Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 3 0 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
4. የዎርልድ ኧርባናይዜሽን ፕሮስፔክትስ (የተባበሩት መንግስታት) ዘገባ እንዲህ ይላል:- “ልክ ከሚሊኒየሙ መቀየር በኋላ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ውስጥ የከተማ ነዋሪዎች በባህላዊ ገጠራማ አካባቢዎች ከሚገኙት ይበልጣሉ ... በ2006 ግማሹ የዓለም ህዝብ የከተማ ነዋሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ የከተማው ነዋሪዎች ብዛት ከገጠር ነዋሪዎች አንጻር በሦስት እጥፍ በፍጥነት እያደገ ነው ፡፡ በ2030 ከአምስት ሰዎች መካከል ሦስቱ በከተማ አካባቢዎች የሚኖሩ ይሆናሉ ፡፡”
5. በምድር ላይ ካሉ ሌሎች ነዋሪዎች ሁሉ የበለጠ የከተማ ነዋሪዎች አሉ ፤ ይህም አሁን ወቅታዊው እውነታ ሆኗል።
መ / ከተሞች የአገልግሎት እና የተጽእኖ ማዕከላት ናቸው ፡፡
1. ከተሞች የመንግስት ፣ የትምህርት ፣ የጤና-ክብካቤ ፣ የመረጃ ፣ የመዝናኛ ፣የንግድ ፣ የኢንዱስትሪ ፣ የህግ ፣ የወታደራዊ እና የሀይማኖት ማዕከላት ናቸው ፡፡
3
2. የዓለምን ታላላቅ ከተሞች - ዋሽንግተን ፣ ኒው ዮርክ ፣ ሴውል ፣ ካይሮ ፣ ብራዚሊያ ፣ ኢስታንቡል ፣ ሞስኮ ፣ ስቶክሆልም ፣ ለንደን ፣ ፓሪስ ፣ ቦነስ አይረስ ፣ አምስተርዳም ፣ ሎስ አንጀለስ እና የመሳሰሉትን ሳይጠቅሱ ዘመናዊ ስልጣኔን ማሰብ አይቻልም ፡፡
ሀ. የባህል ከተሞች (ዓለምን በፋሽን ፣ በጥበባት እና ሀሳቦች የሚመሩ) ለምሳሌ ፓሪስ ፣ ኦክስፎርድ ፣ ቦስተን ፣ ሳን ፍራንሲስኮ
ለ. የፖለቲካ እና አስተዳደራዊ ከተሞች (ዓለም አቀፍ የውሳኔ ሰጪ ማዕከላት ወይም የመንግስታት እና ቢሮዎቻቸው መገኛዎች) ለምሳሌ ዋሽንግተን ፣ ሞስኮ ፣ ኒው ዴልሂ
ሐ. የኢንዱስትሪ ከተሞች (ጫጫታ የሞላባቸው ፣ የፋብሪካ እና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ማዕከላት) ለምሳሌ ቦምቤይ ፣ ሳኦ ፓውሎ ፣ ቺካጎ - ጋሪ አካባቢ
Made with FlippingBook - Online catalogs