Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 0 8 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ይሁን እንጂ ከተማዋ እነዚህ ሁሉ አስደናቂ በረከቶች ቢኖሯትም፥ በጣም የሚያስደንቀው ነገር አሁን የእግዚአብሔር ማደሪያ በሰው ልጆች ዘንድ መሆኑ ነው፡፡ ራዕይ 21፡1-4 - “አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም። ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ። ታላቅም ድምፅ ከሰማይ፦ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።” ይህችን ከተማ በጣም ተፈላጊ፣ እጅግ የከበረች እና በጣም አስደናቂ የሚያደርጋት እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር አብሮ የሚኖርባት መሆኑ ነው፤ እርሱ አምላካቸው ይሆናል እነርሱም ህዝቦቹ ይሆናሉ፡፡ እንባዎች ሁሉ ይታበሳሉ፣ ሞት ይወገዳል፣ ልቅሶና ህመምም እንዲሁ፣ የቀደመውም ዓመፃና ጭካኔ ሁሉ ለዘላለም ይወገዳል፡፡ ከዚህ የበለጠ ምን አስገራሚና ተፈላጊ ሊሆን የሚችል ነገር ይኖራል? ከተማዋ በመጀመሪያ የአመጽና የጣዖት አምልኮ ስፍራ መሆኗ አዲሲቷን ኢየሩሳሌምን ይበልጥ አስደናቂ የሚያደርጋት ዕውነታ ነው። የሰማዩ አምላክ ክፉውን ከተማ ተቀብሎ ወደ ገነትነት ራሱ ይለውጠዋል ብሎ የሚያስብ ማን አለ? የአምላካችን ጥበብ እና እውቀት የማይመረመርና ከመረዳት ያለፈ ነው (ሮሜ11፡34)! ለሰው ልጆች የሁሉም ነገር ፍጻሜ ከተማ መሆኑን ለማሰላሰል ጊዜ ውሰድ - በእርሱ ንድፍ የተሰራችና በመገኘቱ ያለልክ የበለጸገች ከተማ፡፡ የዘመናት ሁሉ የቅዱሳት ተስፋ የእግዚአብሔርን ከተማ መውረስ ነው፡፡ ዕብ 11፡10 - “መሰረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሰራትንና የፈጠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና፡፡” መለኮታዊው አናጺ ለራሱ ለዘላለም የሚኖርባትን ከተማ የመገንባቱን ታላቅ ስራውን እያጠናቀቀ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ትርጉም የሚሰጥ ወይም የሚያስደንቅ ነገር ይኖራልን? ከእርሱ የበለጠ የጥበብ፣ የውበትና የልቀት ስሜት ያለው ይኖራል? ጥበቡን በጽጌረዳ ወይም ጥድ ዛፍ ላይ የሚገልጥ እርሱ ለእኛ ስለሚሰራው አስደናቂ ስፍራና ስለግንባታው እንዴት እርሱን ማመን ይከብደናል? እግዚአብሔር የቀየሳትና የገነባትን ከተማ በመጠባበቅ ዛሬም ከተማ ላይ እንስራ፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ከተማን አዘጋጅቶልናል፡፡ ዕብ 13፡14 - “በዚህ የምትኖር ከተማ የለችንምና፥ ነገር ግን ትመጣ ዘንድ ያላትን እንፈልጋለን፡፡”

3

Made with FlippingBook - Online catalogs