Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 1 1
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ክርስቲያን ሚሽን እና ከተማ ሴግመንት 1፡መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የከተማ መረዳትን መለየትና መተርጎም
CONTENT
ቄስ ዶ/ር ኤል ዴቪስ
የከተማ ጽንሰ ሃሳብ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ማዕከላዊ ሃሳብ ሲሆን ስለጥንታዊው የከተማ ባህሪያት ጠቅለል ያለ ዕይታ ይሰጠናል፡፡ በጥንታዊው አለም ያሉ ከተሞች ከመንደሮች የተለዩ በመሆናቸው በግንቦች የተቀጠሩ የቤቶችና የህንጻዎች ስብስብ ቢሆኑም ለዘመናቸው የሚመጥኑና አስገራሚዎቹ ነበሩ፤ አንዳንዶቹ ከተሞች ደግሞ ለጥበቃና ለአቅርቦት በሌሎች ከተሞች ላይ ጥገኞች ነበሩ፡፡ በጥንታዊው አለም የነበሩት ከተሞች በአንጻራዊነት አነስተኛ ንድፍ የሌላቸው፤ በወፍራም ግንቦችና ከፍ ባሉ ማማዎች የተጠናከሩና የመንግስትና የባለስልጣናት መቀማመጫዎች ነበሩ፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ከተዘረዘሩት የከተማ መንፋሳዊ ትርጉም አንጻር ከተሞች ከሰው አመጽና ምንዝር (ሄኖክ፣ የቃየን ከተማ)፣ ከነጻነትና እብሪት (በባቤል ግንብ እንደሆነው)፣ ክፋትና አምላክ አልባነት (እንደ ባቢሎን) ጋር የተዛመዱ ነበሩ፡፡ ከተሞች በኃጢአታቸው ምክንያት በእግዚአብሔር ይፈርድባቸው ነበር (ለምሳሌ ሰዶምና ገሞራ፣ ኢያሪኮና ነነዌ)፤ እንዲሁም በሐሰተኛ የደህንነትና የኃይል ስሜታቸው ይወገዙ ነበር (በተለይም ኢየሩሳሌም)፡፡ እግዚአብሔር ከተማን እንደ መኖሪያውና የበረከት ስፍራው የወሰደበትን ምስል ስንመለከት ኢየሩሳሌምን ለራሱ መምረጡና በምድር ላይ ለምስጋና እንድትሆን መወሰኑን እንረዳለን፡፡ ከዚያም ባሻገር የአመጻን ምስል ወደ መሸጋገሪያ ምስል (ማለትም የመማጸኛ ከተሞች)፤ እና የራሱ ይቅር ባይነት እና በረከት ማወቂያ መለማመጃ ቦታ (ዮሐንስና የነነዌ ተሞክሮ) በማድረግ ውስጥ የእግዚአብሔር አሰራር ታይቷል፡፡ ከእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት የተነሳ በፍርዱ ፊት ለሚመለሱና በቅጣቱ ፊት ምህረቱን ለሚሻ የትኛውም ከተማ እግዚአብሔር ተስፋን ሰጥቷል፡፡ ለዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የከተማ መረዳትን መለየትና መተርጎም ለተሰኘ ሴግመንት አላማችን የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት እንድንችል ነው:- • የከተማ ጽንሰ ሃሳብ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ማዕከላዊ ሃሳብ ሲሆን ስለጥንታዊው የከተማ ባህሪያት ጠቅለል ያለ ዕይታ ይሰጠናል፡፡ በጥንታዊው አለም ያሉ ከተሞች ከመንደሮች የተለዩ በመሆናቸው በግንቦች የተቀጠሩ የቤቶችና የህንጻዎች ስብስብ ቢሆኑም ለዘመናቸው የሚመጥኑና አስገራሚዎቹ ነበሩ፤ አንዳንዶቹ ከተሞች ደግሞ ለጥበቃና ለአቅርቦት በሌሎች ከተሞች ላይ ጥገኞች ነበሩ፡፡ በጥንታዊው አለም የነበሩት ከተሞች በአንጻራዊነት አነስተኛ ንድፍ የሌላቸው፤ በወፍራም ግንቦችና ከፍ ባሉ ማማዎች የተጠናከሩና የመንግስትና የባለስልጣናት መቀማመጫዎች ነበሩ፡፡ • በቅዱሳት መጻሕፍት ከተዘረዘሩት የከተማመንፋሳዊ ትርጉም አንጻር ከተሞች ከሰው አመጽና ምንዝር (ሄኖክ፣ የቃየን ከተማ)፣ ከነጻነትና እብሪት (በባቤል ግንብ እንደሆነው)፣ ክፋትና አምላክ አልባነት (እንደ ባቢሎን) ጋር የተዛመዱ ነበሩ፡፡ ከተሞች በኃጢአታቸው ምክንያት በእግዚአብሔር ይፈርድባቸው ነበር (ለምሳሌ ሰዶምና ገሞራ፣ ኢያሪኮና ነነዌ)፤ እንዲሁም በሐሰተኛ የደህንነትና የኃይል ስሜታቸው ይወገዙ ነበር (በተለይም ኢየሩሳሌም)፡፡
የሴግመንት 1 ማጠቃለያ
3
Made with FlippingBook - Online catalogs