Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 2 3

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

አገራቸው ነው፥ እና እያንዳንዱም አገራቸው እንደ ባዕድ አገር ነው... ኑሮአቸው በምድር ላይ ነው፥ ነገር ግን ዜግነታቸው በሰማይ ነው” (ኤፒስትል ቱ ዲዮግኔተስ 5፡1-9)፡፡ ሶስተኛው የእምነት ሕይወት እግዚአብሔር የራሱን ከተማ ለመመስረት በሰጠው ታላቅ ተስፋ ላይ የመተማመን ህይወት ነው፡፡ ዕብራውያን ስለ አብርሃም እምነት እንዲህ ይላል:- “ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና (ዕብ 11፡9-10)፡፡ ሰማያዊ ዜግነት በህይወት ፈተናዎች ላይ መተማመኛ መሰረት እና ህይወት የሚመራበት ግብ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን የአዲስ ኪዳን አማኞችን ከብሉይ ኪዳን አቻዎቻቸው የሚለዩአቸው ጉልህ ልዩነቶች አሉ፡፡ ስለ ኋለኞቹ እንዲህ ይላል:- “እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ።” (ዕብራውያን 11፥13)። እስከ ፍጻሜ ድረስ (1ኛጴጥ 1፡1 2፡11) ክርሰቲያን በዚህ ሁኔታ መቀጠል ያለበት ቢሆንም ጥልቅና እውነተኛ በሆነ መንገድ ከክርስቶስ የማስተሰርየት ስራ የተነሳ ሐጅ ፍጻሜውን አግኝቷል (ኤፌ 2፡19)፡፡ በኢየሱስ ጽናትና በመተካት ባሳየው ታማኝነት (ዕብ 12:2) አማካኝነት ክርስቲያኖች “ወደ ጽዮን ተራራ እና ወደ ህያው እግዚአብሔር ከተማ፣ ወደ ሰማይቱ ኢየሩሳሌም ደርሰዋል” (ዕብ 12፡22)። ስለዚህ የእግዚአብሔር ከተማ ጂኦፖለቲካዊ መገለጫ ገና ወደፊት ቢሆንም በኢየሱስ ስራ ለዘላለም በሰማያት የተቋቋመ ሲሆን በኢየሱስ የሚያምኑ ደግሞ ከእርሱ ጋር ካላቸው ህብረት የተነሳ (ኤፌ 2፡6) አስቀድመው በዚያ መኖር ጀምረዋል (ዮሐ 14፡1-3)፡፡ ስለዚህ የኢየሱስ ቤተክርስቲያን አሁን በአለም ውስጥ “በተራራ ላይ እንዳለች” (ማቴ 5፡14) ቅድስት ከተማ ትኖራለች፡፡ አውግስቲን እንዲህ ገልጾታል:- “ትሁት ከተማ የቅዱሳን ሰዎች እና የመልካም መላዕክት ማህበረሰብ ናት፡፡ አንደኛዋ ከተማ በእግዚአብሔር ፍቅር የተጀመረች ሌላኛዋ ደግሞ ጅማሬዋን በራስ ፍቅር ላይ አደረገች” (የእግዚአብሔር ከተማ 14፡13)፡፡

3

~Leland Ryken. The Dictionary of Biblical Imagery. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000. p. 153-154.

Made with FlippingBook - Online catalogs