Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 2 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• የኢየሱስ አገልግሎት ራሱ እንዴት በከተማ ስራ ላይ እንዴት እንደተመሰረተ ማሳየት ትችላለህ፤ መንግስቱን የመስበክ ስራው ኢየሩሳሌም ውስጥ ነው፡፡ በተጨማሪም ክርስትና በአንድ ከተማ ውስጥ ተወልዶ እንዴት በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በሮማ ግዛት ውስጥ በነበሩት ታላቅ ከተሞች (እንደ ደማስቆ፣ አንጾኪያ፣ ፊሊጵስዩስ፣ ተሰሎንቄ አቴንስና ሮም) እንዴት እንደተስፋፋ ትረዳለህ፡፡ ሐዋሪያዊ አግልግሎትም (የጳውሎስን ጉዞዎች ጨምሮ) በባህሪው ከተማ ተኮር ነው፣ ከተሞች ወደ ታዛቁ የሮማ ግዛት መግቢያ በሮች ነበሩ፡፡ • በኢየሱስና በሐዋርያት ዘመን በነበሩ ከተሞች ውስጥ የነበሩ ተመሳሳይ ችግሮች እና እድሎች አሁን ባሉት ዘመናዊ ከተሞች ውስጥም የመታየታቸውን ዕውነታ ትገነዘባለህ፡፡ እነዚህ ዘመናዊ ከተሞች በመጠን፣ በስፋትና በህዝብ ብዛትም ታላላቅ ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ከተሞች የመንግስት፣ የትምህርት፣ የጤና-ክብካቤ፣ የመረጃ፣ የመዝናኛ፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ የህግ፣ የወታደራዊና የሃይማኖት ተቋማት በመሆን ያገለግላሉ፡፡ • አንትሮፖሎጂስቶች ከተሞችን ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር በትኩረታቸውና በአይነታቸው ለይተው ያስቀምጣሉ፡፡ የባህል፣ የፖለቲካና የአስተዳደር፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ ታሪካዊ ወይም ዋና ከተማ በመባል ተከፍለዋል። • ለተጠቁ፣ ለተጨቆኑና ለድሆች መጠጊያ በመሆን እንደሚያገለግላሉ መረዳት ትችላለህ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው እይታ እግዚአብሔር ለድሆች ስላለው ልብ ይመሰክርልናል፤ በመሆኑም እግዚአብሔር ስለድሆች ግድ የሚለው ከሆነ አሜሪካ ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና በድህነት ስለሚሰቃዩት ከተሞችም ግድ ይለዋል ማለት ነው ስለሚለው ክርክር ግንዛቤ ትጨብጣለህ፡፡ • ከተማ እንዴት የመዳረሻችንና የርስታችን ምስል እና ምሳሌ እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች በመነሳት ማጠቃለያ መስጠት ትችላለህ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ስለሚገኝባትና ኢየሱስም እንደ ሁሉ ጌታ የሚደነቅባት አዲሲቱ ኢየሩሳሌምን እንዲሞሉ ነው የእግዚአብሔር የመጨረሻ የከተማ ተሃድሶ ፕሮጀክት)፡፡ • የሚሽን ዋናው ግብ የአለምን ከተሞች የአማኞች ሁሉ እናት የሆነችውን አዲሲቷን ኢየሩሳሌምን እንዲሞሉ መማረክ ነው የእግዚአብሔር የመጨረሻው የከተማ ተሃድሶ ፕሮጀክት)፡ • ከተማ በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በዘመናዊው አለም ካለው ጠቀሜታ አንጻር በሚሽን አገልግሎት ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ I. ከተማ የተጽዕኖ፣ የሃይልና የመንፈሳዊ እንቅስቃሴ መቀመጫ ናት ማቴዎስ 9 ፥ 35-38 - “ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር። ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው።”
3
የቪድዮ ሴግመንት 2 ዝርዝር
Made with FlippingBook - Online catalogs