Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 1

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

1. የመረጥከው የንባብ ክፍል ዋና ጭብጥ ወይም ሃሳብ ምን እንደሆነ ለይተህ አስቀምጥ። 2. የምንባቡን ዋና ትርጉም በአጭሩ ግለጽ (ይህን በሁለት ወይም በሶስት አንቀጽ ልታስቀምጠው ትችላለህ ወይም ደግሞ በእያንዳንዱ ቁጥር አጫጭር ማጣቀሻ ወይም ማመሳከሪያ እየተጠቀምክ መሄድ ትችላለህ።) 3. ይህ የምንባብ ክፍል ሊሰጠን የሚችሉ ከአንድ እስከ ሶስት የሚደርሱ የክርስቲያን ሚሽን መርሆዎችን ዘርዝር። 4. ከመርሆዎቹ ውስጥ አንዱ፣ የተወሰኑት ወይም በጠቅላላው ከሚከተሉት ነጥቦች ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ አሳይ፥ ሀ. ከአንተ የግል መንፈሳዊ ህይወት እና ከጌታ ጋር ካለህ ጉዞ ጋር ሐ. ባለህበት ማህበረሰብም ሆነ በጠቅላላው ህብረተሰብ ውስጥ ከሚንጸባረቁ ሁኔታዎችና ችግሮች ጋር የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ እና ማጣቀሻዎችን እንደ መመሪያና እንደ መርጃ ለመጠቀም ነጻነት ይኑርህ፤ ይህን በምታደርግበት ወቅት ግን የሌላን ሰው ምልከታ ከተዋስክ ወይም በዛ ምልከታ ላይ የራስህን ከመሰረትክ ለባለሃሳቡ ዕውቅና መስጠትን መዘንጋት የለብህም። ለዚህም የጽሁፍ ውስጥ ማጣቀሻዎችን፣ የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ ወይም የመጨረሻ ማስታወሻዎችን ተጠቀም። የተጠቀምከው የማስታወሻ ዘዴ ተቀባይነት የሚኖረው 1) በጠቅላላው የጽሁፍ ስራህ ውስጥ ወጥነት ያለው ሲሆንና 2) የተጠቀምከውን የሌላን ሰው ሃሳብ በትክክል የሚያመለክት ሲሆንና ተገቢውን እውቅና ሲሰጥ ብቻ ነው ፡፡(ለተጨማሪ መረጃ ከአባሪዎች ገጽ ላይ Documenting Your Work : A guide to Help You Give Credit Where Credit is Due ተመልከት ፡፡) የትርጓሜ ጥናቱ (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክቱ) የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን አረጋግጥ:- • በአግባቡ መጻፉን(ታይፕ መደረጉን) • ከላይ ከተሰጡት ምንባቦች የአንዱ ጥናት መሆኑን • ሳይዘገይ በቀኑና በሰኣቱ ገቢ መደረጉን • ርዘመቱ 5 ገጽ መሆኑን • ከላይ የተሰጠውን መመሪያ ተከትሎ መሰራቱንና አንባቢው በቀላሉ ተከትሎ ሊረዳው የሚችል መሆኑን • ምንባቡ ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ያላቸውን ዝምድና የሚያሳይ መሆኑን እነዚህን መመሪያዎች አይተህ አትደናገጥ፤ ይህ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት ነው፤ ማድረግ የሚያስፈልግህ ምንባቡን በደንብ ማጥናት፤ ከምንባቡ ውስጥ ትርጉም መፈለግ፤ ከዚያም ቁልፍ የሆኑ መርሆዎችን ከምነባቡ ማውጣት እና መርሆዎቹንም ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ማዛመድ ናቸው፡፡ ለ. በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ካለህ አገልግሎት ጋር

Made with FlippingBook - Online catalogs