Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 0 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ክርስቲያን ሚሽን እና ከተማ
ት ም ህ ር ት 3
የትምህርቱ አላማዎች
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ ካነበብክ፣ ካጠናህ፣ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • የከተማን ጽንሰ ሀሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ በመነሳት ትርጓሜ መስጠት ትችላለህ፡፡ ይህም ከተሞች በቅጥሮች ውስጥ የሚገኙ የቤቶችና የህንጻዎች ስብስብ፣ በዘመናቸው በጣም ጠቃሚና አስደናቂ፤ እና አንዳንዶቹ ደግሞ ለአቅርቦትና ለጥበቃ በሌሎች ላይ ጥገኛ እንደነበሩ መናገር ትችላለህ፡፡ በጥንታዊው አለም ከተሞች በአንጻራዊነት አነስተኛ፣ ንጣፍ የሌላቸው፣ በወፍራም ግርግዳዎች እና ከፍ ባሉ ማማዎች የተጠናከሩ እና የመንግስት እና የባለስልጣናት መቀመጫዎች ነበሩ፡፡ • የከተማን መንፈሳዊ ትርጉም ማለትም ከተሞች ከሰው አመጽ እና ምንዝር (ሄኖክ፤ የቃየን ከተማ)፣ ከነጻነትና እብሪት (በባቤል ግንብ እንደሆነው)፣ ክፋትና አምላክ አልባነት (እንደ ባቢሎን) ጋር የተዛመዱበትን መንገድ ማስቀመጥ ትችላለህ፡፡ ከተሞች በሃጥያታቸው ምክንያት በእግዚአብሔር ይፈረድባቸው ነበር (ለምሳሌ ሰዶምና ገሞራ፣ ኢያሪኮና ነነዌ)፤ እንዲሁም በሃሰተኛ የደህንነትና የኃይል ስሜታቸው ይወገዙ ነበር (በተለይም ኢየሩሳሌም)፡፡ • እግዚአብሔር ከተማን እንደ መኖሪያውና የበረከት ስፍራው የወሰደበትን ምስል ማሳየት ትችላለህ፤ ይህም ማለት ኢየሩሳሌምን ለራሱ መምረጡና በምድር ላይ ለምስጋና እንድትሆን መወሰኑ ነው፡፡ ከዚያም ባሻገር የአመጻን ምስል ወደ መሸጋገሪያ ምስል (ማለትም የመማጸኛ ከተሞች)፤ እና የእርሱን ይቅር ባይነት እና በረከት ማወቂያ እና መለማመጃ ቦታ (ዮናስና የነነዌ ተሞክሮ) በማድረግ ውስጥ የእግዚአብሔርን አሰራር ማሳየት ትችላለህ፡፡ • ከእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት የተነሳ በፍርዱ ፊት ለሚመለሱና በቅጣቱ ፊት ምህረቱን ለሚሻ የትኛውም ከተማ እንዴት ተስፋ እንዳለ በዝርዝር መረዳት ትችላለህ፡፡ • ዛሬ ባለውየሚሽን እንቅስቃሴውስጥኧርባንሚሽን ቅድሚያ የሚሰጠውጉዳይ የሚሆንበትን ሶስት ወሳን ምክንያቶች መስጠት ትችላለህ፡፡ ይህም እነዚህን ያጠቃልላል:- ከተማ በአለም ውስጥ እንደ ተጽዕኖ፤ ኃይልና መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች መቀመጫ፣ ለተጠቁ፣ ለተጨቆኑና ለድሆች እንደመሸሸጊያ በመሆን እንደ መንፈሳዊ መዳረሻችንና ርስታችን ይታያል፡፡ • የኢየሱስ አገልግሎት ራሱ በከተማ ስራ ላይ እንዴት እንደተመሰረተ ማሳየት ትችላለህ፤ መንግስቱን የመስበክ ስራው ኢየሩሳሌም ውስጥ ነው፡፡በተጨማሪም ክርስትና በአንድ ከተማ ውስጥ ተወልዶ እንዴት በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በሮማ ግዛት ውስጥ በነበሩት ታላቅ ከተሞች (እንደ ደማስቆ፣ አንጾኪያ፣ ፊሊጵስዮስ፣ ተሰሎንቄ፣ አቴናና ሮም) እንዴት እንደተስፋፋ ትረዳለህ፡፡ ሐዋሪያዊው አግልግሎትም (የጳውሎስን ጉዞዎች ጨምሮ) በባህሪው ከተማ ተኮር ነው፥ ከተሞች ወደ ታላቋ የሮማ ግዛት መግቢያ በሮች ነበሩ፡፡
3
Made with FlippingBook - Online catalogs