Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 2 1

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

መ / የእግዚአብሔር ሥራ አንድምታዎች - ለከተማይቱ ተስፋ አለ ፣ ምክንያቱም አምላካችን መልካም እና ይቅር ባይ አምላክ ስለሆነ ህዝቦች እንዲጠፉ አይፈልግም!

1. ደም አፋሳሽ ከተማን ጨምሮ ንሰሃ በሚገቡ ከተሞች ላይ ቁጣውን ይገታል ፣ መዝ. 78.38

2. ንስሐ ለሚገቡት ምህረቱ በፍርድ ላይ ድል ይነሳል ፣ ሆሴ. 11.8-9

ማጠቃለያ

» የጥንታዊቷ ከተማ ፅንሰ-ሀሳብ የተወለደው በራሷ ካላት መተማመን ፣ እብሪተኝነት እና በእግዚአብሔር ላይ ከማመፅ ጋር ካለው ግንኙነት ነው ፡፡ ከነነዌ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ፣ እግዚአብሔር ከተማን የቀጣው በክፋትዋ እና በመተላለፏ ምክንያት ነው ፡፡ » በከበረውና ሉዓላዊ በሆነው ምርጫው ከተማን ከራሱ መገኘት ጋር በማያያዝ ወደ መጠጊያነት ፣ የንስሃ እና ወደ የተሐድሶ ስፍራነት በራሱ የመለወጥን ሀሳብ ተቀብሏል ፡፡

3

መሸጋገሪያ 1

እባክህ በአነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱት ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመሰጠት ሞክር፡፡ በዚህ ክፍል የከተማን ጽንሰ ሃሳብ አጀማመርና እድገት ተመልክተናል፡፡ ጥንታዊቷ ከተማ ከራስ መተማመን፣ እብሪትና አመጽ ጋር በተሳሰረ መንፈስ ተጸንሳ፣ በቃየን አመጽና እብሪት ተወልዳለች፡፡ በበርካታ አጋጣሚዎች እግዚአብሔር በከተማዋ ላይ በጣኦት አምልኮ፣ በፍትህ መጓደልና በክፋት ምክንያት ፍርድን እምጥቷል፡፡ ሆኖም ግን ከእግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር የተነሳ እርሱ ራሱ በገዛ ሉአላዊነቱ ከተማዋን ለእርሱ መኖሪያነትና እንደ መሸሸጊያ፣ የንስሐና የተሀድሶ ስፍራ በመቀየር መርጧታል፡፡ የኧርባን ክርስቲያን መሪ እንደመሆንህ መጠን እነዚህን ጽንሰ ሃሳቦች በአግባቡ ተረድተህ አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ መልሶችህን በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ፡፡ 1. ስለ ጥንታዊቷ ከተማ አጠቃላይ ባህሪያት የተወሰኑ ዕይታዎችን አስቀምጥ። ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር ነው ይህ ጽንሰ ሃሳብ የመነጨው? የጥንት ከተሞች ከመንደሮች የሚለዩት በምንድን ነው? 2. የከተሞችን ምስረታ ከቃየን ጋር ማገናኘቱ ለምን እንደዚህ አሰፈላጊ መንፈሳዊ ጽንሰ ሃሳብ ሆነ? በባቤል ከተከሰተው ክስተት ስለከተማ ባህሪ ምን እንማራለን? በተመሳሳይ የባቢሎን ከተማ ስለከተሞች አምላክ የለሽነት የሚነግረን ነገር ምንድን ነው? 3. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኃጢአት ታቸውና በንስሀ ባለመግባታቸው ምክንያት የእግዚአብሄር ፍርድ ያገኛቸው ከተሞች የትኞቹ ናቸው?ኢየሩሳሌም በተለይም ለራሷ ስላላት የተሳሳተ የደህንነትና የኃይል ስሜት ተወገዘች?

የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሽ

Made with FlippingBook - Online catalogs