Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 2 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
4. ምንም እንኳን ከተማዋ ከሰው ልጆች አመጽ ጋር የተቆራኘች ቢሆንም እግዚአብሔር የራሱ የመኖሪያ ስፍራና የበረከት ምልክት እድርጎ የወሰዳት እንዴት ነው? የጽዮን (ኢየሩሳሌም) ምሳሌ ይህን የቸርና ሉአላዊ አምላክ ምርጫ የሚያሳየው እንዴት ነው? እግዚአብሔር ከመገኘቱና ከክብሩ አንጻር ስለ ኢየሩሳሌም የወሰነው ምንድን ነው? 5. ከእግዚአብሔር ጋር የተዛመደውን “መለኮታዊ ምፀት” (divine irony) ምንነት ከከተማ አለማዊው ምስል እና የእግዚአብሔርን ወደ አዲስና የተለየ ምስል መቀየር አንጻር አስረዳ፡፡ 6. የእግዚአብሔር የስድስቱን የመማጸኛ ከተሞች ንድፍ መስራት እና ነነዌን ይቅር ማለት ለአለማዊና ያልተዋጀች ከተማ ያለንን አመለካከት እንዴት ሊቀይር ይችላል? አብራራ 7. በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ ለሚገባ የትኛውም ከተማ በፍርድና በሞት ፊት እንኳን ሳይቀር እግዚአብሔር ፊቱንና ምህረቱን እንደሚመልስላቸው ይመስላቸዋል የሚለውን እውነት በምን ማመካኘት እንችላለን? 8. ከተማን ከአመጻ መገኛነት ወደ መገኛ ስፍራው እግዚአብሔር ከቀየረበት አንጻር ስለኛ የክርስቲያኖች ሃላፊነት የራይከንን ትንተና ከዚህ በታች አንብብ። እግዚአብሔር ከተማን ከቀየረበት አንጻር እኛ እንዴት ማድረግ እንዳለብን ራይከን ስላለው ነገር ያንተ አቋም ምንድን ነው?
3
የእግዚአብሔር ከተማን መለወጥ ዛሬ በህይወታችን ላይ ምን ተጽዕኖ ሊኖረው ይገባል?
የከተማ ምስል ከሚፈጥረው ውስብስብ ሁኔታ አንጻር የክርስቲያን ህይወት የተወሰኑ ባህርያትን ማሳየት አለበት፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ክርስቲያን ህግን በመፈጸም ሳይሆን በእምነት በሆነ ጽድቅ የእግዚአብሔር ከተማ ዜጋ ነው፡፡ ጳውሎስ በምሳሌያዊ ገለጻው እነዚህን ሁለት “የኋላይኛይቱ ኢየሩሳሌም” እና “የአሁኒቱ ኢየሩሳሌም” አመለካከቶችን ያነጻጽራል (ገላ 4፡ 22-26 ፊሊ 3፡20)፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን ለማጽደቅ የሚሞክሩ ሰዎች የኋለኛዋ ከተማ ዜጎች ሲሆኑ በእምነት ወደ ክርስቶስ የሚመለከቱት ደግሞ የቀደመችው ከተማ ዜጎች ናቸው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የክርስቲያን ህይወት ከውድቀቱ አንስቶ እስከ ፍጻሜው ድረስ እግዚአብሔር እንደሰጠው የስነስርዓት ምንጭ ለሰብዓዊው መንግስት በሚደረግ መገዛት የሚታወቅ ነው (ማቴ 22፡21፣ ሮሜ 13፡1-7፣ 1ኛጴጥ 2፡13-17)፡፡ ስለሆነም አማኝ ልክ እንደ ዮሴፍ ወይም እንደ ዳንኤል በዙሪያው ካለው አለም ጋር ተዛምዶ መኖር አለበት። Epistle of Diognetus - Defense of Christianity የተሰኘው ጥንታዊው የዲዮግኔተስ ደብዳቤ ክርስቲያኖችን ሲገልጻቸው እንዲህ ብሏል:- “በገዛ አገራቸው የሚኖሩ፣ ግን እንደ መጻተኞች ብቻ፣ እንደ ዜጎች ደግሞ የኃላፊነት ድርሻቸውን ይወጣሉ፤ እናም እንደ እንግዶች መከራን ይታገሳሉ፡፡ እያንዳንዱ የባእድ አገር ለእነርሱ እንደ
Made with FlippingBook - Online catalogs