Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 0 7
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤ አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና።” እዚህ ላይ የተጠቀሰው ታላቁ “hall of faith” አንዱን የአዲስ ኪዳን ከፍታ ይወክላል፤ አማኞች ሁሉ በክርስቶስ በማመናቸው እርስ በእርሳቸው ስላላቸው እንድነትና ትስስር ይናገራል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ በየትኛውም የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎችን እርስ በእርሳቸው የሚያስተሳስራቸው የተስፋና እምነት፣ የእግዚአብሔርና የእርስ በእርስ ፍቅር፣ በግልም ሆነ በጋራ የእግዚአብሔር ተስፋ ለእያንዳንዱ የመፈጸሙን ተስፋ በእምነት መጠባበቅ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ክፍል፥ በዕብራውያን 11 እምነት ከተሻለች አገር አንጻር ተተርጉሟል፤ ያለሃፍረት ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት የምናደርግባት ሰማያዊት ሀገርና ከሰሪዋ ጋር የምንኖርባት ከተማ፡፡ እግዚአብሔር በየዘመናቱ ለተነሱት ቅዱሳን ከተማን ማዘጋጀቱ ያስደንቅሀል? ዛሬ ለብዙ ክርስትያኖች ከተማ ማለት የሚያስጨንቅ፣ የሚያስፈራና የማይማርክ ስፍራ ነው፡፡ በጣም የተወሳሰበ፣ የተጨናነቀ፣ ህዝብ የበዛበት፣ ጫጫታ የነገሰበት፣ በንግድ፣ በትራፊክ እንቅስቃሴ፣ በወንጀልና በኢ-ስነምግባራዊነት የተሞላ ስፍራ ነው፡፡ ታዲያ በየዘመናቱ ለተነሱት ቅዱሳን ለዘላለም መኖሪያነት እግዚአብሔር ለምን እና እንዴት ከተማን ለመገንባት ፈለገ? ይህ ጥሩ ጥያቄ ነው ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የተሻለ ምላሽ አለው! በመጀመሪያ እግዚአብሔር ለራሱ መኖሪያን ማዘጋጀቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም የሚወደድና በአዱስ ኪዳን ደግሞ ጎልቶ የሚጠቀስ ሀሳብ ነው፡፡ በበጎቹና በፍየሎቹ ፍርድ ወቅት ኢየሱስ ንጉሱ በቀኙ ላሉት አለም ከመመስረቱ አንስቶ እግዚአብሔር አብ ወዳዘጋጀላቸው መንግስት ይገቡና ይወርሱ ዘንድ ያውጃል (ማቴ25፡34)፤ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ እንዳይፈሩ አዟቸዋል፤ እግዚአብሔር መንግስቱን ለእነርሱ በመስጠት ደስ ይሰኛልና (ሉቃ12፡32)፤ ደግሞም በአባቱ ቤት ብዙ መኖሪያ እንዳለና እነርሱም ከእርሱ ጋር ይኖሩ ዘንድ መኖሪያን እንደሚያዘጋጅላቸው ተስፋን ሰጥቷቸዋል (ዮሐ14፡1-4) ጳውሎስ ለፊሊጵስዩስ ሰዎች የአማኞች ዜግነት ሰማያዊ ነው፥ ሁሉን በሚገዛው ኃይሉ ደካማ አካሎቻችንን ከክብሩ ሰው ጋር እንዲያስማማሊያደርግ የሚችለውን አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስንም የምንጠባበቀው ከዚያው ነው (ፊል 3፡20-21)፡፡ በእውነቱ የክርሰትያን ተስፋ እግዚአብሔር የእርሱን ማዳን ለሚወርሱ ሁሉ ቦታ የማዘጋጀቱ ሃሳብ ሲሆን ይህም ሃሳብ በሚያስደንቅ ሁኔታ አንደከተማ ተገልጧል፡፡ በተጨማሪም ማንም ክርስቲያን ስለ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም ያለመደነቅና ያለመጠባበቅ ሊያነብብ አይችልም፡፡ አብና ወልድ የሚኖሩባት፣ በጥሩ ወርቅ የታነጸች አንጸባራቂ ከተማ ናት፤ የጌታ ግርማ ስለሚያበራላት ከተማዋ መብራት አያስፈልጋትም፡፡ በእግዚአብሔር በራሱ ግርማ ውስጧ የታነጸችን ከተማ ማን ሊገነዘባት ይችላል፤ የመቃብር ቤት ወይም ስፍራ የሌለባት (በዚያ ሙታን ስለሌሉ) ሆስፒታል ወይም መድሃኒት ቤት የሌለባት (በዚያ ህመም ስለሌለ)፣ ፍርድ ቤት ወይም እስር ቤት የሌለባት (በዚያ ወንጀል ስለሌለ)፣ እና የአዕምሮ ሀኪም ወይም የስነ ልቦና አማካሪ የሌለበት (በዚያ ሀዘን ስለሌለ) የከተማዋ ስፋት ከተራ ቦታ ይልቅ እንደ ጨረቃ ያደርጋታል (የዮሐንስን መለኪያዎች ቃል በቃል ከወሰድን 1500 ማይልስ ካሬ ነው)፣ የጠፈሩ መሀንዲስ በሆነው በጌታችን ኢየሱስ እጅ የተራች ነች፡፡ እንደ ስነመለኮት ምሁርነቴ ጌታችን አናጢ ስለነበረ በእርሱ ተቀይሳ የምትገነባ ነች ከቃላት በላይ እጅግ አስደናቂና ከአዕምሮ በላይ እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡
3
Made with FlippingBook - Online catalogs