Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 3

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሀፍ ቅዱሳዊ መሰረት - ክፍል 1

ት ም ህ ር ት 1

የትምህርቱ አላማ

ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ • ጠቅለል ያለ “ፕሮሌጎሜና” (“የመጀመሪያ ቃል”) ወይም የሚሽንን ትልቁን ምስል ትረዳለህ፡፡ • ሚሽን “እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ስራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት ለሰው ልጆች ሁሉ ያዘጋጀው የድነትና የቤዛነት ዓዋጅ” እንደሆነ ትገነዘባለህ፡፡ • በክርስቶስ ኢየሱስ ሰውነትና ስራ ላይ በተመሰረተውና በምስሎች፥ በስዕሎችና በታሪኮች ውስጥ በቀረበው የታሪክ ሂደት አማካኝነት እግዚአብሔር ለፍጥረታት ሁሉ ስላለው ሚሽን በአግባቡ ትረዳለህ፡፡ • አራቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሚሽን ማዕቀፎች/ምስሎች ማስቀመጥ ትችላለህ፥ ማለትም ሚሽን እንደ ዘወትር ክስተት (በታሪኩ ውስጥ እግዚአብሔር እንደ ዋና ገፀ ባህሪ) ፤ እንደ መለኮታዊ ቃል ኪዳን ውሳኔ (የእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ኪዳን መጠበቅ)፤ እንደ ዘመናት የፍቅር ግንኙነት ( እግዚአብሔር ለተዋጀው ህዝቡ እንደ ሙሽራ) እና እንደ አማጵያን ጦርነት (እግዚአብሔር በፍጥረት አለም ላይ መንግስቱን በ ድጋሚ እንደሚመሰርት ጦረኛ)፡፡ • ከእግዚአብሔር የማይታጠፈው አላማ በመነሳት በዘወትር ክስተት ውስጥ ያሉትን ዋና ዋና ነገሮች ማሳየት ትችላለህ። ከዘመን በፊት (የእግዚአብሔር ቅድመ ህልውና እና አላማ ፣ የአመፃን ምስጢርና የኢ-ፍትሃዊነትን ኃይል የሚያሳይ)፤ የጊዜ መጀመሪያ (የአጽናፈ አለሙንና የሰው ልጅ ፍጥረትን ውድቀትና እርግማን ፕሮቶኢቫንጌሊየምን፤ የኤደን መጨረሻ፤ የሞትን አገዛዝና የመጀመሪያዎቹን የጸጋ ምልክቶች ያጠቃልላል)፤ የጊዜ መገለጥ (አብርሃማዊውን ተስፋ፣ ዘጸአትን፣ የመሬትን ምርኮ፣ የከተማ - መቅደስ - ዙፋን፣ የግዞት እና የቅሬታዎችን መመለስ ያጠቃልላል።) • ስለ ዘመን ፍጻሜ የማይታጠፈው የእግዚአብሔር ተስፋ፤ የኢየሱስን ስጋ መልበስ፤ የመንግስቱን መገለጥ፤ የኢየሱስን ህማማት፤ ሞት፤ ትንሳኤና እርገት እንደሚያጠቃልል ትገነዘባለህ፡፡ ስለመጨረሻው ዘመን ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ፤ የቤተክርስትያንን ተሀድሶ፤ የአህዛብን መካተትና የአለማቀፋዊውን ሚሽን ማጠቃለል ትረዳለህ፡፡ • እንዴት የእግዚአብሔር ኡአላዊ አላማ የሰው ልጆችን ታሪክ እንደሚጽፍ ፤ በመለኮታዊ የታሪክ ሂደት ውስጥ የእግዚአብሔር እንደ ዋና ገፀ ባህሪ መሆን፤ ሚሽን በዘመን መጀመሪያ የጠፋውን እንደማደስ ፤ እና እግዚአብሔር የሰጠንን ድርሻ ለመወጣት አህዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት በማድረግ ሚሽን እንደ ዘወትር ክስተት የሚኖረውን ምልከታ ትረዳለህ፡፡

1

Made with FlippingBook - Online catalogs