Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ውስጥ አንዱ ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል፡፡ ፍላጎታችን እና ተስፋችን ቅዱሳት መጻሕፍት የአንተን እና የምታገለግላቸውን ሰዎች ሕይወት በተጨባጭ ለመለወጥ ያላቸውን አቅም እንድትረዳ ነው። ኮርሱን በምትወስድበት ጊዜ የበለጠ ለማጥናት በምትፈልገው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ የንባብ ክፍል (በግምት ከ4-9 ቁጥሮች) ለማጥናት አታመንታ፡፡ የፕሮጀክቱ ዝርዝሮች በገጽ 10-11 ላይ የተካተቱ ሲሆን በዚህ ትምህርት መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ እኛ የምንጠብቀው ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሕይወታቸው ውስጥ እና በአገልግሎት ድርሻቸው ላይ በተጨባጭ እንዲተገብሩት ነው ፡፡ ተማሪው የተማራቸውን መርሆዎች ከተግባራዊ አገልግሎት ጋር አጣምሮ የሚኒስትሪ ኘሮጀክት የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዝርዝሮች በገጽ 12 ላይ የተገለጡ ሲሆን በትምህርቱ መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ የክፍል ሥራ እና የተለያዩ ዓይነት የቤት ሥራዎች በክፍል ትምህርት ወቅት በመምህርህ ሊሰጡህ ወይም በተማሪው መልመጃ (Student Workbook) ውስጥ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ ስለሚፈለገው ነገርም ሆነ የቤት ስራ ስለ ማስረከቢያው ጊዜ ጥያቄ ካለህ መምህርህን ጠይቅ። ለክፍል ውይይት ለመዘጋጀት ተማሪው የተመደበውን ንባብ ከጽሑፉ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት ማንበቡ አስፈላጊ ነው ፡፡ እባክህ በየሳምንቱ ከአንተ የተማሪው የመልመጃ መጽሐፍ ውስጥ “የንባብ ማጠናቀቂያ ቅጽ” ን ተመልከት። ለሚደረጉ ተጨማሪ ንባቦች ተጨማሪ ዋጋ/ነጥብ የማግኘት እድል ይኖራል ፡፡ በትምህርቱ መጨረሻ ላይ መምህርህ በቤት ውስጥ የሚጠናቀቅ የመጨረሻ ፈተና (የተዘጋጀ ጥራዝ) ይሰጥሃል። በትምህርቱ ውስጥ የተማርከውን እና በአገልግሎትህ ላይ ያለህን አስተሳሰብ ወይም አሠራር እንዴት እንደሚቀይረው አንድታሰላስል የሚረዳ ጥያቄ ትጠየቃለህ፡፡ ስለ መጨረሻው ፈተና እና ሌሎች ጉዳዮች መምህርህ አስፈላጊውን መረጃዎች ይሰጥሃል።
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት
የክፍል እና የቤት ሥራ ምደባዎች
ንባቦች
ከቤት-የሚሰራ የማጠቃለያ ፈተና
ውጤት አሰጥጥ የሚከተሉት ውጤቶች በክፍለ-ጊዜው መጨረሻ ላይ በዚህ ክፍል ውስጥ ይሰጣሉ እናም በእያንዳንዱ ተማሪ መዝገብ ላይ ይቀመጣሉ።
A - የላቀ ሥራ
D - የማለፊያ ሥራ
B - በጣም ጥሩ ሥራ
F - አጥጋቢ ያልሆነ ሥራ
C - አጥጋቢ ሥራ
I - ያልተሟላ
ለእያንዳንዱ የመጨረሻ ክፍል አግባብነት ያላቸው ውጤቶች ይሰጣቸዋል ፣ ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚሰጠው የክፍል ነጥብ በጠቅላላው አማካይነት ውጤት ላይ የሚታሰብ ይሆናል። ያልተፈቀደ የስራ መዘግየት ወይም ሥራዎችን አለማስረከብ በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፣ ስለሆነም እባክህ አስቀድመህ አቅደህ ከመምህርህ ጋር ተነጋገር።
Made with FlippingBook - Online catalogs