Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 2 4 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ክርስቲያን ሚሽን እና ከተማ ሴግመንት 2 - ምክንያታዊነት ወሳኝ ለሆነ የከተማ ሚሽን
ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ
የሴግመንት 2 ማጠቃለያ
ዛሬ ባለው የሚሽን እንቅስቃሴ ውስጥ ኧርባን ሚሽን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የሚሆንባቸው ሶስት ወሳኝ ምክንያቶች አሉ፤ እነዚህም፡- ከተማ በአለም ውስጥ የተጽዕኖ፣ የሃይልና የመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች መቀመጫ ናት፤ ለተጠቁ፣ ለተጨቆኑና ለድሆች መጠጊያ ናት፤ እንዲሁም ከተማ እንደመንፈሳዊ መዳረሻችና ርስታችን ይታያል፡፡ ከተማ ለኢየሱስ እና ለደቀመዛሙርቱም አገልግሎት ያበረከተው ድርሻ ከፍ ያለ ነው፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ራሱ ከተማ ላይ በጣም የተመሰረተ ሲሆን መንግስቱን የመስበክ ስራውም ኢየሩሳሌም ውስጥ ነበር፤ በተጨማሪም ክርስትና አንድ ከተማ ውስጥ ተወልዶ በወቅቱ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በሮማ ግዛት ውስጥ ወደ ነበሩት ታላቅ ከተሞች (እንደ ደማስቆ፣ አንጾኪያ፣ ፊሊፒሲውስ፣ ተሰሎንቄ፣ አተንስነ ሮም) ተስፋፍቷል፡፡ በኢየሱስና በሐዋርያት ዘመን በነበሩ ከተሞች ውስጥ የነበሩ ተመሳሳይ ችግሮች እና እድሎች አሁን ባሉት ዘመናዊ ከተሞች ውስጥም ይታያሉ፡፡ እነዚህ ዘመናዊ ከተሞች በመጠን፣ በስፋትና በህዝብ ብዛትም ታላላቅ ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ከተሞች የመንግስት፣ የትምህርት፣ የጤና-ክብካቤ፣ የመረጃ፣ የመዝናኛ፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ የህግ፣ የወታደራዊና የሃይማኖት ተቋማት በመሆን ያገለግላሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከተሞች በትኩረታቸውና በአይነታቸው ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ የባህል፣ የፖለቲካና የአስተዳደር፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ ታሪካዊ ወይም ዋና ከተማ በመባል የአለማችን ዘመናዊ ከተሞች ለተጠቁ፣ ለተጨቆኑና ለድሆች መጠጊያ በመሆን ያገለግላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው እይታ እግዚአብሔር ለድሆች ስላለው ልብ ይመሰክርልናል፤ በመሆኑም እግዚአብሔር ስለድሆች ግድ የሚለው ከሆነ አሜሪካ ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና በድህነት ስለሚሰቃዩት ከተሞችም ግድ ይለዋል ማለት ነው፡፡ ከተማ የመዳረሻችንና የርስታችን ምስል እና ምሳሌ ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔር የሚገኝባትንና ኢየሱስም እንደ ሁለት ጌታ የሚደነቅባትን አዲሲቷን ኢየሩሳሌምን ያሳያል፡፡ ስለዚህም የሚሽን ዋናው ግብ የአለምን ከተሞች የአማኞች ሁሉ እናት የሆነችውን አዲሲቷን ኢየሩሳሌምን እንዲሞሉ መማረክ ነው የእግዚአብሔር የመጨረሻው የከተማ ተሃድሶ ፕሮጀክት)፡፡ በመሆኑም ከተማ በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በዘመናዊው አለም ካለው ጠቀሜታ አንጻር በሚሽን አገልግሎት ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ የዚህ ምክንያታዊነት ወሳኝ ለሆነ የከተማ ሚሽን የተሰኘ ሴግመንት አላማ የሚከተሉትን ማየት ትችል ዘንድ ነው:- • ዛሬ ባለው የሚሽን እንቅስቃሴ ውስጥ ኧርባን ሚሽን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የሚሆንባቸው ሶስት ወሳኝ ምክንያቶች አሉ፤ እነዚህም፡- ከተማ በአለም ውስጥ የተጽዕኖ፣ የሃይልና የመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች መቀመጫ ናት፤ ለተጠቁ፣ ለተጨቆኑና ለድሆች መጠጊያ ናት፤ እንዲሁም ከተማ እንደመንፈሳዊ መዳረሻችና ርስታችን ይታያል፡፡ • ከተማ ለኢየሱስ እና ለደቀመዛሙርቱም አገልግሎት ያበረከተው ድርሻ ከፍ ያለ መሆኑን ትረዳለህ፡፡
3
Made with FlippingBook - Online catalogs