰይጣንን እንዴት እንዳሸነፈና ከኃጢአት ነፃ በሆነ ህይወቱ እና በእኛ ምትክ በመሞቱ ከኃጢአትና ከእርግማን እንዴት ነፃ እንዳወጣን ያብራራል። አሁን ንስሃ በመግባት (ከኃጢአታችን ወደ እግዚአብሔር በመመለስ) እና በእምነት (በኢየሱስ ሥራ ላይ በእርጋጥ በማመን) ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባለን:: በጸጋው ያድነናል ፤ በክርስቶስ አካል ውስጥ እንጠመቃለን፤ እንዲሁም በክርስትና ህይወታችን እኛን ለመርዳት መንፈስ ቅዱስ ይሰጠናል፡፡ ትምሕርት 3 የምናገኘው መግቢያ : - ህይወታችንን በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ህይወት ጋር ማያያዝ የሚለው ትምህርት ከጌታ ከኢየሱስ ጋር እንዴት በእምነት እንደተሳሰርን ያስተምራል (ማለትም አሁን እኛ “በክርስቶስ” ነን)፡፡ በዚህ ትስስር ወይም ህብረት ምክንያት ጌታ ኢየሱስ የሆነውን እና የሚሰጠውን ሁሉ ትቀበላላችሁ ትለማመዳላችሁም፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስ አማካይነት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዕዘን ራስ ድንጋይ ወደሆነበት ሐዋርያትና ነቢያት መሰረት ወደ ሆኑበት የእርሱ ቤተሰብ ወይም ቤተ ክርስቲያን አባላት እንሆናለን፡፡ እያንዳንዱ የአጥቢያ ማኅበረ ምዕመናም የሰማይን ፍላጎቶች የሚያገለግል የእግዚአብሔር መንግሥት ኤምባሲ ሆኖ ያገለግላል ይወከላል፡፡ እኛ አማኞችም የዚህ መንግስት አምባሳደሮች እና ወኪሎች ሆነን እናገለግላለን፡፡ ትምሕርት 4 በዚህ ትምህርት የተቀበልነው ስጦታ: -በመልካሙ የእምነት ተጋድሎ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ሚና የሚለውን እንነጋገራለን፡፡ ይህ ትምህርት መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ እንዴት እንደሚያድር፣ እና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለእያንዳንዱን ስጦታ የሚሰጥበትን መንገድ ያሳያል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዳቸን እንደሚሰጠን ዕድል መመሪያ እና ብርታት መጠን ከሌሎች አማኞች ጋር ስጦታችንን መለማመድ እንድንችል በክርስቶስ ነፃ ወጥተናል፡፡ እያንዳንዱ አማኝ ኅብረቱን በአንድነትና በፍቅር በሚያገለግልበት ወቅት ሁላችን እንደ አካል ተያይዘን እናድጋለን፡፡ በትምህርት 5 ውስጥ ስለምናሳየው ልዕቀት: - በዚህ ዓለም እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን እና የክርስቶስ አምባሳደሮች መኖር የሚለውን እንመለከታለን። ሁላችንም እንደ ተወደዱ ልጆች የእርሱን ምሳሌ እንድንከተል የተጠራን መሆናችንን እናያለን፡፡ በክርስቶስ እኛ የእግዚአብሄር ቅዱሳን (ቅዱስ) ተብለን በሰዎች ሁሉ ፊት ቅዱሳንና የእርሱን በጎነት በመናገር እግዚአብሄርን እንድንወክል ተጠርተናል፡፡ እንዲሁም እንደ ክርስቶስ አምባሳደሮቹ፡ ለጓደኞቻችን፤ ለቤተሰቦቻችን እና ለሌሎች ጎረቤቶቻችን የመዳንን መልካም ዜና በማካፈል እና መልካም የፍቅር ስራዎችን በመስራት፤ ለክርስቶስ መስራት እና ለሌሎች አገልግሎት በመስጠት እንድናገለግል ተጠርተናል፡፡ ትምህርት 6 የምንፈለገው መታነጽ: - በክርስቶስ አካል ውስጥ እርስ በእርስ መተናነጽ በሚለው ትምህርት ውስጥ የክርስቲያን ሕይወት ፅንሰ ሃሳብ በህበረት ውስጥ ለመኖር የተቀየሰ እንደ እግዚአብሔር ቤተሰቦች አብሮ ለማደግ የክርስቶስ አካል እና የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ እንደሆነ እንዳስሳለን።፡ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን እና በትንንሽ ቡድኖች ውስጥ ከሌሎች አማኞች ጋር ተያይዘን
መግቢያ • 9
ከሌሎች ጋር አብረን የክርስትና ህይወትን ለመኖር የእርሱን እውነት በመረዳት እግዚአብሔርን በማምለክ እና እንደ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት አብረን እያደጉ ለመሄድ ተጠርተናል። ይህን በማድረግ በእምነታችን ላይ እየተገነባን (እየታነፅን) እና ስለ ክርስቶስ ክብር (በአክብሮት) አንዳንዳችን ለሌላችን እንዴት መገዛት እንዳለብን እንማራለን፡፡ ትምህርት 7 የምንዋጋው ጠላት: - በእግዚአብሔር ጠላቶች ላይ በድል መመላለስ የሚለው ትምህርት የተቀላቀልነውን ታላቅና አዲስ ታሪክ ባህሪውን ይገልጻል፡፡ ይህ ዓጽናፈ ዓለም በመንፈሳዊ ጦርነት ውስጥ ነው ያለው - ዲያቢሎስና የጨለማው መንግሥት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እና የብርሃን መንግስትን እየተዋጉ ናቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወቱ፣ በሞቱ እና በትንሳኤው በጠላታችን ላይ ማለትም በዚህ በወደቀ ዓለም ውስጥ ያለውን ስርዓት በመጠቀም በማታለል እና በድሮው ኃጢአተኛ ተፈጥሮ ውስጥ ይህም “በሥጋ ምኞቶች” እያሰራ ባለው ዲያቢሎስ ላይ ድልን ተቀዳጅቷል። እኛም በክርስቶስ በመኖር በእምነት በመመላለስ እና ዲያቢሎስ እኛን ለመፈትን የሚጠቀመውን ማናቸውንም የውሸትና የማታለል ጥረትና ሴራዎች በንቃት ከተከላከልን ድል እንነሳዋለን፡፡ ትምህርት 8 የምንታጠቀው መሳሪያ: የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ መልበስ የሚለውን ርዕስ ይዳስሳል ። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱን አማኝ ጠላትን ለመቋቋም እንዲችሉ እና በክፉ ቀን ሁሉን ፈጽመው ለመቆም የሚያስችላቸውን አስፈላጊውን አቅርቦተ እንዳደረገላቸው ያብራራል። የቅዱስ ቃሉ እውነት (ማለትም የእግዚአብሔር ቃል) ጠላት በእኛ ላይ የሚሰራውን ውሸት ለመለየት፤ ለመቃወም እና ለማስወገድ ያስችለናል፤ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ በግልም ሆነ ከሌሎች አማኞች ጋር መንፈሳዊ ልምምዶችን ስንለማመድ በተጋድሎው ፀንተን እንድንቆም ብርታትንና ጥንካሬን ይሰጠናል፡፡ ትምህርት 9 የመጨረሻው ትምሕርታችን ነው፤ ይህም የምናሳየው ጽናት: - የቅዱሳን ጽናት የቅዱሳት ጽናት የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል። በዚህ ትምህርት ውስጥ ወደ ክርስቶስ እያደገ የመሄድ ህይወት ማዕከላዊና መሰረታዊ መርሁ መፅናት፤ ንቁ መሆን እና በጠላት ከመያዝ ውጭ እንደሆነ እንመለከታለን። እንደ የክርስቶስ ተወካዮች ነገሮች የቱንም ያህል ከባድ እና አስቸጋሪ ቢሆኑም ሽልማታችንን ለማግኘት ወደፊት መግፋት እና መቀጥል አለብን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለተጠራንበት መጠራት በእውነት ለመቆም የሚያስችለንን ኃይል ይሰጠናል እንዲሁም ክርስቶስን በታማኝነት ስንወክልና ስንገልጥ ሌሎች አማኞችን በመንፈሳዊ ተጋድሎአቸው ጊዜ ለማበረታታና ለማጠንናከር ይጠቀምብናል፡፡ የእያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜ ንድፍ : መሰረቶቹ እና ክፍሎች እያንዳንዱ ትምህርት አትኩሮት መስጠት በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ መሰረት በማድረግ አጽነዖት መስጠት እንዲችሉ በአንድ ዓይነት ክፍፍሎች ተከፋፍሏል። (እንደ መሪም ሆነ ወይም እንደ የትንንሽ ቡድን አስተባባሪ ሆነው ይህን መፅሐፍ ከሌሎች ጋር ሆነው ሲያጠኑ ይህንን መገንዘብ በጣም ጠቃሚ ነው)። የትምህርቱ ዓላማዎች ለእያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜ ሦስት ግቦች አሉት፤ ይህም በግልም ሆነ ወይም ከሌሎች ጋር ሆነው ሲያጠኑ በትምህርቱ ማጠቃለያ ላይ በትክክል መረዳት የሚገባችሁን እንድትረዱ እና ምን ማመን እንዳለባችሁ እንድታውቁ ይረዳችኋል፡፡ የመክፈቻ ጸሎት- ለጥበብ ይህን ጸሎት በቃላችሁ እንድትደጋግሙት እና ከፍ ባልድምጽ እንድትጸልዩት እናበረታታለን። የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች ከማጥናታችን በፊት ጌታ ኢየሱስ ለእኛ ሊናገር ያለውን ሁሉ እንድንረዳ እና መቀበል እንድንችል ልባችንን እንዲከፍትልን እንፀልይ።
10 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ማገናኘት ይህ የማገናኘት ክፍል ከእውነታው ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን መሰረታዊ የህይወት ጉዳዮችን ሁኔታዎችን እና ጥያቄዎችን በመጠየቅ ከእውነተኛ ሃሳቦች ጋር በማገናዘብ ወደ ክፍሉ በጥልቀት ለመግባት የሚያስችለን “ዋናው ሃይል” ነው። በእነዚህ ምሳሌዎች ላይ ጥሩና በቂ የሆነ ጊዜን በማሳለፍ እንዲሁም የእነዚህን ጉዳዮች የህይወት እንድምታ በጥንቃቄ አጥኑ። እያንዳንዱን ትምህርት እያጠኑ ወደፊት በተጓዙ ቁጥር እነዚህ ምሳሌዎች የእናንተን የአስተሳሰብ እና የምርምር አቅም ወደላቀ ደረጃ ይቀርፃሉ። ይዘት የይዘት ክፍል ልናጠናውና ልንማረው የተዘጋጀውን ክፍል የመግቢያ ሃሳብን ይገልፃል፤ ትክክለኛ ጥያቄዎችን እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎችን በማቅረብ ለጥያቄውች መልስን በመመለስ የተዘጋጀውን የትምህርት ክፍል እንድንመለከት ያደርጋል። ማጠቃለያ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከተመለከትን በኋላ እና በማውጫ ክፍሉ ውስጥ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ ከሰጠን በኋላ የእያንዳንዱን ክፍለ-ጊዜ ቁልፍ ሐሳቦች አጭር እውነታዎች እና የትምህርቱ ክፍል ሊያስተላልፋቸው የፈለገውን ማጠቃለያ ሃሳቦችን ያቀርባል። ይህ በተለይ ለእናንተ በጣም ጠቃሚ የሆነ መመሪያ ነው በተለይም መጽሐፍ ቅዱስን በግል በምታጠኑበት ወቅት “ዋናውን ጭብጥ ሃሳብ “ ምን እንደሆነ እንደተረዳችሁት ወይም እንዳልተረዳችሁት ለማረጋገጥ ያስችላችኋል። ተጨማሪ አባሪዎች በዚህ ክፍል ውስጥ በክፍለ ትምህርቶች ውስጥ ያለውን ይዘት በእጅጉ እንድትረዱ እና በተግባረ ላይ ለማዋል ሊያስችሉ የሚረዱ ተገቢና አስፈላጊ የሆኑ ግራፊክስ ጽሁፎችን፣ አጠር ያሉ ተጨማሪ ጽሁፎችን እና ሰነዶችን አዘጋጅተን በአባሪነት አካተናል። በዚህ ክፍል ወስጥ የተካተቱት አባሪዎች በእያንዳንዱ ትምህርት ውስጥ ያሉትን ዋና ዋና እና መሰረታዊ መርሆዎችን እና ሃሳቦች በጥለቀት ለመረዳትና ግንዛቤዎን ለማሻሻል ጠቃሚ ሆነው ስለሚገኙ በዚህ ክፍል ውስጥ የተካተቱትን አባሪዎችን በአንክሮ ይመልከቱ፡፡ አስረጅ ወይም የማሳያ ጥናቶች ይህ ክፍል እያንዳንዱን ትምህርት መማርዎ በህይወትዎ ላይ የሚያመጣው አዎንታዊ እንድምታ እንዲሁም በተጨባጭ አስረጅ ወይም የማሳያ ጥናቶች በቀረቡት ጉዳዩች ዙሪያ የተረዱትን ለማስረዳት ዕድል ይሰጥዎታል። የደቀመዝሙርነት ህይወት ማለት እውነትን ለማሰብ እና ለመወያየት ብቻ አይደለም ይልቁንም ደቀመዝሙርነት ስለ እውነተኛ ህይወት ነው፤ ሰዎች ስለሚታገሏቸውና በሕይወታቸውም ላይ ተፅእኖ እና ጫና ስለሚፈጥሩባቸው የተለያዩ ህይወት ተግዳሮቶችም ጭምር የሚያሳይ ነው። በመሆኑም እነዚህ ጥናቶች በማደግ ላይ እንዳለ እንደ አንድ ደቀመዝሙር የእርሶን አስተሳሰብ ለማነሳሳት፣ ታሪኩን እና የታሪኩን እውነታ ከእርስዎ ታሪኮች እና እውነታዎች ጋር እንዴት ማዛመድ እንዳለቦት ይረዳሉ፡፡ እውነትን ማወቃችን ብልህ ያደርገናል ማለት አይደለም ነገር ግን ነፃነታችንን ያጎናፅፈናል፡፡ (ዮሐንስ 8.31-32). ስለዚህም እጅግ በጣም አስፈላጊው ነገር “ትክክለኛ መልስ” ከሚለው በላይ “ ለመማር ትሁት” መሆን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ሂደት ላይ ይህን ታያላችሁ ብዙውን ጊዜ ማንም ቢሆን ግልጽ ትክክለኛ እና ጥርት ያለውን መልስ ከእኛ የናሙና ወይም የማሳያ ጥናት ተመስርቶ ላይሰጥ ይችላል። ይልቁኑ በዚህ ላይ ተመስረተን የተረዳነውን ከህይወት ተዛምዶአችን ጋር እንድናካፍ በትሕትና ጥናት እንድናደርግና እንድናስተምር እንዲሁም ሁሉንም በመፈተንና መልካም የሆነውን ለመያዝ ተጠርተናል (1 ተሰ 521)። በመሆኑም እነዚህን የማሳያ ጥናቶች አሁን ከክፍሉ የተማራችሁትን ትምህርት ሊሆኑ ይችላሉ ለምትሏቸው ትርጓሜዎች ፍችዎች ለመመርመር እንዲሁም በእነዚህ አስረጅ ወይም የማሳያ ጥናቶች አማካኝነት በህይውታችሁ ውስጥ ቁልፍ መርህ ይህ ክፍል የትምህርቱን አጠቃላይ ትምህርት በአንድ ዓረፍተ ነገር ወይም በጥቅስ አጠቃሎ ያቀርባል፡፡
መግቢያ • 11
የሚያጋጥሟችሁን የተለያዩ ጉዳዮች የምትረዱበትን መረዳት ለማሻሻል እንድትችሉ መንፈስ ቅዱስ እንዲለውጣችህ ፍቀዱ።
ማገናኘት ይህ ክፍል በክፍሉ ውስጥ የተማረችኋቸውን እውነታዎች በተግባር መተግበራቸውን (“በተግባር ላይ መዋሉ”) እና ተጨባጭ መሆኑ ላይ ያተኩራል። በመሆኑም እናንተም የተማራችሁትን ትምህርት በአስተሳሰባችህ በንግግራቸሁ በተግባራችሁ እና ከሌሎች ጋር በሚኖራቸሁ ግንኙነት ውስጥ ሁለ የሚዛመዱበትንና የሚገናኙበትን መንገዶች ሁሉ መፍጠር አለባችሁ። ስለዚህ በዚህ ክፍል ውስጥ የምትማሩትን ትምህርት በግል ኑሮአችሁ ከህይወታቸሁ ጋር ለማዘመድ የሚትችሉበትን አገናኝ መንገዶችን ሁሉ ፈልጉ። ማረጋገጫ ይሄ እጥር ምጥን ያለ ክፍል ከትምህርቱ ውስጥ የተውጣጡና በሳምንቱ ውስጥ ልናደረጋቸውና ልንመሰክራቸው ወይም ልናውጃቸው የሚገቡ ትምህረቶችን መርሆችንና እውነቶች የያዘ ክፍል ነው። ጸሎትበዚህ ክፍል ውስጥ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከያንዳንዱ ትምህርት ጭብጥ ጋር የተያያዙትን ልመናዎች እና የጸሎቶች ዓይነቶች ምን እንደሚመስሉ ለማየት እንዲረዳችሁ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ካላቸው እና ከሚታወቁ ቁልፍ ሰውዎች ጸሎታቸው እንዲካተት ተደርጓል። የልብ ጩኸት ለጌታ ይህ በትምህርቱ መጨረሻ ላይ መጸለይ ያለብህ ጸሎት ነው። ጸሎቶች በተለያዩ መልክ ሊቀርቡ ይችላሉ። ለምሳሌ ልክ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሚገኙት መዝሙርዎች በጽሁፍ የተነደፉና በፅሁፍ መልክ ሊደረጉ ይችላሉ አልያም ደግሞ በፈቃደኝነት ወዲያው ሊደረግ ይችላል። እነዚህ ጸሎቶች ጌታ በዚህ ትምህርት ለሚያስተምረን እውነት ፀጋን ለመቀበል እና በህይውታችን እንድናዛምድ የሚያስፈልገንን የተለየ አቅም እንድንጠይቅ ይረዱናል። እነዚህ የትህትና የአቅርቦትና የመተማመን ፀሎቶች ናቸው። በመሆኑም መንፈስ ቅዱስ እንደሚመራህ በጸጥታ ይሁን በጩኸት ጸልይ፡፡
ተጨማሪ ጥናት ይህ ክፍል በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ በተማርካቸው ርዕሶች ላይ የበለጠ ለማወቅና ለማዳበር የምትፈልጉ ከሆነ ተጨማሪ ጥቆማዎችን የምንሰጥብት ክፍል ነው፡፡
ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ይህ ክፍል በቀጣዮቹ ምዕራፎች ወይም ክፍሎች ውስጥ የሚዳሰሱትን የትምህርት ይዘቶች እና ገጽታዎችን አጭር እና ግልጽ በሆነ ሁኔታ ቅድመ ዕይታን ይሰጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ የቃል ጥናት ቃሉን በልባችን ውስጥ ብንሸሽገው (ብናሰላስልውና/ ብናጠናው) በጌታ ላይ ኃጢአት አንሰራም የሚል ፅኑ እምነት አለን (መዝ. 119፡11)። ቃሉን ከልብ ማወቅ ማለት የልብ ማበረታቻ እና የጠላት ውሸቶችን ለመከላከል ዝግጁ የሚደርገን አቅም ነው፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ አንድ የማስታወሻ ጥቅስ ይዟል። ስለዚህም የተማራችኋቸውን እውነቶች ሊያስታውሳቸሁ የሚችል እና ቢያንስ በሳምንቱ እና በሚቀጥሉት ሳምንቶች ውስጥ አካሄዳችሁን ለማቅናት እንዲረዳችሁ የሚስችል ቢያንስ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ወይም ጥቅስን አካትቷል። የቤት ሥራዎች ይህ የመጨረሻ ክፍል ትምህርቱን በሚያጠናቅቁበት ወቅት እንዲሰሯቸው የተወሰኑ “የቤት ስራዎችን” ያካትታል፡፡ እነዚህ ጠቃሚ እና ተግባራዊ ስራዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሃላፊነቶች በተግባር ላይ የምታውሉ ከሆነ በቁም ነገር የምትይዙዋቸው እንዲሁም በጥልቀት እና በጥሩ ሁኔታ ለማከናወን ከፍተኛ ጥረት ካደረጋችሁ ትምህርቱን መማራችሁ በጣም ፍሬያማና ውጤታማ ያደርጋችኋል። የቤት ስራዎቹ የተዋቀሩትም ያጠኑትን ትምህረት መሰረት በማድረግ በክርስቶስ ለማደግ እንዲረዳዎት ነው፡፡ ሥለዚህ እባክዎ የቤት ስራዎትን ያጠናቁ በአፋጣኝ/ በአፅንዎት/
12 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ይከታተሉ፡፡ ይህም ከማሰብ በዘለለ ትምህረቱንና ስራዎቹን ተግባራዊ ባደረጉ ቁጥር የመማር ሂደትዎን በላቀ ሁኔታ ያሻሽለዋል፡፡
መልካሙን የእምነት ገድል መጋደል፦ ይፋ በሆነው የእግዚአብሔር ትዕይንት ውስጥ የግል ድርሻን መወጣት (የተቀደሰው መሰረት የክትትል ስርዓተ- ትምህርት) ክርስቲያን መሆን ማለት የእግዚአብሔርን ታሪክ መቀላቀል ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔር ሁል ጊዜ የሚናገረውና የሚያሳካው ታሪክ ማለት ነው! የእግዚአብሄር የመቤዠት እና የፍቅር፤ የደህንነት እና ተስፋ፤ የውጊያ እና የድል ታሪክ አሁን የእናንተ ታሪክ ሆኗል፡፡ የዚህ የተቀደሰው መሰረት የክትትል ስርዓተ- ትምህርት ታሪክ ወደ ዘመናት ጅማሬ ይመልሰንና ከዚያም በክርስቶስ የንግሥና ግዛት ወደተነገረው የከበረ መንግስት ተስፋን ይውስደናል። በጌታ በኢየሱስ በማመናችሁ ከኃጢአት ከቅጣት እና ከባርነት ነፃ ወጥታችኋል እንዲሁም በጦርነቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ ተመርጣችኋል፡፡ በዚህ የመማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ እንዴት እንደምትታጠቁ፣ የጠላት ሽንገላዎችን እንዴት እንደምትለዩ እና ከአማኞች ጋር እንዴት ማደግ እንደምትችሉ ትማራላችሁ፡፡ በዚህ ውጊያ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተመዝግበዋል ስለዚህ መንፈሳዊ ተጋድሎን እንዴት መጋደል እንዳለቦት ማወቅና የተጋድሎውም ድል ሁሉን ድል ለነሳው ጌታ መሆኑን ማወቅ ይኖረቦታል፡፡ መንፈሳዊ ውጊያን በተመለከተ ብዙ የፃፈ ፓስተር ጆን ኤልድሬጅ እንዲህ ብሏላ “”የህይወትዎ ታሪክ እርስዎ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ በሚያውቅና- በሚፈራ አካል እና በልበዎ ውስጥ የረጅምና በጭካኔ የተሞላ የጥቃት ታሪክ ነው።’’ ይላል። እግዚአብሔር በቤተሰቦቻችሁ በጓደኞቻችሁ በዙሪያችሁ ባሉትና በጎረቤታችሁ ፊት ክርስቶስን ለመወከል ስትማሩ አምላክ ለእናንተ ያደረገውን ለእናንተ የሰውርውን ርስት ምን እንደሆን ማን ያውቃል፡፡ ስልዚህ ውጊያ ማድረግን መማር አለብዎት፡፡ ይህ የክርስትና ሕይወትን እንዴት በትክክለኛው ዕይታ ማየትና መልካመን የእምነት ገድል መጋደል የሚያስችሎትን መሳሪያዎች ለመርዳት የተነደፈ “የክትትል” ስርዓተ-ትምህርት ነው፡፡ ይህ የመመሪያ መጽሐፍ “እንዴት” የሚለውን ሃሳብ ያሳይዎታል፡፡ ስቱ ዌብበር የተባለ ጡረተኛ የጦር መኮንን እና አሁን ፓስተር የሆነ አገልጋይ በክርስትና ገና አዲስ ለሆኑትም ሆን በመንፈሳዊ ውጊያ ልምድ ላላቸው ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በየእለቱ ስልሚጋፈጠው የምንፈሳዊ ውጊያ ባህሪ እንዲህ በማለት ፅፏል እያንዳንዱ ክርስቲያን የሚንቀሳቀስ የጦር ሜዳ ነው፡፡ እያንዳንዱ አማኝ በውስጡ አስፈሪ ግጭትን በጥልቅ ተሸክሞአል። እናም አብዛኞቻችን ውጊያውን እንድናሸንፍ የሚረዳን ነገር ለማግኘት ማንኛውንም ነገር እንሞክራለን። ይህንን በፈለጋችሁት ስያሜ ልትሰይሙት ትችላላችሁ፤ በስጋ እና በመንፈስ መካከል የሚደረግ ጦርንት ብለው ይጥሩት ወይም ለክርስቲአናዊ ህይወት ድል የሚደረግ ፍለጋ አልያም ያሻችሁን ስያሜ መሰየም ትችላላችሁ። ነገር ግን ይህ ቤት-አልባ- ወደታች- ጎትቶ- የሚጠል- ውጊያ ነው። እናም ሲጠናቀቅ አሁንም በጽናት ከቆሙት መካከል መሆንን ያስመኛል ወይም ትፈልጋላችሁ። የጦርነት መርሆዎች በመላው ዓለም በሚገኙ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋሞች ውስጥ ይሰጣሉ። በአብዛኛዎቹ መንገዶች መንፈሳዊ ውጊያ ከወታደራዊ ጦርነቶች ፈጽሞ የተለየ አይደለም፡፡ እያንዳንዱን ወታደር በህይወት የሚያቆየውን መርሆችን መረዳት ብቻ ሳይሆን አሸናፊ ለመሆን የሚጠበቅበትን መርሆዎች መማርና በየዕለቱ ተጋድሎ ውስጥ መተግበር ይጠበቅበታል። ምክንያቱም “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ” (ኤፌሶን 6, 12ለ)
~ Stu Webber. Spirit Warriors. Sisters, OR: Multnomah Publishers, 2001, p. 16.
መግቢያ • 13
በውጊያው ከመትረፍ በላይ ሊሰሩ ይችላሉ። ማሸነፍ ትችላላችሁ፤ በማሸነፋችሁም ክርስቶስ ይከበራል፡፡ የእግዚአብሄርን እውነት በምትማሩበት ሂደት ውስጥ እግዚአብሔር ጥበብንና ጥንካሬን እንዲሰጣችሁ ጠይቁት፡፡ የእርሱን እውነቶች ለመረዳት በሕይወታችሁ ተግባራዊ ለማድረግ ድፍረትን እና ይህንንም ለሌሎች ለማካፈል ፍቅርን እና አብርሆትን እንዲሰጣችሁ ጠይቁት። መልካሙን የእምነት ገድል ለመጋደል እርሱ ሲያስተምረን ከመንፈስ ቅዱስ ለመማር ከእኛ ጋር እንድትማሩ እንጋብዝችኋለን። በዶናስ አልሰማን ስም የኔ ተባባሪ ፀሃፊና ወታደር እንዲሁም የጠቅላላ ቲዩኤምአይ ማህበሮቻችን ለፕሮጀክቱ ጊዜና ጥረት ላበረከቱት አስተዋጽዖ ሁሉ - እግዚአብሔርን ስለእናነተ እናመሰግናለን። በእግዚአብሄር ታሪካዊ የማዳን ስራ እና ፍጥረትን ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ በሚያደረገው ታላቅ ስራ ውስጥ የእረሶን ወሳኝ ሚና ለመወጣት እንድትችሉ ከልብ የመነጨው ፀሎታችን ነው።
ወደዚህ ቤተሰብ እንኳን ደህና መጡ! ወደ ውጊያው እንኳን ደህና መጡ!
ዶ. ዶን ኤል. ዳቪስ Wichita, Kansas, Advent 2014
ትምህርት 1 ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል ታሪካችን በእግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ
በእግዚአብሄር አጠቃላይ ጥበብና ማስተዋል ለምናምን የእግዚአብሔር የተትረፈረፈ ጸጋ በእኛ ላይ ታይቷል፡፡ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ ይህም በራሱ ዓላማ የተያዘ በክርስቶስ የነበረ ነው፣ በዘመን ፍፃሜ የተገለጠ ክቡር ዕቅዱም ማለትም እግዚአብሔር በሰማይ እና በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ ጨምሮ ሁሉንም ነገሮች በክርስቶስ አንድ ለማድረግ ነው፡፡
~ ጳውሎስ ለኤፌሶን (ኤፌ 1.8-10
በዚህ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ የሚከተሉትን ዋና ዋና ሃሳቦች በማመን ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል ምን እንደሆነ እንረዳለን • የዓጽናፈ ዓለሙ አምላክ ፣ ሁሉን ቻይ ጌታ፣ እውነተኛና ዘላለማዊ አንድ አምላክ በሦስት አካላት ማለትም አብ፣ ወልድና፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እንድሆነ በማወቅ • እግዚአብሔር የሁሉ ነገሮች ፈጣሪ፣ የሚታዩትን እና የማይታዩትን እንዲሁም ሰውንም በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረ እንደሆነ በማወቅ • በሰይጣን ዓመፅ* እና በመጀመሪያዎቹን ሰብዓዊ ጥንዶች * ምክንያት ፍጥረቱ ሁሉ እንደተረገመ ነገር ግን እግዚአብሔር ክፋትን ለማሸነፍ እና ሁሉንም ነገር በአዳኙ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለማዳን ዕቅድ እና የተስፋ ቃል እንደሰጠ በማወቅ ዘለአለማዊው አምላክ አባቴ ሆይ በቃልህ እንደተናገርክ አንተ የእውቀት እና የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነህ፡፡ ይህም እውነት መሆኑን አምናለሁ፣ ውድ አባቴ ሆይ የእውነትን ቃል በትክክለኛ መንገድ ማከፈል እንድችል መለኮታዊ ጥበብ እንድትሞላብኝ እጠይቅሃለሁ (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡ 15)። እባክህ የምሄድበትን መንገድ ምራኝና አስተምርኝ (መዝሙር 32፡8) እርምጃዬንም አቅና። ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን አዘንብል አስተሳሰቤን እና ንግግሬን አቅና እንዲሁም ከስህተት በመመለስ በትክክለኛው መንገድ ምራኝ። አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን እንድትሰጠኝ እና ቃልህንም በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርት መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ እርዳኝ። በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋል ስጠኝ። ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመጥ የፈጠንሁ፤ ለመናገርና ለቁጣ የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1፡19)። የአፌም ቃልና የልቤ አሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው። ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ።
ዓላማዎች
የመክፈቻ ጸሎት-ለጥበብ
* ሰይጣን - ሰይጣን የዲያቢሎስ የግል መጠሪያ ስሙ ነው፣ የእግዚአብሔር እና የሰው ልጅ ባላጋራም ነው። *ሰብዓዊ ጥንዶች - አዳምና ሔዋን በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ከእግዚአብሄር ጋር በህብረት እንዲኖሩ፣ ትርጉም ያለው ስራን ለመስራት እና በእግዚአብሔር ፍጹም ዓለም ያለውን ሃብት እየተደሰቱ እንዲኖሩ የመጀመሪያዎቹ ወንድ እና ሴት ሆነው የተፈጠሩ ናቸው፡፡
15
16 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ፡፡ ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቅሃለሁ አሜን!
1. በዓጽናፈ ዓለም ውስጥ የምንኖር እኛ ብቻ ነንን? ብዙዎቹ የሆሊዉድ ፊልሞች አብዛኛውን ጊዜ ከአሉታዊ ወይም መጥፎ ነገሮች ጋር የተዛመዱ እንግዳና ያልተለመዱ ፍጥረቶችን ያሳዩናል። ምንም እንኳን ይህ ሕይወት የት እንደሆነ ወይም ምን እንደ ሆነ ባያውቁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዓጽናፈ ዓለም ውስጥ ብቻችንን እንዳልሆንን ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ የሰው ዘር በራሱ በጠፈር ውስጥ ካሉ የሰማይ አካላት ላይ ከሚገኙት የፀሐይ ግዑዝ ጨረሮችና የሰማይ ጋላክሲ ብቻ እንደሚኖር ያምናሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በተራ ተፈጥሯዊ ሂደቶች ሌሎች ደግሞ በመለኮታዊ* አሰራር አማካይነት የተፈጠርን ነን ብለው ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ማንም ሊያውቅ እንደማይችል አጥብቀው ይናገራሉ። ከልጅነትዎ ጀምሮ ከየት እንደመጣን በተመለከተ የእርስዎ አመለካከት ምን ነበር? ስለ ሰማይና ስለ ዓለም መገኛ ምን ዓይነት አስተምሮዎ ነበርዎት? 2. “ከዕለታት አንድ ቀን . . . !” አብዛኞቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የጨዋታ ዘፈኖቻችን ለልጆች የተፈጠሩ ተረቶችን እና የተለያዩ ታሪኮችን በቤት ውስጥም ሆነ በቤተክርስቲያን አልያም በትምህርት ቤት እየሰማን ነው ያደግነው፡፡ በዓለም ውስጥ በየትኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ታሪኮችን መስማት እና መተረክን ይወዳሉ። በፊልሞች በመጽሃፎች በኮሜዲዎች በቴሌቪዥን ትርዒቶች በዘጋቢ ፊልሞች በማህበራዊ ሚዲያዎች በጋዜጦች እና በሬዲዮ - በየቀኑ በደርዘን የሚቆጠሩ ታሪኮችን እንሰማለን፤ አንዳንዶቹ እውነተኛ አንዳንድ ሐሰተኛ ፤ አንዳንዶቼ አነሳሽ ሌሎች ደግሞ አሳፋሪዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ቅዱሳት መፅሐፍቶችን የያዘ አንድ ትልቅ ቤተ-መፅሐፍ ነው( ከ 1500 ዓመታት በላይ በበርካታ ደራሲዎች የተጻፉ 66 ቅዱሳት መፅሐፍትን የያዘ) ነገር ግን ስለ አንድ ወጥ ታሪክ - ስለ እግዚአብሄር እና እርሱ ፍጥረቶቹን ለማዳን ስላለው ፍላጎት ይናገራሉ። በአጠቃላይ ታሪኮችን በተመለከተ ምን ያስባሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ማዳኑ ወጥ ታሪክን እንደሚናገር ሰምተው ያውቃሉ? በበርካታ ታሪኮች ወይም ባነበብናቸው ታሪኮች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ልዩነቶች እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ደራሲዎች ስለ እግዚአብሔር እና ለዓለም ድኅነት የመሰጠትን ወጥ ታሪክ መካከል ምን ልዩነቶች አሉ? 3. “እስከሚገባኝ ድረስ ግልጽ የሆነ አንድ ዕቅድ አይታይኝም።” ከክርስትና እምነት ጅማሮ ማለትም ከሐዋርያት ዘመን ብዙም ሳይቆይ አማኞች መሠረታዊ የክርስትና እምነቶቻቸውን የሃይማኖት መግለጫ በሚል ስያሜ አንቀጾችን በማዋቀር እምነታቸውን በአጽንዎት አረጋግጠዋል። በታሪክ ውስጥም ሆነ እስከ ዛሬ ድረስም ከሚታውቁት እና በተደጋጋሚ ከተጠቀሱት የሃይማኖት መግለጫዎች ውስጥ የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ እና የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ዓብይና በዋናነት የታወቁ ናቸው (አባሪውን ይመልከቱ)። እነዚህ ሁለት ግልጽ የእምነት መግለጫዎች እግዚአብሔር ማን እንደ ሆነ፣ በክርስቶስ በኩል የሰራቸውን ስራዎች እንዲሁም በእግዚአብሔር ጊዜና ጥበብ አሰራር መሰረት እርሱ ፍጥረታቱን እንዴት ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንደሚመልስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታን አጠቃልለው ያቀርባሉ። ይሁን እንጂ ብዙዎቹ የማያምኑ ሰዎች ኮስሞስ (አጽናፈ ዓለም) ያለምንም ዓላማና ፈጣሪ ባጋጣሚ የተፈጠረ ወይም ወደ ሕልውና የመጣው ነው ብለው ይከራከራሉ። ሁሉንም ነገር አንድ ላይ የሚያገናኝ ምንም ዕቅድ እንደሌለ ይናገራሉ፤ እንዲሁም ይህ ለምን እንዲህ እንደሆነ፣ እኛ እዚህ ለምን እንደምነኖር የት እንደምንሄድ እና ሁሉም ነገር እንዴ ትፍፃሜን ደሚያገኝ ለማወቅ የሚረዳን አንድም ማብራሪያና ማሰርጃ ማግኘት እንደማይቻል ይከራከራሉ። ኤቲስቶች
ግንኙነት
*መለኮታዊ ፦ መለኮታዊ ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ኃይሎች ናቸው ወይም ታላቅ ኃይል ያላቸው አማልክት ናቸው።
ትምህርት 1 ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል • 17
(እግዚአብሄር አምላክ መኖሩን የሚክዱ) አምላክ እንዳለ ማመን ወይም ለሕይወት የሚሆን ትልቅ ዕቅድ አለ በሎ ማሰብና ማመን ሞኝነት ነው ይላሉ። እንዲሁም እግዚአብሔር ስለሌለ ዓጽናፈ ዓለሙ የራሱ የሆነ አሠራር ብቻ ነው ያለው፤ ለሕይወት እና ለዓለም ምንም ዕጣ ፈንታ ወይም ዓላማ የለም ብለው መከራከያ ሃሳብ ያቀርባሉ። አግኖስቲክስ (እግዚኣብሄር እንዳለ ማወቅ አንችልም ብለው የሚያምኑ) እግዚአብሔር ቢኖረም እንኳን እሱ/ እርሷ/ ነገር ይሁን አይሁን ልናውቅ አንቸልም፤ እኛ ልናደርግ የምንችለው የመጨረሻ ጥሩ ነገር - ምናልባት ነገሮች ወደ ጥሩ ይለወጣሉ ብሎ ተስፋ ማድረግ ነው! ብለው ያምናሉ። ታዲያ የሐዋርያትና የኒቂያ የሃይማኖት መግለጫዎች እግዚአብሄር እንደሌለ እና በዓጽናፈ ዓለም ውስጥ ምንም ዕቅድ እንደሌለው ለሚከራከሩ ሰዎችና ለሚሰነዝሩት ተቃውሞ ምላሽ ለመስጠት እንዴት ሊረዱን ይችላሉ? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያተኮረውን የእግዚአብሔርን እና የሰውን ዘር ታሪክ እናገኛለን። ነገር ግን ይህ ወሳኝ ታሪክ እኛ እንድናነበው የተቀመጠ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ይልቁንም እኛ የምንሳተፍበት ክፍል ነው። የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ እንደመሆናችን መጠን አሁን አዲስ ማንነት አለን እናም እርስዎም ራስዎን በሚያገኙበት በዚህ ወሳኝ ታሪክ ውስጥ የራሶን ድርሻ ይወጣሉ። ዓጽናፈ ዓለሙ የተፈጠረው በሉዓላዊና* በሥሉስ* አምላክ ነው ማለትም በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ነው። ከዘመናት በፊት በዘላለም ክብር ውስጥ የሚኖር እና ምንም የማይጎድለው እግዚአብሔር አምላክ በራሱ መልክና አምሳል የተፈጠረውን የሰውን ልጅ የፍጥረቱን ሙሉነት ሊለማመድ /ሙሉ በሙሉ ሊያገኝበት/ የሚችልበትን ዓለም ለመፍጠር መረጠ። ነገር ግን ይህ ዓጽናፈ ዓለም በዓመፀኛው መልዓክ* በሰይጣን መጣል ምክኒያት በጥፋት ተውጦ ነበር። ሰይጣን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመገልበጥ በማቀድ የመጀመሪያዎቹን ሰብዓዊ ጥንዶች (አዳምና ሔዋን) በእግዚአብሔር ላይ በማሳመፅ የሰውን ዘር በመርገም ስርና እንዲውድቁ እና የመዳንን ተስፋ አሳጥቶ እነዲኖሩ አደረጋቸው። በዚህ ዓመፅ ፊትለፊት እግዚአብሔር ይህንን ውድቀት የሚያስተካክል እና እርግማን ያስከተለውን ውጤት ለዘላለም የሚያስወግድና የሚቤዥ አንድ ድል አድራጊና አዳኝ ለማስነሳት ቆርጦ ነበር። በአብርሃም በኩል እግዚአብሔር ይህንን መሲህ (የተቀባ) ለማምጣት እና መሲሁ የሚመጣበትን ሕዝብ (እስራኤልን) ለማስነሳት ቃል ኪዳን ገባ። እናም የዘመኑ ፍፃሜ በደረስ ጊዜ እግዚአበሄር አብ ክብሩን ለመግለጥ ሕዝቡን ለማዳን እና ፍጥረቱን ለመዋጀት አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከው። ጌታ ኢየሱስም በትምህርቱና በተዓምራቶቹ አማካኝነት የእግዚአብሄርን መንግሥት ጥበብና በኃይል በሙላት ገልጧል። በመስቀል ላይ ውድ ሕይወቱን በፈቃደኝነት በመስጠቱ የኃጢአታችን* ቅጣት ከፈለ፤ የዲያቢሎስንም ስራዎች ሁሉ አጥፋ። እግዚአብሔርም ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን አስነሳው፤ ከአርባ ቀንም በኋላ ጌታም በድል አድራጊነት ወደ ሰማይ ዓረገ። ከትንሣኤው በኋላ
ይዘት
*ሉዓላዊው - በተፈጥሮና በታሪክ ጉዳዮች ላይ ቁጥጥር ማድረግ የሚችል ገደብየለሽ ወይም ልዑል ኃይልን ያመለክታል *ሥላሴ - ሦስትዮሽ - “በሶስት አካላት የተገለጠን አንድ አምላክ” የሚለውን ሃሳብ በሌላ መንገድ የመግለጫ መንገድ ነው። አንዳንድ ጊዜ “ሥላሴ” የሚለው ቃል አንድ አምላክ ነገርግን ሦስትን ብቻ ስለሚያመለክት ነው፡፡ *መላዕክት - መላዕክት ከሰው ልጆች በላይ ታላቅ ኃይል እና የማሰብ ችሎታ ያላቸው በእግዚአብሔር የተፈጠሩ ፍጡራን ናቸው። *ኃጢያት - ኃጢያት ማለት እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር በምንናገረው አልያም በምንሰራው ወይም በምናስብበት ነገር ከማድረግ መጉደል ማለት ነው። *ወደ ሰማይ መውጣት - ኢየሱስ ምድሪቱን ትቶ በአካል ተከታዮቹም እያዩ ወደ ሰማይ ሄደ። ከሞቱና ከትንሳኤው በኋላ ዕርገቱ በዚህች ምድር ድል መንሳቱንና በሰማይም እንደ ድል አድራጊ ንጉሥ በመሆን በዙፋኑ ላይ መቀመጡን ያሳያል፡፡ በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ ያሉትን ክርስቲያኖች ሁሉ ኃይልን ሊያቀዳጅ የሚችል የመንፈስ ቅዱስ መምጣትም አቀናጅቷል።
18 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
በሃምሳኛው ቀን እያደግች የነበረችውን የኢየሱስን ክርስቶስን ካምፓኒ ማለትም ደቀ መዛሙርትን* ወይም ቤተክርስቲያን* በኃይል ለማስታጠቅ መንፈስ ቅዱስን ላከላቸው። እንደ እግዚአብሔር አብ ቤተሰብ የክርስቶስ አካል እና የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ እንደመሆናችን መጠን ቤተክርስቲያን በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ሰዎችን ሁሉ በዚህ ወሳኝ ታሪክ እንዲካፈሉ ለመጋበዝ ተወክላለች። በእምነት የምናደርገው መልካሙ ገድል ሲጠናቀቅ ጊታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃዘንን በሽታን እና ሞትን የሚጠፋባትን የእግዚአብሔርን መንግሥት በመላው ጽንፈ ዓለም ውስጥ ለመመስረት ይመጣል ከሕዝቡም ጋር ለዘላለም ይነግሣል ለስሙ ክብር ይሁን! በተለይ ወደ መፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ ስንሸጋገር እነዚህ ጥያቄዎች አንገብጋቢ ሊሆኑ ይገባል ምክኒያቱም ይህን የመቀልበስ ስራው በእጥፍ ወይም በሦስት እጥፍ ሊሆን ይችላል። በእነዚያ የታሪክ መጽሐፍት እና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ታሪኮች አንድ ገፅ በገለጥን ቁጥረ ፈተናውን የመቀልበስ ስራ በተደጋጋሚ ይገጥመናል። ከመካከላችን አንዱ በሌላ ስፍራ እንደጻፋው ‘በታሪክ ወሳኝ ሁኔታዎች ውስጥ እግዚአብሔር ታላላቅ ተዓምራቶቹን በመግለጥ የራሱን ተፈጥሮ እና ፈቃዱን ሲገልጥ፤ እግዚአብሔር ድሆችን እና የተጨቆኑትን ለማዳንም ደግሞ ጣልቃ ገብቷል ማለት ነው::’ እግዚአብሄር ጣልቃ የገባባቸው ጊዜያቶችም እንዲሁ የመቀልበሻ ጊዜያቶች ናቸው፤ አንድ ሰው የሚጠብቀው ሳይሆን ያልጠበቀው ሲሆንለት በዓለም ያሉ ሰዎች እንደሚያስቡት እግዚአብሄር አላስፈላጊ መሆኑን ሳይሆን እርሱ ለዓለም በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ያምናሉ።
~ ሮናልድ ሲርደር እና ማይክል ማኪ. አስጊ በሆነው ዓለም ውስጥ ሕይወትን መስበክ ፊላዴልፊያ-ዌስትሚንስተር ፕሬስ, 1987, ገጽ 56-57.
ከጌታ ኢየሱስ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስ የታተመ ወይም የተዘጋ መጽሐፍ ነው። ክርስቶስን ማዕከል በማድረግ ያንብቡት ምክንያቱም እስከዛሬ ከተነገሩት ታሪኮች ሁሉ የላቀ ታሪክ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ ለህይወት መመሪያ ማኑዋልነት ብቻ በሚውልብት ጊዜ ዋጋን ይቀንሳል። እንደ ሐዋርያት - እና እንደ ጌታ ኢየሱስም አባባል - መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ማዕከላዊ ገጸ-ባህሪይ አድርጋን ስናነበው አስደናቂ ሆኖ የሚታይ የእግዚአብሄር ትዕይንት ነው።
~ ሚካኤል ሆርተን. ክሪስታል ክርስትና. ግራንድ ራፒድስ, ሚኢ: ቤከር ቡክቸሮች, 2008, ገጽ 142
*ደቀመዛሙርት - ደቀ መዝሙር የኢየሱስ ተ ወይም ተከታይ ነው:: እያንዳንዱ ክርስቲያን ደቀ መዝሙር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ “ደቀ መዝሙር” የሚለው ቃል ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ ለመሳተፍ የመረጣቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ለመጥቀስ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ *ቤተክርስትያን - ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ጌታ መሆኑን አምነው የተቀበሉና የሚመሰክሩ፣ ፈቃዱ በምድር ላይ የተሸከሙ፣ ያለፈውን የአሁንንና የወደፊቱን በታሪክ ውስጥ በየስፍራው በየዘመናቱ እና በምድር ላይ ያሉትን ሁሉ ያጠቃለለ የእግዚአብሔር ህዝብ ማኅበረሰብ ነው፡፡
ትምህርት 1 ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል • 19
ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል፦ ታሪካችን በእግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ ትምህርት 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ እና ከእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የተያያዙትን ጥያቄዎች አጠር ያለ መልስ ይስጡ።
1. ዓጽናፈ ዓለሙን ሁሉን የፈጠረ ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ብቻውን እግዚአሄር ነው። ዘፍጥረት 1፡1-3፡15 ን ያንብቡ።
ሀ. በዚህ ታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር ምን ድርሻ አለው?
ለ. አዳምና ሔዋን በዚህ ታሪክ ውስጥ ምን ድርሻ ነበራቸው?
ሐ. እባቡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ምን ድርሻ አለው?
2. ሁሉም የሰው ልጆች በእግዚአብሔር ፈቃድ እና ኃይል አማካይነት የተፈጠሩና የሚኖሩ ናቸው- የሐዋርያት ሥራ 17፡24-31ን ያንብቡ። ጳውሎስ ለአቴናውያን ስለ እግዚአብሔር ታሪክ በሚያቀርብበት ጊዜ የተናገራቸውን ቢያንስ ሦስት ነገሮችን ዘርዝሩ።
3. እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ በፍጥረቱ በኩል በእስራኤል ነቢያት በኩል በመጨረሻም በዘመን ፍፃሜ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ተናግሮ ነበር። ዕብራውያን 1፡1-4 ያንብቡ
ሀ. ጸሐፊው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተናገረበትን መንገድ እንዴት ይገልጸዋል?
ለ. ጸሐፊው እግዚአብሔር እኛን በጊታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሲናገረን ለዕብራውያን ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
4. እግዚአብሔር ሰው በመሆንና በምድር ላይ በመኖር ታሪኩን ተቀላቅሏል! ዮሐንስ 1፡1-14ን አንብብ።
ሀ. “ቃል” ማን ነው? ከእግዚአብሄር አምላክ ጋርስ ያለው ዝምድና ወይም ግንኙነት ምንድን ነው?
ለ. ቃል ከመላው ፍጥረት ጋርስ ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?
ሐ. በቃሉ ለሚያምኑ ሁሉ ምን ይቀበላሉ እንዲሁም እንዴት ‘ይወለዳሉ’?
20 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
5. በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ታሪክ በየትኛውም ስፍራ ለሚገኙ እና ሁሉም ሰዎች ሊነገር ይገባዋል። ማቴዎስ 28፡18-20ን አንብብ። ጌታ ኢየሱስ ለተከታዮቹ ወይም ለደቀመዛሙርቱ ምን ትእዛዝ ሰጠ?
6. ወንጌል እኛ የምንኖርበትን አስገራሚና አስደናቂ ታሪክ ጠቅለል አድርጎ የሚገልፅ የምሥራች ነው። 1 ቆሮንቶስ 15.1-8 ያንብቡ ጳውሎስ ምን ይላል?
ሀ. «ጸጋ» ማለት ምንድ ነው? ወንጌሉ (መልካም ዜው) ሁልጊዜ ለምን ስለ «ፀጋ» ብቻ ሆነ?
ለ. ወንጌል እግዚአብሔር በክርስቶስ የሰራው ስራ መለዕክት ነው። ምን ተፈጠረ?
ሐ. ኢየሱስ ሥራውን ከጨረሰ በኋላ ራሱን ለማን ገለጠ?
7. የናዝሬቱ ኢየሱስ የታሪክ- ሕይወቱ ሞቱ እና ትንሣኤው የእግዚአብሔር ታሪክ ማዕከል ነው። ማርቆስ 1፡1-13ን ያንብቡ ጌታ ኢየሱስ በተጠመቀበት ጊዜ እግዚአብሄር እንደ አባት ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ሆኖ ተገልጧል፤ የተገለጠበትን መንገድ አዛምድ።
ሀ. አባት
___ በርግበ አምሳል
ለ. ልጅ
___ ከሰማይ ድምፅ
ሐ. መንፈስ ቅዱስ
___ የናዝሬቱ ኢየሱስ
8. እግዚአብሔር በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ታሪክ በሃጢአት ለተጎዱት እና ለድሆች የመታደስ የመፈወስ እና የመባረክ ታሪክ ነው። ኢሳይያስ 61፡1-4ን ያንብቡና ነብዩ ኢሳያስ ጌታ ኢየሱስ የጠፋውን ለፈለግና ለመመለስ ሲመጣ ያደርጋቸውል በሎ የተናገራቸውን አምስት ትንቢቶችን ዘርዝሩ።
ትምህርት 1 ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል • 21
የእኔ ስም ኒ ነው። የተለመደ የቻይና ስም ነው። እንዴት ነው በዚህ ስም የተጠራሁት? እኔ አልመረጥኩትም። ይሄንን ስም ለመምረጥ ስሜ ሊሆኑ ከሚችሉ የቻይናኛ ስሞች ዝርዝር ውስጥ አልገባሁም። የሄንን ኒ የተባለውን ስሜን ለመምረጥ በእርግጠኝነት ምንም አስተወፅኦ አላደረኩም ከዚህም በላይ ለመለወጥም ምንም ማድረግ አልችልም። እኔ ኒ ነኝ ምክንያቱም አባቴ ኒ ነው ፣ እንዲሁም አባቴ ኒ ነው ምክንያቱም አያቴ ኒ ነው። እኔ እንደ ኒ ብሆን እኔ ኒ ነኝ እንዲሁም እኔ እንደ ኒም ባልሆን ያው ኒ ነኝ። የቻይናን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብሆን እንኳ እኔ ያው ኒ ነኝ ወይም በመንገድ ላይ ያለ ጎዳና ተዳዳሪ ብሆንም እንኳን አሁንም ያው ኒ ነኝ። የማደርገው ምንም ነገር ወይም ለመሆን የምሞክረው ነገር ሁሉ እኔን ኒ ከመሆን ውጪ ምንም አያደርገኝም። እኛ በራሳችን ሳይሆን በአዳም ምክንያት ኃጢአተኞች ነን። እኔ ኃጢአት ስለሠራሁ አይደለም ኃጢአተኛ የሆነኩት፤ ነገር ግን በአዳም በኩል ከአዳም ጋር ኃጢአትን ስለሰረሁ ነው ሃጢአተኛ የሆንኩት። ምክንያቱም ከአዳም ዘር ስልተወለድኩ ስለዚህ እኔም የአዳም ክፍል ነኝ። ከዚህም በላይ ይህን ለመለወጥ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም። እኔ ባህሪን በማሻሻል ራሴን ከአዳም ዘር ውጪ ማድረግ አልችልም ስለዚህ ኃጢአተኛ ነኝ። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ መሰረት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሄር ራሱን በሦስት አካላት (አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ) በአንድነት አድርጎ የገለጠ እውነተኛ አምላክ ነው። እግዚአብሔር የእርሱን ፍጥረት ከጥፋት ለማዳን ያለውን ፍቅር እና ቁርጠኝነት የሚገልጽ ታላቁን ( አስገራሚ) ታሪክ ነግሮናል። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች ከባዶ ነገር (ኤክስ ኔሂሎ) ዓጽናፈ ዓለሙን የፈጠረ ፈጣሪ እና እውነተኛውን አዳኝና መሪን የሚያስነሳበትን ሕዝብ እንደሚያነሳ በቃሉ ተናግሯል። ምንም እንኳን ህዝቡን መጀመሪያ ያለምንም ኃጢአት ቢፈጥርም እነርሱ ግን በእሱ ላይ አመፁ ከእርሱ ፀጋም* ጎደሉ፤ በዚህም ምክንያት ጠቅላላ ፍጥረት እና የሰው ዘር በሙሉ በእርግማን ስር ወደቁ ፍፃሜውም ሞትን አመጣ። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የኃጢአታችንን ዋጋ የሚከፍልና የእኛን ያለመታዘዝ ቅጣት የሚቀበል እና በእምነት አማካይነት ዘለዓለማዊ ህይወት የሚሰጠን አዳኝ ለመላክ ቃል ገባልን። የናዝሬቱ ኢየሱስ እኛን ነፃ ለማውጣት የሞተው አዳኛችን ነው። አሁን በእሱ በማመን ከኃጢአት ቅጣት እና ኃይል መዳን እንችላለን እንዲሁም የዘለአለም ህይወትን እንቀበላለን - እግዚአብሔርም የሚናገረውን ታሪክ መቀላቀል እንችላለን! ~ ዋች ማን ኒ ትክክለኛው የክርስቲያን ሕይወት. ፎርት ዋሽንግተን ፒኤ፡ ክርስቲያናዊ ሥነ ጽሑፍ ትውፊት, 1974, ገጽ 26.
ማጠቃለያ
ከዚህ በታች የሚከተሉት አባሪዎች ከዚህ ትምህርት ጋር ተያያዥነት ያላቸውና በጥልቀት ለማጥናትና ለማሰላሰል የሚረዱ ናቸው
ተጨማሪ አባሪዎች
ከዕለታት አንድ አንድ ቀን (ተጨማሪ አባሪ 1) እግዚአብሔር እየነገረን ያለው ታሪክ (ተጨማሪአባሪ 2) ከቀድሞው ጊዜ ወደ ወደ ፊት ጊዜ (ተጨማሪአባሪ 6) ጥላ እና ምግባሩ (ተጨማሪ አባሪ7) ኢየሱስ ክርስቶስ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳይና ጭብጥ (ተጨማሪ አባሪ 22)
*ከፀጋ መጉደል - አዳምና ሔዋን ከሰይጣን ጋር በማመፃቸው ምክንያት ኃጢአታቸው ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸውን ፍጹም ግንኙነት አበላሽተቷል ከእግዚአብሀርም ለይተቷቸዋል፡፡ ድርጊታቸው ከእግዚአብሔር እንዲርቁ እና ለዓለምም ሞት እንዲመጣ አድረጓል፡፡
22 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ (ተጨማሪ አባሪ 24 እና 25) የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ (ተጨማሪ አባሪ 26)
ይህ ዓለም የትዕይንት መድረክ ነው ይባላል። “ከዘመናት ግጭት” ከሚባሉት ትላልቅና አስደናቂ ታሪኮችና ክስተቶች የተሻለ ይህንን እውነትነት በግልጽ ሊያሳይ የሚችል የለም። ቅዱስ ቃሉ እና ታሪክ በግልጽ እንደሚያሳዩን በሁለት መንግሥታት መካከል የተጀመረ ጦርነት እንዳለ እና እኛም በእግዚአብሔር ዕቅድ አማካኘንተ የራሳችንን ሚና እንደምንጫውትና ተሳታፊ እንደምንሆን ያሳየናል። በመሆኑም በዚህ የእግዚአብሄርን መንግስት ዓላማ በሚቃውም ታሪካዊ ግጭት ዳራ ውስጥ ሆነው ነው የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጸሐፊዎች ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመጻፍና ለመተርጎም ጥረት ያደረጉት።
~ ጄምስ ደ ዩንግ እና ሣራ ሀሪ ከታዋቂው ባሻገር. ጌርስሃም ኦቲ: ቪዥን ሃውስ ማተሚያ 1995 ገጽ 83-84.
10ሀ ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሄር አምላክ በናዝሬቱ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ወደ ምድር መጣ በመስቀል ሞቱም የሰውን ልጆች በሙሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ (2 ኛ ቆሮንቶስ 5፡19)።
ቁልፍ መርህ
ከዚህ በታች በተመለከቱት ክርክሮች እና ጽንሰ ሐሳቦችን ያንብቡ እና ያብራሩ፤ እንዲሁም ከላይ በተማራችሁት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመመርኮዝ ተገቢውን ምላሽና ይስጡ የእርሶንም መረዳት ያጋሩ። 1. “አምላክ አለ ብዬ አላስብም” በምሳ ሰዓት ላይ ነበር ጃኒስ ከሥራ ባልደረባዋ ሊያ ጋር ዓለም እንዴት እንደተፈጠረች የሚለውን ሃሳብ ሲወያዩ ከሊያ የሰማቸው። ሊያ እግዚአብሄርም ሆነ ሌሎች አማልክት በዓለም ላይ መኖሩን የሚያረጋግጥ ምንም ማስረጃ የለም የሚል ፅኑ እምነት አላት። ሁሉም ሃይማኖቶች እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ምን ያህል አማልክት እንዳሉ እና እንደ ቅዱስ መጽሃፍት የሚቆጠሩትን በተመለከተ የተለያየ ሃሳብ አላቸው ትላለች። ጃኒስ በክርስቶስ የምታምን አማኝ ናት፤ ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሄር አብም ዓለምን እንደፈጠረ እና ያም ፍጥረት ያለ ምንም ዓላማ ወይም ትርጉም እንኳን እጅግ በጣም ቆንጆ እና ድንቅ ነው ትላለች። እናንተ ጃኒስን ብትሆኑ ከሊያ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ዓለም አፈጣጠር ምን እንደሚል አሁን ያነበቡትን የቅዱስ መጻሕፍትን መሰረት በማደረግ ትገልጹታላችሁ፡፡ ፈጣሪ ከሆነ እና ሁሉንም ነገሮች በአንድነት የሰራና የሚቆጣተር ከሆነ ለምንድን ነው ታዲያ በዓለም ላይ አሰቃቂ ነገሮች የሚከሰቱት?” አንዳንዶች እግዚአብሔር በዓለም ውስጥ ስለሚከናወኑት ነገሮች ምንም እንደማያውቅ ይከራከራሉ ሌሎች ግን እግዚአብሔር እንደሚያውቅ ቢናገሩም በሚሆኑት ነገሮች ላይ ግን ጣልቃ ላለመግባት ወስኗል ይላሉ። እስካሁን በተማራችሁትና በምታውቁት ላይ በመመርኮዝ አሁን አሁን በዓለም ላይ ስለሚሆኑት ነገሮች ለምን እንደዚህ ሆኑ ለሚለው ጥያቄ ምን ምላሽ መስጠት ትችላላችሁ? በዚህ ትምህርት ውስጥ የተማርነው ቢያንስ ለአጭር ጊዜ በችግሮች ውስጥ እንድናለፍ የምንደረገው ለምን እንደሆነ ለመረዳት ምን ያህል ይረዳናል? 2. “ እግዚአብሄር አምላክ ታዲያ ነገሮችን ለምን አሁን አይለውጣቸውም?” ከአንዳንድ አዳዲስ ክርስቲያኖች ጋር በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ የመጣ ጥያቄ ነበር። “እግዚአብሔር
የናሙና ጥናቶች
ትምህርት 1 ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል • 23
3. ወደ እግዚአብሔር የሚወስዱ ብዙ መንገዶች አልነበሩምን? በዚህ ዘመን ያሉ ብዙ ሰዎች ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል እንደሆኑና ወደ እግዚአብሄር አምላክ የሚያደርሱ ብዙ የተለያዩ መንገዶች እንዳሉ ያምናሉ። ልክ ከተራራ ግርጌ ዙሪያ ከተለያየ ቦታ በመነሳት ወደ ተራራው ጫፍ ለመሄድ የተሰባሰቡ ብዙ የተለያዩ ቡድኖች ያመለክታሉ ይላሉ። ሁሉም ወደ ተራራው ጫፍ (መለኮታዊ” ህይወት) ለመድረስ ግን በመንገዱ ላይ ባሉት የተለያዩ አቅጣጫዎች ማለተም በተለያዩ አመለካከቶች የሚመጡ ናቸው ይላሉ። በቅርብ ወይም ዘግይቶ (ክርክሩ ይቀጥላል) ሁሉም ወደ ተራራው የሚወጡ ሰዎች (የዓለም ሃይማኖቶች) ከተራራው ጫፍ ላይ መንገዳቸውን (መንፈሳዊነትና መለኮትን) ያገኙታል። በዚህ አመለካከት ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል ናቸው ሁሉም መለኮታዊውን ቃል ይናገራሉ እና ሁሉም እግዚአብሔርን ለማግኘትና ለመከተል ይችላሉ። የእኛ ጥናት ለእንደዚህ ዓይነቱ አመለካከት/ በርካታ መንገዶች አሉ ለሚለው አመለካከት/ እንዴት ሊናገርና ሊረዳ ይችላል? አሁን ግን ንስሃ በመግባት(ከኃጢአት ጎዳና በመፀፀትና በመመለስ) የናዝሬቱ ኢየሱስን የህይውታችሁ ጌታ አድርጋችኋል፤ በወንጌለም እምነት አማካኝነት ከላይ ተወልዳችኋል የእግዚአብሔርም ልጆች ሆናችኋል። ይህም ማለት ለእግዚአብሔር ክብር የሰውን ዘር ለማዳን ባለው ታላቅ ዕቅዱ ውስጥ እንድተሳተፉ ተመርጣችኋል ማለት ነው፡፡ አሁን የእግዚአብሔርን ዕቅድና ታሪክ በማንበብ ላይ ብቻ አይደለም ያላችሁት ይልቁንም አሁን ዕቅዱን ተቀላቅላችኋል! አሁን በእምነት ከክርሰቶስ ጋር ተቀላቅላችኋል እናም ኃጢያታችሁ ሁሉ ይቅር ተብሏል፤ የእግዚአብሄርም ቤተሰብ ሆነዋል ወደ እርሱ ሠራዊትም ተቀላቅለዋል። በጌታ ኢየሱስ ባመናችሁ ጊዜ የእግዚአብሄርን ታላቅ ታሪክ ተቀላቅላችኋል! በመሆኑም አሁን ስለዚህ ታላቅ ታሪክ ማወቅ ያስፈልግዎታል፤ እግዚአብሔር ምን እንደሚያደርግ እንዴት እንድትኖሩ እንደሚፈልግ እና ሌሎችን ወደ እርሱ የፍቅር እና የመዳን ታሪክ እንዲቀላቀሉ እንዴት ሊጠቀምባችሁ እንደሚችል ማወቅ ያስፍልጋችኋል። አትፍሩ! እግዚአብሔር እናንተን ለማስተማር ቅዱስ መንፈሱንና የቤተክርስቲያን ወንድሞቻችሁን ወዳጆቻችሁ እንዲሆኑና ይህን ታላቅ ታሪክ ለመኖር የሚያስፈልጋችሁን መንፈሳዊ አቅርቦትን ሁሉ ለማሟላት እንዲረዳችሁ የጸሎት ኃይል ሰጥቷችኋል። አሁን አዳዲስ ወዳጆችና እና አዳዲስ ጠላቶች አሏችሁ! እግዚአብሄር ከጨለማ ኃይልና ጉልበት አድናችኋል በመሆኑም አሁን የሰይጣንን ውሸቶች፣ የዓለምን ፈተናዎች እና የድሮ የኃጢያት ባህሪያችሁን መከልከልን መማር አለባችሁ። መዳን ማለት በሁሉም ስፍራ ለሚገኙ የሰው ልጆች ልብንና አእምሮን ለማስታረቅ የእግዚአብሔርን ወገን መሆን ማለት ነው። ነገር ግን አትጨነቁ! እግዚአብሄር የክርስትናን ህይወት እርሱን ለማስደሰትና ለማክበር እንድንኖርና በዚህ ታላቅ ታሪክ ውስጥ ጠላትን ድል ለምነሳት የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶናል። በመሆኑም እግዚአብሄር ወደ ራሱ ስላሰጠጋችሁ ልጆቹም ስላደረጋችሁና የዘላለም ህይወት ስለሰጣችሁ ጊዜ ውስዳችሁ አመስግኑት አክብሩትም። እንደ ጌታ ኢየሱስ ደቀመዝሙር (ተከታይ) ጥንካሬ እና እርዳታ እንዲለግሳችሁ መማር ማደግንና በሠራዊቱ ውስጥ እንደ ወታደር ሆኖ መቀጠል እንዲያስችላችሁ ጠይቁት። እርሱ ፈጽሞ አይተወንም አይጥለንም።
ግንኙነት
እንኳን ወደ ቤተሰቡና ወደ ውጊያው በደህና መጡ!
24 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ምንም እንኳን በአንድ ወቅት የእግዚአብሔር ጠላት ብሆንም እኔ በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠርኩና በውድቀትም ምክንያት የጠፋውን ሁሉ ለማዳን በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ለመሳተፍ የተመረጥኩ ነኝ።
ማረጋገጥ
የጌታ ኢየሱስ ጸሎት በማቴዎስ ምዕራፍ 6 ከቁጥር 9 እስከ 13 እና በሉቃስ ምዕራፍ 11 ቁጥር 2 እና 4 ውስጥ ለደቀመዛሙርቱ ያስተማራቸው ትምህርቶች ላይ በመመሥረት በቤተክርስቲያን ውስጥ ለዘመናት ጥቅም ላይ ውሏል። በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ቅዱስ ነው መንግሥተ ትምጣ ፈቃድህም መሉ በሙሉ በሰማይ እንደተፈፀመች እንዲሁ በምድርም ላይ እንድትመጣና ሙሉ በሙሉ እንዲፈጸም እንጠይቅሃለን። ለህይወታችንም በየዕለቱ እንጀራችንን ስጠን በደላችንንም ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል። ዘለአለማዊው አምላክ አባቴ ሆይ ያንተን ታላቅ ዕቅድ እና አስደናቂ ታሪክ በቅዱስ ቃልህ ስለገለፅህልኝ አመሰግናለሁ፡፡ አንተ ጽንፈ ዓለሙን ና ምደርን የፈጠርክ አንተ ሠሪዬና አምላኬ ነህ፡፡ በኢየሱስ ለሚያምኑ የተዘጋጀውን የዘላለም ሕይወት ስጦታ ለመቀበል እንድችል የመዳናንን ወንጌል ለመስማት ልቤን ስለከፈተልኝ አመሰግናለሁ፡፡ እኔ እንደወደድከኝና እንዳዳንከኝ አምናለሁ፡ ፡ የአንተን ታሪክ አካል አድርገኸኛል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እንዴት መኖር እንደምችልና - ከአንተ እንድርቅና ወደ ዓለም እንድመለስ በሚጎትቱኝ ኃይላት መካከል ፀንቼ በመቆም አንትን ከፍ ከፍ እንዳደርግ እረድዳኝ፡፡ ዛሬም አንተን ለማስደሰትእንድችል ጸጋን ስጡኝ፡፡ በኢየሱስ ስም አሜን፡ ፡
ጸሎት
የልብ ጩኸት ለጌታ
At www.tumi.org/sacredroots , ለተጨማሪ የጽሁፍ እና የቪዲዮ መርጃዎች የተቀናጀ ክፍል አለን፡፡
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
ኖርማን ጌስለር መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ኢየሱስን ፈልጉ፡፡ Eugene, OR: Wipf and Stock Publishers, 2002.
በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ወዶ ዘማችነታችን እና የሚከተሉትን አርዕስቶች እንመለከታለን 1. ኢየሱስ ሰይጣንን ድል በማድረግ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድንቀላቀል መንገድ አዘጋጀልን፡፡ 2. በንስሐ በመመለስ በእምነትና በፀጋ በኩል በክርስቶ አካል ውስጥ ውስጥ ተጠመቅን፡፡ 3. የርስታችን መያዣ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ተቀብለናል፡፡
ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ
1 ዮሐ 3.8
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥናት
1. በተለየ ወረቀት ላይ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ጠቅለል አድርገው ያቅርቡ፡፡ የሰራችሁትን የእርሶን ማጠቃለያ በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ለሚገኝ በእምነት ለጎለመሰ አማኝ ያጋሩ። 2. ተጨማሪውን “መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እንዴት ልጀምር” የሚለውን አንብብ 3. በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብ ዕቅድ ይጀምሩ
የቤት ስራ
ትምህርት 2 ወዶ ዘማችነታችን ዘመን ጠገብ በሆነው በዓጽናፈ ዓለም ግጭት ውስጥ ያለንን ሚና መቀበል
በናዝሬቱ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በእርሱ ባመናችሁበት በዚያ ቅፅበት በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤ እርሱም ሁሉን እስኪዋጅ ድረስ ወደፊት ልንቀበል ላለው ርስታችን መያዣ ነው ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።
~ ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሰዎች (ኤፌ. 1:13-14)
በዚህ ክፍልጊዜ መጨረሻ ላይ የሚከተሉትን ሃሳቦች በማውቀና በማመን እኛ ሁላችን ስለምናደረገው ወዶዘማችንት ትረዳላችሁ • ጌታ ኢየሱስ ያለ ኃጢአታ በመኖርና በእኛ ምትክ በመሞቱ ምክንያት ሰይጣንን ድል አድርጎ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምንገባበትን መንገድ አዘጋጀ፡፡ • በንስሓ (ከኃጢአታችን ወደ እግዚአብሔር በመዞር) እና በእምነት (በኢየሱስ ሥራ በማመን) በእግዚአብሔር ፀጋ እኛ በክርስቶስ አካል ውስጥ ተጠመቅን። • መንፈስ ቅዱስ ለርስታችን ዋስትና ይሆነን ዘንድ ተሰጥን። ዘለአለማዊው አምላክ አባቴ ሆይ በቃልህ እንደተናገርክ አንተ የእውቀት እና የጥበብ ሁሉ ምንጭ ነህ፡፡ ይህም እውነት መሆኑን አምናለሁ አውጃለሁም፣ ውድ አባቴ ሆይ የእውነትን ቃል በትክክለኛ መንገድ ማከፈል እንድችል መለኮታዊ ጥበብ እንድትሞላብኝ እጠይቅሃለሁ (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡ 15)። እባክህ የምሄድበትን መንገድ ምራኝና አስተምርኝ (መዝሙር 32፡8) እርምጃዬንም አቅና። ድምፅህን ለመስማት ጆሮዬን አዘንብል አስተሳሰቤን እና ንግግሬን አቅና እንዲሁም ከስህተት በመመለስ በትክክለኛው መንገድ ምራኝ። አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን እንድትሰጠኝ እና ቃልህንም በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርት መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ እርዳኝ። በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋል ስጠኝ። አባት ሆይ የማስተዋል እና የመለየትን ስጦታን ስጠኝ እናም ቃልህን በምማርበት ጊዜ በእውነተኛውና በሃሰተኛው ትምህርቶች፣ መናፍስትና ጸጋዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንድረዳ እርኝ፡፡ በመንፈስ ቅዱስህ ፈቃድህን አሳየኝ ፈቃድህንም በሙሉ ልቤ መቀበልና መያዝ እንድችል ማስተዋል ስጠኝ፡፡ የተከበርክ ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመ የፈጠንሁ ፤ ለመናገር ለቁጣ የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1.19)፡፡ የአፌም ቃልና የልቤ አሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው፡፡ ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ፡፡ ጌታ ሆይ እባክህን ለመስማት እና ለማዳመጥ የፈጠንሁ፤ ለመናገርና ለቁጣ የዘገየሁ እንድሆን እርዳኝ (ያዕቆብ 1፡19)። የአፌም ቃልና የልቤ አሳብ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራቸው። ሰው ሁሉ እውነትህ ሊረዳና ሊያተርፍበት እንዲችል እውነትህን የምናገርበትን ጥበብን ሥጠኝ።
ዓላማ
ለጥብብ የመክፈቻ ፀሎት
25
26 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
በዚህ ጥናት ቃልህንና መመሪያህን እንድቀበል አስተምረኝ፡፡ ይህንን ሁሉ ጌታዬና አዳኜ በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱ ስም እጠይቅሃለሁ አሜን!
1. “ዲያቢሎስ ለምን እኛን ይጠላናል፤ እኛ ምንም ነገር አላደረግነው አድርገናል እንዴ?” ለአዲስ አማኞች በተዘጋጅ አነስተኛ የቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ አዲስ በጊታ ያመኑ ሕፃናት ክርስቲያኖች ከመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪ ጋር የቡድን ጥናታቸውን እየተካፈሉ ነበር። በጥናቱ ወቅት የመጀመሪያዎቹ ሰብዓዊ ጥንዶች አዳምና ሔዋንን ሰይጣን በውሸትና በሽንገላ እንዴት እንዳታላቸውና ኃጢአት ሊሰሩ እንደቻሉ አወቁ። ከተማሪዎቹ አንዱ አስተማሪውን “እኔ አልገባኝም። ዲያቢሎስ ለአዳምና ለሔዋን በመዋሸት ወደ ችግር መድረስ እና ለሁሉም ነገር መደፍረስ እና መረበሽ ምክንያት ያደረጋቸው እነርሱ ምን ስላደረጉት ነው? እነርሱ በእርሱ ላይ ምን አድርገውበታል? ሰይጣን ሰዎችን በጣም የሚጠላው ለምንድን ነው? “ ብሎ ይጠይቅ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እና ስለ እግዚአብሄር ስራ ታሪክ በምታውቀው መሰረት መፅሃፍ ቅዱስ ዲያቢሎስ ሰዎችን እጅግ የሚጠላቸው፣ የሚሸነግላቸው የሚያታልላቸው መከራ የሚያበዛባቸው ለምን እንደሆነ ይናገራል? ከመጀመሪያው አንስቶ እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው? 2. “እርግጠኛ አይደለሁም ቢያነስ አሁን ባለኝ ደረጃ እኔ ሁሉንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ብዬ አልገምትም።” ማርሻ ስለ በጌታ ስለሚገኘው የዘለአለም ህይወት የምስራቹን ወንጌል ከዘመዷ ከራልፍ ጋር ሲነጋገሩ ሳታውቅ ምን ማድረግ እንዳለበት በማታውቀው ነገር ውስጥ ገባች። ራልፍ እግዚአብሄር ያዘጋጀው የዘላልም ህይወት በረከት መልካምና ያማረ እንደሆነ አምናለሁ ነገር ግን ከሃጢአት ወደ እግዚአብሔር መዞር/ መመለስ/ የሚለው ሃሳብ ግን አይመቸኝም (ምክኒያቱም ራልፍ በኢነተርኔት መርብ በሚደረግ የቁማር ጨዋታ እንዲሁም አንዳንድ አጋንንታዊ ንክኪነት ካላቸው የአዕምሮ ስነ-ጥበባዊ ተግባሮች ውስጥ ተካፋይ ነበርና)። ማርሻ ስለ ክርስቶስ ስራና ፍቅር ምስክርነትን ሲሰጥ ራልፍ እንዲህ አለ “እግዚአብሄር አምላክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮ ስለ እኛ መስዋዕት በመሆኑ እኛን ምን ያህል እንደሚወደው በእርግጥ አይቻለሁ - አስገራሚም ነገር ነው። ነገር ግን በእርግጠኝነት የምነግርህ አንድ ነገር ቢኖር አሁን ህይወቴን ለእርሱ መስጠት እችላለሁ ብዬ አላምንም፤ በተለይም ደግሞ ሁሉንም ነገር መለወጥ እና አሁን የምሰራቸውን ነገሮች መተው እንዳለብኝ ሳስብ ያ ለእኔ በጣም ከባድ ነው። ለእኔ በጌታ በኢየሱስ ማመን ብቻ በቂ አይሆንም? ለምን ከኃጢያቶቼ ንስሀ መግባትና መመለስ ግድ ይሆናል? “ለምን እንደዚህ ማድረግ ይጠበቅብኛል? እንደዚህ ላለው እጅግ የከበረ መሰጠት ዝግጁ ነኝ ብዬ አላስብም። ንስሃውን ማስወገድ አሊያም ማስቀረት የሚቻልበት ሌላ መንገድ አለ? “ ማርሻ ለእነዚህ ጉዳዮች ምላሽ መስጠት ያለበት እንዴት ነው? - ለመዳን ሲሉ ከኃጢአት ንስሀ መግባት አለብን? ያብራሩ። 3. “አሁን የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር በመሆንዎ የጠላት ዒላማ ሆነዋል።” ብዙ ሰዎች የክርስትናን እምነት እንደ እግዚአብሔር ፍቅርና ፀጋ ብቻ አድረገው ይመለከታሉ ነገር ግን ክርስትና የእግዚአብሄር ወገን ሆነን በእግዚአብሄር ጦርነት ውስጥ የምንሳተፍ መሆናችንን በጥልቀት የተርዱና የተቀበሉ ጥቂቶች ናቸው። እውነታው ግን አንድ ሰው ንስሃ ገብቶ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በሚያምንበት ጊዜ በታላቁ ጦርነት ውስጥ አንድ ክርስቲያን ጸሓፊ “የሁሉም ጦርነቶች እናት” ብሎ በሚጠራው ጦርነት ውስጥ ይገባል ወይም ጦርነቱን ይቀላቀላል። “ለክርስቶስ እና ለመንግስቱ” አዎን! ባሉበት በዚያ ጊዜ ለዚህ ዓለም ፈተናዎች ለኀጢአተኛው ባህሪያችን እና ውስጣዊ ስሜቶቻችን እንዲሁም ለጠላት ውሸት “አምቢ ወይም አይሆንም!” ማለታችን ጦርነታችን የጦርነቱ መጀመሪያ ነው። አብዛኛዎቹ እነዚህ ውሸቶች የእኛ ማንነት ቀርፀውታል እኛ በእነዚህ ሃሰቶች በህይወታችን ዘመን ሁሉ ስናምን ኖረናል። በመሆኑም ክርስቲያን መሆን የክርስቶስ ወታደር መሆን ማለት ነው የእግዚአብሔር ጠላቶችም ዒላማ መሆን ማለት ነው።
ግንኙነት
ትምህርት 2 ወዶ ዘማችነታችን • 27
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝህና ጌታህ ከተቀበልክበት ጊዜ ጀምሮ ይህ እውነት ሆኖ ያገኘኸው በምን መንገድ ነው?
ባለፈው ክፍለ ጊዜ (ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል) ውስጥ የእግዚአብሔር ድነት የሚለው ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በደንብ እንደተብራራና በህይወት ውስጥም ለሚነሱ ትልልቅ ጥያቄዎች መልስ እንዴት እንደሠጠ ተምረናል። ነገር ግን ይህ አስገራሚ የእግዚአብሄር ታላቅ ታሪክ ልክ እንደ ፊልም ወዲያው ታይቶ ለመዝናናት እና ከዚያም ለመርሳት እንደሚሆን መሆን የለበትም። ይልቁንም ይህንን ትልቅና አስደናቂ ታሪክ ማለትም እግዚአብሄር ፍጥረትን በክርስቶስ ለማዳንና ለማደስ ያለውን ሃሳብ ስንሰማ ከእግዚአብሔር ጋር ለመተባበር ውሳኔ ማድረግ አለብን። የእርሱን ታላቅ ስራ ታሪክ ምስክርነት ስንሰማ እውነት እንደሆነ መቀበል የራሳችን ታሪክ ማድረግና ከዚያም በዚህ መልካሙን የእምነት ገድል ውስጥ መሳተፍ መጀመር አለብን። መደባችንን በመለየት እና በፈቃደኝነት ወደ ጌታ ሰራዊት በመቀላቀል መልካሙን የእምነት ገድል መጋደል አለብን። በራሳችን መልካምነት ምንም የሚሆን ነገር የለንም ይልቁንም በክርስቶስ ምትክነት (“በእኛ ቦታ በመሞቱ”) በእርሱ በኩል ብቻ ለእኛ በተገለጠ በእግዚአብሄር ምህረት ሰዎች ሁሉ ወደዚህ ታላቅ ተጋድሎ እንዲሳተፉ ጥሪን እናቀርባለን። የመዳን ግብዣው ጥሪ ለጦርንት የክተት ዘመቻ ጥሪ ነው- ከጨለማው መንግሥት ወደ ብርሃን ምንግሰት ለእኔነት ብቻ ከተደረገ ኑሮ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምባሳደር ለመሆን የሚደረግ ጉዞ እንዲሁም እረሱን በዚህ በጠማማ እና በተበላሸ ዓለም ውስጥ በጽድቅና በእውነት መከተል ማለት ነው። ዓመፀኝነትህንና ኃጢአትህን በመናዘዝና ንስሐ* በመግባት ከእርሱም ምህረትንና ይቀርታን ብትጠይቅ እግዚአብሄርን በመስቀል ላይ በሞተውና ደሙን ባፈሰሰው በክርስቶስ በኩል ይቅር ይለሃል ያነፃሃልም እንዲሁም ከእርሱ ጋር ትክክለኛ ግንኙነት እንዲኖርህ ያደርጋል። የእግዚአብሔርም ቤተሰብ ወደሆነችው ወደ ክርስቶስም አካል ወደቤተክርስቲያንም ያስገባሃል። ድነትን በመቀበላችን ምክንያት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤቱን በእኛ ውስጥ አድርጓል እግዚአብሔርን ለማክበር ክርስቶስን ለማገልገል እና ሥራውን ለማከናወን በየዕለቱ ኃይል ይሰጠናል። መንፈስ ቅዱስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመለስበት ጊዜ ወደ እኛ ይዞ የሚያመጣውን የእግዚአብሔር ሙሉ ስጦታ መያዣ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ለወደፊቱ በክርስቶስ ለምንቀበለው ውርስ እንደ ዋስትና ይሆነናል። ከኃጢያት መመለስ እና በእምነት ከክርስቶስ ጋር መጣበጥ ማለት ለሰይጣን መንግሥት ካለን ታማኝነት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መመለስና መለወጥ ማለት ነው። ይህን ስናደርግ በእምነት እግዚኣብሄርን ካመኑት እና ከሚመጣው ቁጣ ለማማለጥ ከተባረኩት ሁሉ ጋር እንገናኛለን ወይም እንተባበራለን። የውኃ ጥምቀትም* ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁሉ አማኞች ያዘዘው ሲሆን ይህም መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ለሰራው የፀጋ ስራ ማለትም እኛን ጌታችንና መሪያችን ከሆነው ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ያቆራኘንና ለትንሳኤው ጌታ ያለንን ታማኝነታችንን በይፋ እና ባደባባይ የምናውጅበት ውጫዊ ምልክት ነው።
ይዘት
*ንስሀ መግባት - ማለት ሃሳብን መቀየር፣ መመለስ እና በሌላ ተቃራኒ መንገድ መሄድ እና እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ መመላለስ ማለት ነው። ንስሀ ስትገባ በተሳሳተ ጎዳና ላይ እንደሆንክ እና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ለመኖር ባህሪህን እንደምትለውጥ ከእግዚአብሔር ጋር መስማማትህን መግለፅህ ነው።
*ጥምቀት - አማኞች ወደ ክርስቶስ አካል ውስጥ እንዲገቡ ለማድረግና ለመተባበር ውሃን በመጠቀም የሚፈፀም ሃይማኖታዊ ስርዓት ነው። ይህም በውሃ ውስጥ በማጥለቅ አሊያም በራስ ላይ በማፍሰስ ሊፈፀም ይችላል። ጥምቀት የሚለው ቃል “ባፕቲዞ/baptidzo” ከሚለው ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም “ወደ ውስጥ መግባትወይም መሸፈን” ማለት ነው። ስለዚህ ጥምቀት ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም የመንፈሳዊ እውነታ ማለትም አሁን እናንተ ክርስቶስ ውስጥ እንደሆናችሁ የሚያመለክት ውጫዊና ይፋዊ መግለጫ ነው። እያንዳንዱ አማኝ መጠመቅ አለበት ምክንያቱም ኢየሱስ ሁላችንም እንድናደረገው አዞናል በማድረጋቸንም ለእሱ ያለንን ታማኝነት እናሳያለን።
28 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝ እና ጌታ መቀበል ማለት የክርስቶስን ሠራዊትን ማቀላቀል ማለት ነው። ብናውቀውም ባናውቀውም ለጦርነቱ ተመርጠዋል።
~ ጆን ዋይት “ግብግቡ’’ Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1976, p. 217
ወዶ ዘማችነታችን: -ዘመን ጠገብ በሆነው በዓጽናፈ ዓለም ግጭት ውስጥ ያለንን ሚና መቀበል ትምህርት 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ እና ከእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ጋር የተያያዙትን ሃሳቦችን አጠር ያለ መልስ ይስጡ።
1. ቃል ሥጋ ሆነ ለሚያምኑትም ዘላለማዊ መዳንን ያቀርባል። ዮሐንስ 1 10-14ን አንብብ።
ሀ. በዮሐንስ ወንጌል መሠረት ቃል የተባለው እርሱ ማን ነው? ከእግዚአብሔር አብ ጋር ያለው ግንኙነትስ ምንድን ነው?
ለ. ይህ ቃል ከመጥምቁ ዮሐንስ ጋር ያለው ግንኙነት ምን ነበር? ከዓለም ጋር ያለው ግንኙነትስ ምንድን ነው?
ሐ. እግዚአብሔር ሰዎችን የእርሱ ልጆች የመሆን መብት እንዴት ይሰጣቸዋል?
መ. የእግዚአብሔር ልጆች የምንሆነው እንዴት ነው? (ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ): i. በደም የተወለደ ወይም ተፈጥሯዊ መውለድ ii. በሰዎች ፈቃድ ወይም በባልም ውሳኔ የተወለደ iii. ከእግዚአብሔር ተወለደ
2. በእግዚአብሔር ጸጋ አማካኝነት ከኃጢአትና ከሞት መዳንን በእምነት በኩል ተሰጥቶናል። ኤፌሶን 21-10ን ያንብቡ።
ሀ. ሐዋርያው* የሰው ዘር ንስሐ ከመግባታቸውና ከማመናቸው በፊት ከሰይጣን (የአየር ላይ መንፈስ አለቃ) ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዴት ይገልፀዋል?
*ሐዋርያው - ሐዋርያ ማለት “የተላከ” ማለት ነው። ይህ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሁለት መንገድ ጥቅም ላይ ውሏል። ብዙውን ጊዜ ልክ እንደዚሁ, ቃሉ የሚያመለክተው ኢየሱስ ራሱ በምድራዊ አገልግሎቱን ዘመን አብረውት የነበሩትን 12 ደቀመዛሙርት እና እንደ ጳውሎስ ዓይነት ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 9 ውስጥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ግላዊ ተልዕኮን ለተቀበለው ነው:: የሐዋርያቱ የዓይን ምስክርነት ለእኛ ወሳኝ ነው ምክንያቱም የእነሱ ምስክርነት ስለ ክርስቶስ የምናውቀውን ሁሉ የሚገልጽ ነው (1 ዮሐንስ 1.1-4 እና 2 ኛ ጴጥሮስ 1.16-18ን ተመልከት)። ለዚህ ነው የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ እምነታችን “ሐዋርያዊ” ብሎ ሲናገር የእኛ መጽሐፍ ቅዱስ እና የሰው ታሪክን የምንተረጉመው በሐዋርያት ትምህርት ላይ መሰረት በማድረግ ነው፡፡ በሁለተኛው መንገድ “ሐዋርያ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል (ለምሳሌ ኤፌ 4:11) ይህም በመንፈስ ቅዱስ ሰጦታ ለተለየ ተግባር ወይም ተልዕኮ ለተላኩት ነው፡፡ ዛሬ እኛ “ሚስዮናውያን” ብለን እንጠራቸዋለን ማለትም ለተወሰኑ ዓላማዎች እንደ ተላኩ ለምሳሌ አብያተ ክርስቲያናትን ለመትከልና ለመሳሰሉት።
ትምህርት 2 ወዶ ዘማችነታችን • 29
ለ. የእግዚአብሔርን ምሕረት ከማቀበልዎ በፊት የነበሩ ሶስት ነገሮችን ይዘርዝሩ?
i.
ii.
iii.
ሐ. እንዴት ነው የዳነው? (ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ) i. በእምነት በኩል (እንደ እግዚአብሔር ስጦታ) ii. በራሳችን መልካምነት (ስለዚህ መመካት እንችላለን)
መ. እኛ ለምንድን ነው የዳንነው? - አሁን ድነትን ካገኘን በኋላ ጌታ እግዚአብሔር እንዴት እንድንሆንና ምን እንድናደርግ ነው የሚፈልገው?
3. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጥረትንና የሰው ዘርን በሙሉ እንደገና አዲስ ፍጥረት ለማድረግ እና ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ በሰይጣን ላይ ድልን ተቀዳጅቷል። ሉቃ 11.14-23ን አንብብ
ሀ. ጌታ ኢየሱስ ከአንዲት ብላቴና ላይ አጋንንትን ካወጣ በኋላ ከሳሾቹ ምን ብለው ከሰሱት?
ለ. በምላሹ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እርስ በእርሷ ስለምትከፋፈል መንግሥት ምንነት ምን ይጠቁማል?
ሐ. ጌታ ኢየሱስ በእግዚአብሄር ጣት (ማለትም በእግዚአብሔር መንፈስ) አጋንንትን ማውጣቱ ይህ ምንን እንደሚያመለክት ተናገረ?
መ. ጌታ ኢየሱስ በዚህ ምሳሌ ውስጥ “ኃይለኛውን” (ዲያብሎስን) ለማሸነፍ ምን መደረግ እንዳለበት ገልጿል?
ሠ. በሉቃስ 11 ውስጥ ያለው የኢየሱስ ምሳሌ በ 1ዮሐንስ 3፡8 ውስጥ ግልፅ በሆነ መንገድ ተገልጿፅል፤ ኢየሱስ በምድር ላይ የመጣበት ምክንያት ምን ነበር?
4. የናዝሬቱ ጌታ ኢየሱስ ለማዳንና ለመፈረድ ከአባቱ ዘንድ ሙሉ ሥልጣን ተሰጥቶታል። ዮሐንስ 5:9-27 ያንብቡ።
ሀ. ኢየሱስ ከአባቱ ጋር በተገናኘ የሚሠራውን ሥራ እንዴት ገለጸው?
30 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ለ. ሰዎች ክርስቶስን ማክበር ካልቻሉ ይህ ከአብ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ምን ማለት ነው?
ሐ. ጌታ ኢየሱስ ቃሉን ስለሚሰሙት ሰዎችና እርሱን ስለላከው ስለማመን ምን ብሏል?
i. __________ ሕይወት አለው
ii. __________ አይኖርም
iii. ከ ______________ ወደ ሕይወት ተላልፏል
5. ማንም ሰው በመልካም ሥራው ምክንያት ጻድቅ ሊባል አይችልም፤ እኛ ሁላችን በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ብቻ ነው ፃድቃን መሆን የቻልነው ሮሜ 3 9-28 ያንብቡ።
ሀ. የሰው ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ስላላቸው የሞራል ሁኔታ የሚገልጹባቸውን ሦስት መንገዶች ይዘርዝሩ:
i.
ii.
iii.
ለ. ጳውሎስ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ እንደሆንን የሚናገራቸውን ሦስት ነገሮችን ዘርዝሩ
i.
ii.
iii.
ሐ. ያለ ህግ መታዘዝ እንዴት በእግዚአብሄር ፊት ጻድቃን( ነፃ ናችሁ) ተብሎ ተረጋገጠ?
6. እኛ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በአዲስ ሕይወት ዳግመኛ ተወለድን። ዮሐንስ 3.1-21ን አንብብ፡፡
ሀ. ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ለመግባት ዳግመኛ መወለድ ያስፈለገው ለምንድን ነው?
ለ. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ ሰው ልጆች እንዴት እንደሚሞት ለኒቆዲሞስ ለማስረዳት ከብሉይ ኪዳን ከዘኁልቁ ምዕራፍ 21 ውስጥ ስለ አንድ ታሪክ ጠቅሷል።
ትምህርት 2 ወዶ ዘማችነታችን • 31
በታሪኩ ውስጥ ምን ምልክት ተገልጧል? ሰዎች ለመፈወስ ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? ጌታ ኢየሱስ ኒቆዲሞስን ለማስተማር ታሪክን የተጠቀመው እንዴት ነው (ቁ 15)?
መ. ባዶ ቦታዎቹን ሙላ (ቁ 15-16)
i. የሰው ልጅ ከፍ ብሎ ይሰቀል ይገባዋል ዘንድ ይገባዋል ስለዚህ_________________________ _________________________________________________.
ii. እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ ስለወደደ አንድያ ልጁን ሰጥቷል በመሆ ኑም_________________________________________________________________.
iii. ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ __________________ __________________________. እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና
7. በአንድ ወቅት እኛ የማናስተውልና የማንታዘዝ ነበርን አሁን ግን በእምነት አማካኝነት በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በኩል የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል። ቲቶ 3፡1-8 አንብብ
ሀ. እኛ በክርስቶስ ያመንን አዲስ አማኞች ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነት እንዴት ልንጠብቅ ይገባል?
i. ከገዥዎች እና ከባለስልጣኖች
ii. ከሁሉም ሰዎች ጋር
ለ. ንስሐ ከመግባታችንና በክርስቶስ ከማመናችን በፊት የነበሩትን መንገዶች ግለጽ
ሐ. ‘የአምላካችን ቸርነት እና ሰውን የመውደዱ ደግነት’ ሲገለጥልን ምን ሆነልን?
መ. አሁን በእግዚአብሔር ጸጋ ድነትን ካገኘን በኋላ እንዴት እንኖራለን?
8. ካመንን በኋላ መንፈስ ቅዱስ በሰውነታችን ውስጥ እንዲኖር በማድረግ እና የጌታ ንብረት እንድንሆንና ለምንጋደለው መልካሙ ገድል አትሞናል!
ሀ. ኤፌሶን 1 13-14ን አንብብና ባዶዎቹን ሙላ:
i. በእርሱ ስታምኑ በ _________________________ ታትማችኋል፡፡
ii. መንፈስ ቅዱስ _____________________ የእኛ ዋስትና ነው ዋስትና ነው፡፡
ለ. ሮሜ 8: 12-17ን አንብቡና ለሚከተሉት ጥያቄዎች እውነት ወይም ሐሰት በማለት ይመልሱ
32 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
i. አሁን መንፈስ ቅዱስን የተቀበልን እኛ ለኃጢያት መሰጠት የለብንም፡፡
ii. እኛ በመንፈስ አማካኝነት የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ለመሆን ተወልደናል፡፡
iii. እኛ የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
9. እግዚአብሔር በዲያቢሎስ እና በኃጢአት ላይ ክርስቶስ ያደረገውን ድል የምስራቹን እንዲናገሩ መልእክተኞችን ወደ ዓለም ልኳል። የሐዋርያት ሥራ 26፡12-18ን አንብበው ባዶ ቦታዎቹን ይሙሉ። ጳውሎስ ከኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥን ሲቀበል ጌታ ኢየሱስ ምን እንዲያደርግ ሾመው?
ሀ. ለሚያያቸው ነገሮች አገልጋይ እና _____________ (ቁ 16)
ለ. የሰዎች ዓይን ይከፍት ዘንድ ከ ___________________ ወደ ብርሃንና ወደ ከ __________________ ወደ እግዚአብሔር የኃጢአትንም _________________ በተቀደሱት መካከል ___________________ ርስትን ያገኙ ዘንድ (ቁ. 18)።
ወደ እግዚአብሄር የተመለሰ(ንስሃ) የገባና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን እንደተነሳና ጌታ እንደሆነ የተቀበለ (እምነት)ሰው ሁሉ በእሱ ድኗል - ይቅር ተብሏል በእግዚአብሄር ቤተሰብነት ውስጥ ተቀላቅሏል። ይህ የእግዚአብሄር ልጅ ለመሆን የቀረበ ጥሪ ለዚህን ዓለም እና ለኃጢአት ያለንን ታማኝነታችንን ክደን ለክርስቶስ እና ለእርሱ መንግሥት ታማኝ ለመሆን ተጠርተናል ማለት ነው። ማመን ማለት ከዚህ ዓለም ወደ እግዚአብሔር ዞር ማለት፣ ለሌላ ጌታ አዲስ መንግሥት እና አዲስ ህይወት ታማኝ መሆን ማለት ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው የሰይጣንን ሥራ ለማጥፋት የሰውን ዘር ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ትክክለኛው ግንኙነት ለመመለስ እና በቅርቡ ሲመለስ በመንግሥቱ ግዛት ስራዓት ፍጥረትን ሁሉ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንዲመልሳቸው ነው። ድነትን ያገኘነው በእግዚአብሔር ፀጋ እንጂ ለእርሱ ህግ በመታዘዛችን ወይም በራሳችን መልካም ማንነት ወይም በመልካም ስራዎቻችን ምክንያት አይደለም። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ህብረት ሊኖረን የቻለው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ምትክነት (“በእኛ ቦታ በመሞቱ”) እና በእርሱ ምህረት ብቻ ነው። አሁን ድነናል በአንፃሩ ከኃጢአት ከክፉ እና ከጨለማ መንግሥታት ጋር በመዋጋት ላይ እንገኛለን። እንደ እውነቱ ከሆነ ለመዳን የቀረበው ግብዣና ጥሪ የጌታን የተወደደው ሠራዊት ለመቀላቀል እና ከዓለም ከአሮጌው የኃጢአት ተፈጥሮ እና ከሰይጣን ጋር ለመዋጋት የቀረበም ጥሪ ነው። እኛ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ካመንን በኋላ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ መኖሪያውን እንዲያደርግ ብርታት መመሪያን እና እግዚአብሔርን ማክበርን እንዲሁም ክርስቶስን ማገልገልና የእርሱን ሥራ እንድንሰራ በመንፈስ ቅዱስ አትሞናል። መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ በሚመለስበት ጊዜ ወደ እኛ የሚያመጣውን የእግዚአብሔር ሙሉ ስጦታ ቀብድ ክፍያ (መያዣ) ነው። መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ላለን የሚመጣ ውርስ ዋስትናችን ሆኗል። የእግዚአብሔር ደጋግ ስጦታዎችና በረከቶች ማለትም የኃጢአት ይቅርታን ማግኘት ከዲያቢሎስ እና ከጨለማ መንግስት መዳን እንዲሁም የክርስትናን ሕይወት ስንኖር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመታዘዝ እንድንችል ኃይል ማግኘትን በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ በኩል እውን ሆነዋል።
ማጠቃለያ
ትምህርት 2 ወዶ ዘማችነታችን • 33
እኛ ራሳችንን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በማጣመር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንተባበራለን፣ የራሳችንን አሉታዊ አደገኛ አጥፊ እና እውነት ያልሆኑ ቃላትን መጠቀምን አቁመን በምትኩ እውነት የሞላበትና ከቅዱስ ቃሉ ጋር ተዛማጅ የሆኑትንና ትክክለኛ የሆነው ቃል እንናገራለን። እኛ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረቶች ነን እናም አሁን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስለ ቀድሞው ህይወታችን ከሁሉም በላይ ደግሞ እግዚአብሄር በውስጣችን ስላስቀመጠው ዕምቅ ችሎታችን እና ስለወደፊታችን ተስፋቸን የተፃፈውንና የተነገሩትን መንፈሳዊ እውነቶችን መቀበል አለብን። እኛ ከእንግዲህ ወዲህ በጨለማ መንግሥት ግዛት ውስጥ አይደለንም፤ እኛ የብርሃን መንግሥት ወደሆነው ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት ፈልሰናል። አሁንም የተቤዠን ውዱ ጌታችን ይህንን እውነት ደግሞ ደግሞ ይናገረን (መዝ 107፡1-3)!
ከዚህ ትምህርት ጋር ተያያዥነት ላላቸው ነገሮች ለማጥናትና ለማሰላሰል እንዲረዳችሁ የሚከተሉትን ይመልከቱው
ተጨማሪ አባሪዎች
የናዝሬቱ ኢየሱስ-የመጪው ጊዜ መገኘት (ቅፅል 4) የእግዚአብሔር ታሪክ: የእኛ ቅዱስ መሰረት (ቅፅል 5) ከቀድሞው ጊዜ ወደ ላቀ ጊዜ (ቅፅል 6) ጥላ እና አካል (ቅፅል 7)
ለተቀበሉት ሁሉ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው (ዮሐ 1፡ 12)
ቁልፍ መርህ
ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ፅሁፎች ላይ በመመርኮዝ የሚከተሉትን ክርክሮች እና ጽንሰ ሐሳቦች ከላይ በተማራችሁት መሰረት በተገቢው መንገድ ያብራሩ እና መልስ ይስጡ።
የናሙና ጥናቶች
1. “አሁን ብዙ ድል እንዳገኘሁ አይሰማኝም።” ብዙ (እጅግ በጣም ብዙ ባይሆኑም) አዳዲስ ክርስቲያኖች የክርስትና ጉዟቸውን በከፍተኛ አድናቆት ደስታና በራስ መተማመን ጀምረው የተለያዩ ተቃውሞና ተግዳሮት ሲደርስባቸው ራሳቸውን በኃጢያት እና በእፍረት ውስጥ ያገኙታል። በእንደዚያ ዓይንት ጥንካሬና ጀግንነት ጀምረው በጎዳናቸው ላይ አስደነጋጭና አንዳች ተገዳዳሪ ነገር ሲገጥማቸው የክርስትና ሕይወት “ልክ ሰባኪው ቃል እንደገባው ቀላል አይደለም” በማለት ተደናቅፈው እና ተስፋ ቆርጠው ይታያሉ። አሁንም ቢሆን በተለያዩ ፈተናዎች ይፈተናሉ፣ በቀላሉ ይቆጣሉ በኃጢያት መተላለፍ በስጋ ምኞት በስግብግብነት እና በኩራት አሽክላ ተጠለፈው ይገኛሉ። እናም ራሳቸውን እንዲህ በማለት ይጠይቃሉ “በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ ድል የት ደረስ? ለምን ጌታን ስጠራ ነገሮች በፍጥነት መልክ አልያዙም? እግዚአብሔር ከእኔ ጎን ከሆነ ለምን እታገላለሁ?” ስለ ክርስቶስ መንገድ በእንዲህ ዓይነት ግራ በመጋባት ውስጥ ላለው ሰው - በእለት ተዕለት የሕይወት ትግልና ውጥረት ውስጥ ምንም ድል እንደሌለ ለማይሰማቸው ሰዎች ምን ምክርን መስጠት ትችላላችሁ? 2. “በእውነት በእርግጠኝነት ይቅርታ እንደተደረገለኝ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?” ብዙውን ጊዜ በጌታ ያላደጉ ወይም ያልበሰሉ ክርስቲያኖች ስለ ድነታቸው /የዳኑ ስለመሆናቸው/ በተለያዩ መክኒያቶች ጥርጣሬ ይፈጠርባቸዋል። ምንም እንዃን ህይወታቸውን ወደ ጌታ ቢመልሱም በክርስቶስ ካገኙት አዲስ ህይወት ጋር የማይመሳሰሉ ነገሮችን ሲያስቡ ሲናገሩ እና ሲያርጉ ይገኛሉ። አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ዓይነት “የፍጥነት ማሰናከያ” በመንገዳቸው ላይ ሲገጥማቸው ሙሉ በሙሉ ስለመዳናቸው እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸዋል። በሁለቱም ማለትም በጥርጣሬና በፍርሀት ከተሞሉ በተደጋጋሚ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ድነትን እንደገና እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ ሊፈተኑ ይችላሉ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ በመጀመሪያ ለጌታ ንስሓ መግባታቸውንና
34 • መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደሉ
ሐጢአታቸው ከእንሱ “መወገዱን” ዋስትና ማጣት ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ሁሉም ነገር በመጀመሪያ በአዕምሯቸው ውስጥ እርግጠኛ መሆን አለመሆኑን ይጠራጠራሉ። ከዚህ በላይ ያሉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች መመርመራችሁ እና ማጥናታችሁ እንደነዚህ ዓይነት ቀስቃሽና ቀጣይነት ያለውን ጥርጣሬ የሚፈጠርባቸውን ሰዎች ችግር ለመፍታት እንዴት ሊያግዛችሁ ይችላል? አንዳንድ አዳዲስ አማኞች በእያንዳንዱ ቀን ሊገጥማቸውና ሊሰማቸው ከሚችለው የስሜት መዋዠቅ ባሻገር መዳናቸውን እንዲያረጋግጡ እንዴት ልትረዷቸው ትችላላችሁ (1 ዮሐንስ 5.11-13ን ተመልከቱ)? 3. “የሚገርም ነው። እኔ አሁን በእግዚአብሄር ጸጋ ድነት ውስጥ ስለምኖር ሁሉ ማድረግ እችላለሁ። እኔ ነጻ ነኝ!” በአንድ ወቅት አንድ አዲስ አማኝ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሄር ፀጋ ስለ ክርስቶስ ጽድቅ እና የዘለአለም ህይወት የሚሰጠውን ትምህርት ከተመለከተ በኋላ የተናገረው ነው። ትሑት እና አመስጋኝ ከመሆን ይልቅ እውቀቱን በስህተትና በዕብሪተኝነት በተሳሳተ መንገድ ተመልክቶት ድምዳሜውን አጣመመ። ይህንንም የተወላገድ መረዳቱን ከወዳጆቹ ጋር መጋራት ጀመረ “እግዚአብሔር ይወደናል እና በጸጋው አድኖናል፣ ስለዚህም ስለ እኛ አኗኗር መጨነቅ አይኖርብንም። እኛ የምናደርገውን ሁሉ እርሱ ይቅር ይለናል ይቀበለናልም። እኛ በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረን እኛ በምንሰራው ስራ መሠረት ሳይሆን በኢየሱስ በኩል ነው! ስልዚህ ስለምንኖረ ኑሮ መጨነቅ የለብንም” ይህ አዲስ ወንድማችን በክርስቶስ ያገኘነውን አዲስ ህይወት እንዴት መኖር እንዳለብን ስለሚናገረው የእግዚአብሄር ሃሳብ ጋር በተሳሳተ መንገድ የተረዳው እንዴት ነው? በጌታ ከሆንን በኋላ አሁን እንዴት መኖር እንዳለብን እውነተኛ መረዳት ምንድነው? አንድ አማኝ በእግዚአብሔር አስደናቂ ታሪክ ውስጥ ለመጓዝ የመጀመሪያው እና ትርጉም ካላቸው ነገሮች መካከል አንዱ ሁልጊዜ በከፍተኛ ሰልፍ እና በመያቋርጥ ውጊያ ውስጥ ተፋላሚ መሆናቸውን መረዳት ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ስንቀበል ምንም ውጫዊ ነጎድጓድ ወይም አካላዊ ለውጥ የለም (ቢያንስ ቢያንስ በተለምዶ!) ሁሉም ነገር እንደ ነበረ ሊመስል ይችላል። ይሁን እንጂ እውነታው ግን ሁሉም ነገር ተለውጧል። እኛ ከጨለማው ስልጣን አምልጠናል፣ ከኃጢአታችን ሁሉ ይቅር ተብለናል፣ የእግዚአበሄር ልጆች እንድንሆን አዲስ ልደትን አግኝተናል የእግዚአበሄርም ቤተሰብ ሆነናል፣ በመንግስቱ ውስጥም ለመጋደል የውጊያውን ሰራዊት ተቀላቅለናል። የእግዚአብሄ ቃለ እንደሚመሰክረው እኛ በክርስቶስ አዲስ ፈጠረቶች ነን፤ አሮጌው ሁሉ አለፏል ሁሉም አዲስ ሆኗል (2 ቆሮ 5፡17)። በመሆኑም አሁን የውጊያን/የተጋድሎ/ መንፈስን ለመላበስ ወስኑ፣ ለመንፈሳዊ ብርታታችሁ በጌታና በመንፈስ ቅዱስ ተደገፉ፣ ከክርስቶስ ጋር በየዕለቱ ስትራመዱ ለዕርዳታ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፣ እንዲሁም በልባችህ በአዕምሮአችሁን በነፈሳችህ በክፉው ቀን ሁሉን ፈፅማችሁ ለመቆም እንድትችሉ ጽኑ። እግዚአብሄር ድልን ሊሰጣችሁ ቃል ገብቷልና (1 ቆሮ 15፡57) ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካሉት ይልቅ ይበልጣልና (1 ኛ ዮሐንስ 4፡4)። አሁን እናንተ ለጌታ ናችሁ በመሆኑም በስጋቶች በውሸቶችና በማጭበርበሮች ከተሞላው ከቀድሞው ህይወታችሁ ጋር ራሳቸሁን ማዛመድ የለባቸሁም። እናንተ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት በመሆን የእግዚአብሔር ልጅ ሆናችኋል እናም ሆን ብላቸሁ በዚህ በአዲሱ ማነነታቸሁና ልጅነታቸህ እንደ አዲስ ሰው ማሰብ መንቀሳቀስ እና መናገር ጀምሩ። እራችሁን በተዕግስት ተብቁ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን አዳዲስ መንገዶች መማርና እግዚአበሄር እንድትሆኑ የፈለገውን አዲስ ሰው መሆን ትዕግሰትና ጊዜ ይወስዳልና።
ማዛመድ
በዚህ አዲስ ማንነት ውስጥ ለመኖር እንዲረዳችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁት፤ ይህ እግዚአብሔር የሰራው አዲስ ማንነት ካለፈው ካሮጌው ህይወት ምኞት ነፃ የወጣ፣ በአዕምሮአችሁ መታደስ
Made with FlippingBook - Online magazine maker