Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 0 6 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

• ዛሬ ስላሉ ዋና ዋና የትምህርት ማእከላት መጠን፣ ስፋትና የህዝብ ብዛት ጠቅለል ያለ ግንዛቤ ይኖርሃል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ከተሞች የመንግሥት፣ የትምህርት፣ የጤና ክንካቤ፣ መረጃ፣ የመዝናኛ፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ የህግ፣ ወታደራዊና የሃይማኖት ተቋማት ማዕከል በመሆን እንዴት እንደ ሚያገለግሉ ትረዳለህ፡፡ ከተሞችን ከሚሰጡት አግልግሎት በመነሳት እንደ የባህል ከተሞች (አለምን በፋሽን የሚመሩ)፤ የፖለቲካና የአስተዳደር ከተሞች (አለምን ውሳኔ በመስጠት የሚመሩ) አካላት ወይም የመንግስታትና የጽህፈት ቤቶቻቸው መቀመጫ)፤ የኢንዱስትሪ ከተሞች (ረብሻ የበዛባቸው የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ማዕከላት)፤ የንግድ ከተሞች (አለም አቀፍ ግብይቶች የሚካሄዱባቸው ግዙፍ ባዛሮችና የገበያ ማዕከላት)፤ ታሪካዊ ከተሞች (ታላላቅ ታሪካዊ ትግሎች፣ ድሎችና ክስተቶች የተከናወኑባቸው)፤ እና ዋና ከተሞች (እነዚህን ባህሪያት ሁሉ አንድ ላይ የያዙ) መሆናቸውን ትረዳለህ፡፡ • እግዚአብሔር ለድሆች ስላለው ልብ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ በመነሳት በአሁን ወቅት ከተሞች ለተጠቁት፣ ለተጨቆኑት እና ለድሆች እንዴት እንደ መሸሸጊያ እንደሚያገለግሉ ማስቀመጥ ትችላለህ፡፡ ሌላው ደግሞ “እግዚአብሔር ስለ ድሆች ግድ የሚለው ከሆነ አሜሪካ ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና በድህነት ስለሚሰቃዩት ከተሞች ግድ ይለዋል ማለት ነው” ስለሚለው ክርክር ግንዛቤ ትጨብጣለህ፡፡ • ከተማ እንዴት የመዳረሻችንና የርስታችን ምስል እና ምሳሌ እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች በመነሳት ማጠቃለያ መስጠት ትችላለህ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ስለሚገኝባትና ኢየሱስም እንደ ሁሉ ጌታ የሚደነቅባት አዲሲቱ ኢየሩሳሌምን እንዲሞሉ ነው የእግዚአብሔር የመጨረሻ የከተማ ተሀድሶ ፕሮጀክት)፡፡ • የኧርባን ሚሽን ማዕከላዊነትን አንድምታዎች መጠቆም ትችላለህ፤ ይህም ማለት በሁሉም የሚሽን ስራዎቻችን፣ በጸሎታችን፣ በመስጠታችን፣ በመላካችን ሁሉ ከተሞች ላይ ትኩረት ማድረግ ይኖርብናል፡፡ በርካታ ሰራተኞች የከተማ መኸር ላይ እንዲሰማሩ ማዘጋጀት አለብን፤ ያልተደረሱ ከተሞችን ለመድረስ ስትራቴጂ መንደፍ ያስፈልገናል። ከዚህም ባለፈ ለከተሞች ደህንነትና ጥበቃ መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ከተማን አዘጋጅቶልናል ዕብራውያን 11፡8-16 - “አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና። ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ስለዚህ ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ እንደማይቈጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው ከአንዱ ተወለዱ። እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ

3

ጥሞና

Made with FlippingBook - Online catalogs