Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition

ቅዱስ መሰረቶች የከተማ አገልግሎት ተቋም /TUMI/ ዋና ዋና የክርስትና የእምነት መግለጫዎችን ልምምዶችንና የቤተክርስቲያን ጉባዔዎችን ለመግለጽ የሚጠቀምበት ስያሜ ሲሆን፤ ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ100 እስከ 500 ዓመታት ያሉትን የክርስትናን ማዕከላዊ እምነት ያቀፈ ሲሆን ይህም የመጀመሪያውን ቅጅ ደንብን፣ አምልኮን፣ የሐይማኖት መግለጫዎችን እና አስተምሮን ጨምሮ ያካተተ ነው። የከተማ አገልግሎት ተቋም የከተማ ቤተ ክርስቲያኖች እነዚህን መንፈሳዊ መሰረቶች (አንዳንድ ጊዜ ታላቁ ትውፊት ወይም ባህል ተብሎ ይጠራል) ፈልፍሎ በማውጣት ለመንፈሳዊ ተሃድሶና ለሚስዮናዊ ጥንካሬያቸው እገዛን ለማድረግ የዋለ ነው።

ይህ ተግባራዊ ጠቃሚ እና አጋዥ ሃብት/መጽሐፍ/ በተለይ አዲስ እና እያደጉ ያሉ ክርስቲያኖችን ውጤታማ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት (የእምነት አርበኞች) እንዲሆኑ ለመርዳት የተነደፈ ሲሆን ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተነገረው ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ የተገነባ ነው። የኤፌሶን መጽሐፍ ርዕሰ ጉዳይን ንድፍ ከግምት በማስገባት ይህ የማስተማሪያ

መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ አማኞች በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ታሪክ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ቁልፍ ገፅታዎች ምን እንደሚመስል በዘጠኝ ትምህርቶች እንዲረዱት ይረዳቸዋል። እነዚህ ጥናቶች በእግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ የእኛን ድርሻ እንዴት እንደምናከናውን፣ በመሰረታዊ የክርስትና እምነት እና ምልልስ ተማሪዎች የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑና፤ ሌሎችንም ደቀመዛሙርት እንዲያደርጉ የሚያስችላቸውን ቁልፍ ነገሮች ይዘረዝራል። ይህ መጽሐፍ ለከተማ አገልግሎት ተቋም ለካፒስቶን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የሥርዓተ ትምህርት ዋና ማሰልጠኛ ሆኖ የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ዋና መሪ ሃሳቦች እና መሠረታዊ የክርስቲያን ደቀመዝሙርነት መርሆችን በማቅረብ ያገለግላል።

የትምህርቱ ርዕሶች 1.

ራሳችንን የምናገኝበት የህይወት መድብል፦ የእኛን ታሪክ ከእግዚአብሔር ታሪክ ጋር ማስተሳሰር 2. ወዶ ዘማችነታችን፦ -ዘመን ጠገብ በሆነው በዓጽናፈ ዓለም ግጭት ውስጥ ያለንን ሚና መቀበል 3. የምናገኘው መግቢያ : - ህይወታችንን በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ህይወት ጋር ማያያዝ 4. የተቀበልነው ስጦታ: -በመልካሙ የእምነት ተጋድሎ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ሚና 5. የምናሳየው ልዕቀት: - በዚህ ዓለም እንደ እግዚአብሔር ቅዱሳን እና የክርስቶስ አምባሳደሮች መኖር

6. የምንፈለገው መታነጽ: - በክርስቶስ አካል ውስጥ እርስ በእርስ መተናነጽ 7. የምንዋጋው ጠላት: - በእግዚአብሔር ጠላቶች ላይ በድል መመላለስ 8. የምንጠቀመው መሣሪያ: - የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ መልበስ 9. የምናሳየው ጽናት: - የቅዱሳን ጽናት

ለበለጠ መረጃ ፣ ተጨማሪ ቅጂዎች እና ሌሎች ታላላቅ መገልገያዎች በ www.tumistore.org ይጎብኙ

www.tumi.org www.worldimpact.org

የከተማ አገልግሎት ተቋም የዓለምዓቀፍ ተጽዕኖ አገልግሎት ድርጅት ነው.

Made with FlippingBook - Online magazine maker