Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 0 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

የኤክሴጄሲስ ፕሮጀክት(የመ.ቅዱስ ክፍሎች ትርጉም) በካፕስቶን ፋውንዴሽን የክርስቲያናዊሚሽን የጥናትሞጁል ተሳታፊ እንደመሆንህ መጠን ከሚከተሉት ንባቦች በአንዱ ላይ የክርስቲያን ሚሽን እና የከተማ አገልግሎት ምንነት ላይ ኤክሴጄሲስ (ኢንደክቲቭ ጥናት) እንድትሰራ ትጠየቃለህ።  ማቴ 28.18-20  A2 ቆሮንቶስ 6.1-10  ሉቃስ 4.16-22  A2 ጢሞቴዎስ 4.1-5  ማቴዎስ 5.13-16  ቆላስይስ 1.24-29 የዚህ የትርጓሜ ፕሮጀክት (እክሴጀሲስ) ዓላማ ስለ ክርስቲያናዊ ሚሽን ምንነት እና አሠራር የዋና ምንባብ ዝርዝር ጥናት ለማካሄድ እድል ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሚሽነሪ አምላክ መሆኑን ማየት ለእያንዳንዱ የከተማ አገልግሎት ደረጃ መሠረታዊ ነው፡፡ ሚሽን ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ወደ ባህር ማዶ ሄደው ለተወሰነ ወቅት ብቻ የሚሰሩት ሥራ አይደለም፡፡ ይልቁንም ሚሽን እግዚአብሔር በዚህ ምድር ላይ የሚሰራው ስራ እስትንፋስና የአይሁድ-ክርስቲያናዊ የዓለም ምልከታ መሰረት ነው። በአንድ በኩል ጠቅላላው የክርስትና ታሪክ እግዚአብሔር የርሱ የሆኑትን ከአለም ወደራሱ ለመሳብ ያደረገውን መመልከት እንችላለን፤ ሚሽን የኛ ስራ የመሆኑን ያህል የእግዚአብሔርም ስራና የልቡ ፈቃድ ነው። የዚህ ጥናት ዓላማ አንተ ከላይ ከተጠቀሱት ፅሁፎች አንዱን በመምረጥ ስለ ሚሽን - መሠረቱን ፣ አሰራሩን እና ለከተሞች ክርስቲያናዊ አመራር ያለውን ጠቀሜታ በጥልቀት ለመመልከት እንደ መነፅር እንድትጠቀምበት ነው፡፡ ከእነዚህ ንባቦች ውስጥ አንዱን ስታጠና (ወይም አንተ እና የአንተ መምህር የተስማማችሁበትን) ለክርስቲያናዊ ሚሽን መሠረት የሆነውን ቁልፍ ገጽታ እንደምትገነዘብ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ከራስህ የግል የደቀመዝሙርነት ጉዞ ጋር እንዲሁም እግዚአብሔር በቤተክርስቲያንህ እና በአገልግሎትህ ውስጥ ከሰጠህ የመሪነት ሚና ጋር በቀጥታ እንዴት እንደምታዛምደው መንፈስ ቅዱስ ጥልቅ መረዳት እንዲሰጥህ እንመኛለን ፡፡ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት እንደመሆኑ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄሲስ) ለመስራት የጥናት ክፍሉን በአውዱ ውስጥ መረዳት ያስፈልጋል። በመቀጠልም ዋናውን ትርጉም ከተረዳህ በኋላ ለሁላችንም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መርህ ማውጣትና ይህንም በተጨባጭ ከህይወት ጋር ማዛመድ ይኖርብሃል። ይህን የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥናት በምታደርግበት ወቅት እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ሊያግዙህ ይችላሉ:- 1. በተሰጠው ምንባብ ውስጥ ለተጠቀሱት ዋና አድማጮች እግዚአብሔር መናገር የፈለገው ምንድነው? 2. ከዚህ ምንባብ ልንማረው የምንችለውና ለሁሉም ዘመንና በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ልንወስደው የምንችለው መርህ ምንድነው? 3. ዛሬምመንፈስ ቅዱስ እኔን ከተማርኩትመርህ በመነሳት ምን እንዳደርግ ነው የሚፈልግብኝ? እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ከመለስክ በቀጣይ አሳይመንት ስራህ የግልህን መረዳት ለማቅረብ ዝግጁ ነህ ማለት ነው። አሳይመንት ስራህ ይህን ቅደም ተከተል ተከትሎ መስራት ይረዳሃል፥

ዓላማ

ዝርዝር መግለጫ እና አወቃቀር

Made with FlippingBook - Online catalogs